Forward from: ኢትዮ ትረካ
✅✅ የአያቴ ትምህርት
----------------------
🔅 ከዓለማየሁ ገላጋይ
አያቴ የራሷ ስብከት እንዳላት ያወኩት አሁን ነው። ደ ስ ያላላት ድርጊት ላይ ተመርኩዛ ትሰብከኛለች። አንድ ቀን ታናሽ ወንድሜን እየኮረኮርኩ ሳስቀው ደርሳ
"ሰማይ ቤት ነፍስህ የሳንሳ ተይዛ በመልአክቶች ክንፍ ትኮረኮራለች። የነፍስ ጉያ ስስ ናት። መጀመሪያ ያቺ ነፍስ ትስቃለች፣ ትስቃለች፣ በኋላ ሲበዛባት ታለቅሳለች። አለቀሰች ብሎ የሚለቃት ያለ እንዳይመስልህ። መልአኩ አንቺ ነፍስ በቁመናሽ ትሠሪው የነበረውን የኃጢያትሽን ዋጋ ነይ ተቀበይ እያለ መኮልኮሉን ይቀጥላል። ያቺ ነፍስ "ከመዝኑ መኮርኮር መሪር ትላለች"
"ምን ማለቷ ነው?"
"እውነት መኮርኮር እንዲህ መሪር ነውን ስትል ነዋ"
መኮርኮር እንዲህ ከከፋ መቆንጠጥስ?
ለአያቴ ነፍስ አዘንኩላት።
---------------
ው ል ብ ታ
📖 📖 📖 📖 📖
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
ኢትዮ ትረካ