መምህሩ የ2 ሚሊየን ቼካቸውን ተረከቡ
መምህር አዳነ ደሴ ይባላሉ የመምህርነቱን ሙያ በቅርብ ነው የተቀላቀሉት ፡፡ መምህር አዳነ የቀብሪደሀር ነዋሪ ሲሆኑ ከልጅነታቸው ጀምሮ ሁለገብ የሚባል ዓይነት ሰው ናቸው ያገኙትን ይሰራሉ ሥራ አይመርጡም ለዚህም ይመስላል ከመምህርነት ሙያቸው በተጓዳኝ አልፎ አልፎ የዲጂታል ሎተሪ የመሞከር ልማድ አላቸው ፡፡ መቸም “ ደግሞ ደጋግሞ የሞከረ ከዕድል ጋር ተማከረ “ እንዲሉ በ28ኛው አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛው ዕጣ የ2 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆነዋል ፡፤ በደረሳቸውም ገንዘብ መኖርያ ቤት እንደሚገዙበት ገልጸውልናል ፡፡