‹‹ሁሌም ኦሊምፒያን እሆናለሁ፣ የአትሌቶችና የአትሌት ተወካዮች ተሟጋችም እሆናለሁ››
አዲሷ የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ኪርስቲ ኮቨንትሪ፣ ባለፈው ሳምንት የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) በናሚቢያ ባዘጋጀው የአትሌቶች ስብሰባ ላይ የተናገሩት፡፡ በኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴትና አፍሪካዊት ሆነው በቅርቡ በመጋቢት የተመረጡት የቀድሞ ውጤታማ አትሌት የነበሩት ዚምባቡዌያዊቷ ኮቨንትሪ፣ በንግግራቸው ‹‹እኔ ኩሩ አፍሪካዊ ኦሊምፒያን ነኝ። የአፍሪካ አትሌቶችን ጉዞ፣ ተግዳሮቶችና ድሎች ከራሴ ጉዞ በመነሳት ተረድቻለሁ፤›› ብለዋል፡፡ በስፖርት ሕይወታቸውም ይሁን በአፍሪካና በአይኦሲ የአትሌት ተወካይ ሆነው፣ ወይም በአገራቸውና በኦሊምፒክ እንቅስቃሴ በተለያዩ ኃላፊነታቸው ያሳኳቸው ተግባሮች በቡድን በመሥራት እንደሆነ ያመለከቱት የቀድሞ የዚምባቡዌ የስፖርት ሚኒስትር ኮቨንትሪ፣ በአዲሱ የሥራ ድርሻቸውም ተመሳሳይ የአንድነትና የቡድን ሥራ አካሄድ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን አስምረውበታል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140140/