በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በንግድ ማጭበርበር እና ኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣ የነበረ ከ107 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል
#####################
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም)
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እንደቀጠለ ነው።
በግምገማ መድረኩ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት በጉምሩክ ኮሚሽን በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸው ተመላክቷል።
በተለይም ኮንትሮባንድና ንግድ ማጭበርበርን በመከላከል እና መቆጣጠር ዙሪያ ስኬቶች ተመዝገበዋል::
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በግምገማው ወቅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ስድስት ወራት 7.38 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የገቢ ኮንትሮባንድ እና 1.57 ቢሊዮን ብር የወጭ ኮንትሮባንድ በድምሩ 8.95 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስረድተዋል።
በኮንትሮባንድ ዝውውር የተጠረጠሩ 708 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው እየተደረገ ነውም ብለዋል።
በተጨማሪም በንግድ ማጭበርበር ማለትም በኢንተለጀንስ ስራዎች ፣ በድንገተኛ ፍተሻ፣ በቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ቁጥጥር፣ በድህረ ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ፣ በመደበኛ እቃ ፍተሻ እና ሰነድ ምርመራ 98.29 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቁመዋል።
በጠቅላላ በ2017 የበጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በንግድ ማጭበርበር እና በኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣው የነበረ 107.24 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን ገልጸው፤ ኮንትሮባንድና ንግድ ማጭበርበርን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የኮሚሽኑ ዓቅም እየጎለበተ መሆኑንም ኮሚሸነር ደበሌ አስገንዝበዋል።
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission