ጭር ሲል አልወድም!
═══•✦•═══
✍ አይዳ ታደሰ
'
አልወድም ዝምታ
ሲሆን ያለ ቦታ!!
ሕይወትን ያለ ሳቅ
ሀዘንን ያለ ማቅ፣
ለደስታ እንባ ሳይፈስ
ካ'ንጀቴ ጥግ አይደርስ።
ዝምታ እወዳለሁ
ውስጠቴን አያለሁ፣
በፀጥታ ዜማ
የልቤን ስሰማ
የምደርስ ያኔ ነው
ከእውነታው ማማ።
አንዴ ከደረስኩኝ፣
ከሃቁ ዳገት ጫፍ
ቧጥጬ ከቆምኩኝ
ዝምታን አ'ለምድም
ፍትህ እስኪወለድ
"ጭር" ሲል አልወድም!!
══════════
📔 "አልጽፍም"
🗓 2016 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks
═══•✦•═══
✍ አይዳ ታደሰ
'
አልወድም ዝምታ
ሲሆን ያለ ቦታ!!
ሕይወትን ያለ ሳቅ
ሀዘንን ያለ ማቅ፣
ለደስታ እንባ ሳይፈስ
ካ'ንጀቴ ጥግ አይደርስ።
ዝምታ እወዳለሁ
ውስጠቴን አያለሁ፣
በፀጥታ ዜማ
የልቤን ስሰማ
የምደርስ ያኔ ነው
ከእውነታው ማማ።
አንዴ ከደረስኩኝ፣
ከሃቁ ዳገት ጫፍ
ቧጥጬ ከቆምኩኝ
ዝምታን አ'ለምድም
ፍትህ እስኪወለድ
"ጭር" ሲል አልወድም!!
══════════
📔 "አልጽፍም"
🗓 2016 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks