" ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች ! " - ሰልፈኞች
በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል።
ሰልፉ የተዘጋጀው በትግራይ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት አማካኝነት ነው።
ምክር ቤቱ ዛሬ " ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ተገኝተው ነበር።
ሰልፈኞቹ ፦
- ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይመለሱ !
- ህገ-መንግስት ይከበር !
- ፍትህ ለእህቶቻችን ነፃነት ለሁሉ !
- ሂጃብ መልበስ ሃይማኖታዊ መብትና ግዴታ ነው !
- ሂጃቤ መልኬ ነው !
- የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይከበር !
- ሰላም እና ፍትህ ለትግራይ !
- መብታችን ይጠበቅልን !
- ከተበዳዮች ጎን እንቁም !
- ፍትህን እንጠይቃለን !
- ከሂጃባችን ጋር ታግለናል፤ ሂጃባችን ለብሰን እንማራለን !
- ሂጃባችን ምርጫችን እና መብታችን ነው !
... የሚሉና እና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።
በመቐለ ሮማናት አደባባይ ለተሰባሰቡት ሰልፈኞች መልእክት ያስተላለፉት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዜዳንት ሸኽ አደም ዓብደልቃድር ፥ " ትግራይ የሃይማኖቶች የመቻቻል የነፃነት ተምሳሌት ነች፤ ይሁን እንጂ ይህንኑ ስልጡንነት ወደ ኋላ በሚመልስ መልኩ ልጆቻችን ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ ከዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እንዲቀሩ ተደርገዋል " ብለዋል።
ችግሩ ሳይባባስ እንዲፈታ ለሁለት ወራት በላይ የተለያየ ጥረቱ መደረጉ ያወሱት ፕሬዜዳንቱ " ትምህርት ቤቶቹ የክልሉ እና የአገሪቱን ህግ በማክበር የሂጃብ ክልከላውን በአጭር ጊዜ ማንሳት አለባቸው ፤ ጥያቄያችን በአጭር ጊዜ ካልተመለሰ ግን ጥያቄያችን እስከ መጨረሻው ድረስ በሰላማዊ መንገድ እንቀጥላለን " ሲሉ ተናግረዋል።
" የክልሉ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ክርስትያን ወንድሞቻችን ችግሩ ክጅምሩ እንዲፈታ ብዙ ጥረት አድርጋችሃል " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ችግሩ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስም የጀመራችሁት ትግል ተጠናክሮ ይቀጥል " በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።
ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም የሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ጉዳዩ ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት እንዳያመራ የሚያስገነዝብ ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ከትምህርት ገበታቸው የተስተጓጎሉ ሴት ተማሪዎች መካካሻ ትምህርት እንዲያገኙ ያለሙ የሚያወሱ 12 ጥሪዎች እና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ መልእክቶች ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር በማቅረብ እና በማስተላለፍ ከረፋዱ 4:30 ሰልፉ ተጠናቋል።
ሰላማዊ ሰልፉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የከተማዋ የፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥበቃ ያደረጉ ሲሆን በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
በሌላ በኩል ፥ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ ክልከላ አድርገዋል የተባሉት በአክሱም ከተማ የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የጋራ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥተዋል።
ት/ቤቶቹ ምን አሉ ?
" 1. የሴት ሙስሊም ተማሪዎች የሂጃብ አጠቃቀም አስመልክቶ በትግራይ ያለው ህግ እና አተገባበሩ ምን ይመስላል ?
ትምህር ቤቶቻችን የትግራይ ትምህርት ቢሮ በ1995 ዓ.ም ያወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ነው እየተጠቀሙ ያሉት ። አዲስ ፖሊሲ ወይም መመሪያ እና ደንብ በትምህርት ሚንስቴር ከወጣ ደግሞ ከትምህርት ቢሮ ጋር ተነጋግሮ ይህንን መመሪያ እና ደንብ ተጠቀሙ ብሎ ይልክልናል ። እኛም ተግባራዊ እናደርጋለን። ይህን ባለልሆነበት ' እህያውን ፈርቶ ዳውላውን ' የሆነ ጥያቄ እና ጫና ግን ግራ የሚያጋባ ነው።
በ1995 ዓ.ም የወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ደግሞ ተማሪዎች መምህራን ወላጆች ተወያይተው ያፀዱቁት ላለፉት 22 ዓመታት እየተጠቀሙት ያለ መመሪያ ደንብ ነው።
በ1995 ዓ.ም የወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ደንብ ደግሞ እንዲታይ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ከወላጅ ተማሪዎች ጥያቄ ተነስቶ ነበር ። የተነሳው ጥያቄ መሰረት በማድረግ በመመሪያ እና ደንቡ ውይይት ተካሂዶ ታህሳስ 6/2017 ዓ.ም በአንድ ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ፀድቀዋል።
በውይይት እና ድምፅ አሰጣጡ የሙስሊም እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ተሳትፈውበት በሙሉ መግባባት መተማመን የተደረሰበት ነው። ታድያ ከአሁን በፊት ታይቶ የማይታወቅ የሂጃብ ክልከላ ጥያቄ ከየት ? እንዴት መጣ ? ትምህርት ቤቶታቻችን ግራ ገብቶዋቸዋል።
2. የትምህርት ቤት ዩኒፎርም አለባበስ ደንብ እና ስነ-ሰርዓት ምን ይመስላል ?
በ1995 ዓ.ም በፀደቀው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መምሪያ እና ደንብ መሰረት ትምህርት ቤቶቻችን የሚከተለውን የአለባበስ ስርዓት እንዲተገብሩ ያስገድዳል።
የቤተክርስትያን ካህናት እና ዲያቆናት ተማሪዎች ሻሽ መጠምጠምያ ፣ ነጠላ ማድረግ አይፈቀድም። ወንድ ተማሪዎች ባንከር ፣ ፍሪዝ የፀጉር አቆራረጥ አይፈቀድም።
ሴት ተማሪዎችም ነጠላ ፣ መሃረብ ፣ ሻሽ መጠምጠምያ ፣ ጥቁር የሃዘን ሻርፕ ፣ ሂል ጫማ ፣ ሱሪ ፣ የማንኛውም ሃይማኖት አለባበስ የሚያንፀባርቅ ልብስ እንዲለብሱ አይፈቀድም። ይህ የሆነበት ደግሞ በመካከላቸው የሃብት የሃይማኖት ልዩነት ፈጥሮ የመማር የማስተማር ሂደቱ እንዳይታወክ ለማድረግ ያለመ ነው።
ይህ ህግ ደግሞ ክርስትያን ፣ ሙስሊም መምህር የተማሪ ወላጅ ተወያይተው ያፀደቁት እና የሚተዳሩበት ነው። አሁን ታድያ ምን አዲስ ነገር ተፈጥሮ ነው በትምህርት ቤቶቻችን ላይ የሚዘመተው ?
3. ስለ ዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች መሬት ላይ ያለው መረጃ ምንድነው ?
በአክሱም አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉ። በአራቱ ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ ለ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚቀርቡት ተማሪዎች 1044 ናቸው።
ከነዚህ 1044 ተማሪዎች 17 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ 17 ሴት ተማሪዎች ለ22 ዓመታት በቆየው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ እና ደንብ በመቀበል 7 ሴት ተማሪዎች ፈተናው ለመውሰድ ፎርም ሞልተዋል።
10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ከአክሱም ከተማ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በተዘረጋ የውጭ ተፅእኖ ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸው ፎርም አልሞሉም። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ' 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እንዲስተጓጎሉ ተደረገ ' እየተባለ ነው የሚወራው። 142 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻችን የሌሉ የፈጠራ ድርሰቶች ናቸው።
የተቀሩት 10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ቢሆኑ ፎርም መልተው ለመፈተን ፍላጎት አላቸው ፤ ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፣ ከመቐለ ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በየቀኑ እየተደወለ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ የቆየውን አብሮነት እና መቻቻል የሚጎዳ ለህዝብ እና አገር የማይጠቅም መወገዝ ያለበት ተግባር ነው። "
... ሲሉ ትምህርት ቤቶቹ በጥምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በላኩት የፅሁፍ ምላሽ ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaMekelle
#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ
@tikvahethiopia