💥 በኢትዮጵያ ተወልዶ ሕንድን የገዛው ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ሐረር ተወልዶ ሕንድን የገዛው ያልተነገረለት ኢትዮጵያዊ
ዛሬ በፔካ ቻናል በኢትዮጵያ ተወልዶ ወደ ሕንድ በባርነት ከተወሰደ በኋላ ሕንድን ስለገዛው የ16ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊ የምናይ ይሆናል።ሀገራችን ኢትዮጵያ አስገራሚና ያልተፈቱ ታሪክ ካላቸው የአለም ሀገራት መሃል እንደሆነች የምናውቀው ጉዳይ ነው። ከቄሱ ዮሐንስ ጀምሮ ሌሎችም አለምን የሚያጠያይቁ ነገስታት የነበሩባት ምድር ነች። በሆነ የታሪክ ጊዜ ውስጥ የስልጣኔ ማማ ላይ ደርሳ ሙሉ አፍሪካን ከዛም አልፎ ገዝታለች እየተባለ ሲነገር ሰምተናል።ምናልባት ለማመን ይከብድ ይሆናል ነገር ግን ነገሩ እውነታ ነው። ዛሬው ከኒህ አስደናቂ ታሪኮች መሃል አንዱ የሆነውን የማሊክ አምባርን ወይንም በኢትዮጵያዊ መጠሪያው “ቻፑ” እንመለከታለን።
መልካም ንባብ🙌
ቻፑ ወይም ማሊክ አምባር የተወለደው በ1540 አ.ም ገደማ በሐረርጌ አካባቢ ነበር። በማእከላዊው ኢትዮጵያ የሚገኙት የሐረርጌ ቀዝቃዛ ወጣ ገባ ተራራማ ስፍራዎች ከፍታቸውንና አቀበታማ ሸለቆዎች የአምባር የልጅነት ትውስታዎች ናቸው። ስለ አምባር የልጅነት ጊዜ የሚገልጹ የሰነድ ማስረጃዎች አነስተኛ ቢሆኑም እንኳን፣ ቻፑ ተብሎ ይጠራ እንደነበር የሚያሳዩ በርካታ ማጣቀሻዎች አሉ። በሕይወት ዘመኑ ውስጥም በስሙ በተለያየ አጠራር ይጠራበት የነበረ ሲሆን። በሙግሃል መዛግብቶች “አምባርጂኡ” በሚል ስም ተጠቅሷል። ከበርካታ አመታት በኋላ በባግዳድ ውስጥ እየኖረ ሳለ ነበር። በወቅቱ አሳዳሪው የነበረው ሰው አምባር ሲል ሌላ ስም ያወጣለት። ከአመታት ቆይታ በኋላም በህንዷ ቢ-ጃፑር መንግስት፣ በአረብኛ ንጉስ የሚል ትርጉም ያለውን “ማሊክ” የተሰኘውን የክብር የማእረግ መጠሪያ ስያሜ ሰጠው። እኒህም በአንድ ላይ ሲሆኑ አሁን ላይ አለም የሚያውቀውን “ማሊክ አምባር’’ የሚለውን ስያሜ ሰጥተውታል።
በወቅቱ በምስራቅ አፍሪካ በነበረው የባሪያ ንግድ ተገዶ የተቀላቀለው በወጣትነቱ እድሜ ነበር። ከዚያም ወደ መካከለኛው ምስራቅና ወደ ሰፊው የሕንድ ውቅያኖስ የመሳሰሉ የአለም ክፍሎች ይላካሉ። እነዚህ አፍሪካውያን በተለያየ ደረጃዎች ያገለግሉ የነበሩ ሲሆን። በጊዜው ሰብአዊነታቸው ባይከበርም ሙሉ ለሙሉ ክብራቸውን አያጡም ነበር። የኢትዮጵያ ሴቶች በውበታቸው፣ ወንዶቹ ደግሞ በብልሀታቸውና በጀግንነታቸው በአረብና በፋርስ ጻሓፍት ዘንድ የሚታወቁበት አገላለጽ ነው። አንዳንዶችም “በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የደህንነት ዋስትና” ተደርገው ይታዩ እንደነበር የጻፉ አሉ።
አምባር የተወለደበት ስፍራ በጊዜው ጦርነት ይፈራረቅበት የነበረ ስፍራ ነው። ይህም በኋላ ታሪኩ ሕንድ ውስጥ ለገጠመው አካባቢ ሃያልነትን ለመጎናጸፍ አብቅቶታል።ገና ታዳጊ ልጅ የነበረው ቻፑ ወይም አምባር ከሐረርጌ እስከ ዘይላ ጠረፍ ለመድረስም ከምድር ሞቃታማ ገላጣ ስፍራዎች በአንዱ ላይ ከሁለት መቶ ማይሎች በላይ ርቀትን በእግሩ አቋርጦ መጓዝ ነበረበት።
በመቀጠልም በአንድ የአረብ ነጋዴ ሞቻ በሚባል ስፍራ ተገዛ። በወቅቱ አምባር የራሱ የሆነ የተለየ ቋንቋ፣ ባህሎችና ልማዶች ባሉበት የአረብ ሀገር ውስጥ ስለሚገኝ፣ በአዲሱ አካባቢ የሚያጋጣሙትን የተለያዩ ተግዳሮቶች መጋፈጥ ስለሚኖርበት ቋንቋውን አስተውሎ ለማጥናት ወይም ለመማር መሞከሩ እንደማይቀር ይገመታል።
አምባር - ከሞቻ ተነስቶ ወደ ሰሜን እስከ አረቢያን ጠረፍ ድረስ ተወስዶ ወደ መካ ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን፣ሱዳናውያን እና አፍሪካውያን መግቢያ የሆነችውን ወደብ አልፎ እንደተጓዘ ይገመታል።
በዚያው እያለ አምባር የእስልምና ሃይማኖትን ተቀብሏል። አምባር በባግዳድ ሲደርስ - በኦቶማን አገዛዝ ስር ወድቃም ባግዳድ የሙስሊሙ አለም አይነተኛ መናኸሪያ ከተማ እንደሆነች ነበር። ሌሎቹ ከተሞች በዋነኛነት ካይሮ፣ ኢስታንቡል እና ዴልሂ በሕዝብ ብዛት፣ በምሁራዊና በስነ ጥበባዊ እድገት ማእከልነት ቢበልጧትም፡ የጥንታዊ ግሪክ፡ የግብጽ፡ የፋርስ እንዲሁም የሕንድ እና የቻይና ሳይንሳዊ እውቀቶችን የሚያሰባስቡ ምሁራን፡ ተርጓሚዎችና የመጽሓፍት ቅጂ ገልባጮች በአንድ ላይ የሚተሙበት የምትኮራበት ቤተ - መጽሓፍቷ
“ባይት አል ሂክማ” ሲተረጎምም “የጥበብ ቤት” የተባለው ስለሚገኝባት ባግዳድ ከአለም ታላላቅ ከተሞች ዝርዝር ውስጥ የነበራትን ደረጃ እንዳስጠበቀች ዘልቃ ነበር።
የፋርስ ባህል፣ የስነ ጥበብና የኪነ ህንጻ ንድፍ ቅይጥነት መላውን አለም የሚያስደምም ነበር። የከተማዋ ውስብስብ ገጽታ ምልክቶች፣ የጂኦሜትሪያዊና የአበባ ቅይጥ ቅርጾች፡ የሚያምሩ መግቢያዎችን የደጋን ቅርጽ በሮችና መስኮቶች፣ ጉልላቶች፡ በቁም ጽሁፍ ሐረጋት አሸብርቀው የተቀረጹ ጽሑፎች እንዲሁም ለስላሳ ገጽታዎች እና መስመሮች —- የባግዳድ፣ የአረብና የፋርስ ቅይጥ ንድሮች የፈጠሯቸው እንደሆኑ ያስታውቃሉ። እንዲሁ ያሉት ስነ ጥበባዊና ስነ ሕንጻዊ ንድፎች የአምባር የራሱም የስነ ውበታዊ እይታ አካል ለመሆን በመቻላቸው ይዟቸው ወደ “ዴካን” እንዳመጣቸው በኋላ ላይ በገነባቸው ቤተ መንግስቶች እና የመቃብር ሀውልቶች ላይ ሊታይ ችሏል።
በመጨረሻ ላይ በ1550ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የባግዳድ ከተማ መግቢያ በፎች ላይ ደረሰ። የከተማዋን ግዝፈት የተራቀቁ ኪነ ህንጻዎቿን ተመልክቷል። በከተማዋ ይኖሩ የነበሩት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መሃከል ሌሎች አቢሲኒያውያን ይገኛሉ። ባርነት በተስፋፋበት በዚያ ጊዜ አብዛኞቹ ነጻ ሰዎች ነበሩ። አምባር ባግዳድ ከመድረሱ ከረጅም ጊዜ በፊት የኢትዮጵያውያን ልጅ የነበረ “አል-ጃሂዝ” ተብሎ የሚጠራ የዘመኑ ትውልድ ግንባር ቀደም ጠቢብ ነበር። ይህ ኢትዮጵያዊ ጠቢብ ከተዋቂ መጽሐፍቶች መሃል አንዱ በሆነውና “የጥቁሮች ኩራት” ተብሎ በሚጠራው ውስጥ ኢትዮጵያውያንን “እሳት የላሱ አንደበተ ርቱእዎች” ሲል ገልጿቸዋል።
በመቀጠልም አምባር በባግዳድ ውስጥ እያለ በሌላ ነጋዴ ተገዝቶ ለባግዳድ ሰው የነበረ ተሽጧል። አዲሱ ገዥውም እንደ ገዛ ልጁ በታላቅ ርህራሄና ደግነት ተንከባክቦ ይዞት እንደነበር ተጽፏል። በዚያም ማንበብና መጻፍን እንዲሁም መሰረታዊ የገንዘብ አስተዳደርንም ተምሯል። በርካታ በእውቀት የመገንቢያ አመታትን በከተማዋ ማሳለፉም፡ አምባርን ባህሉን ለመገንዘብ ነገሮችን ለመረዳት ችሎታውን ለማዳበርና ሕይወትን ለማጣጣም አስችሎታል። የአረብኛና በመጠኑ የፐርሽያ ፋርሲ ቋንቋንም ተምሯል።
ትርፍ ለማግኘት አልያም ለአዳዲስ እድሎች - አለቃው አምባርን ወደ ሕንድ ሊወስደው ወሰነ። በ1563 አ.ም ገደማ ባግዳድን ለቅቆ በፐርሽያ አድርገው ተጉዘዋል። ባግዳድን በለቀቁ በ2 ሳምታቸውም ወደ ምእራብ ህንድ ጠረፍ መድረስ እንደቻሉ ይታመናል።
የማሊክ አምባር የባህር ጉዞ ስኬት ብዙዎችን ያስገርማል። ምክንያቱም በዚያን ጊዜ እንደዚህ አይነት ረጃጅም የባህር ላይ ጉዞዎችን ማካሄድ አደገኛና ፈታኝ ነበር።