አርሴማን ጥሩልኝ 🥺
ክፍል ፩
ልክ የዛሬ 15 አመት ነበረ ይህ ነገር የሆነው ብዙ ጊዜ እግዚአብሔርን ለምን ልጅ አልሰጠኸኝም ብለው ሲያማርሩ ብሎም ሆስፒታል ሄደው ሲፈላሰፉ አስተውላለሁ እኔና ባለቤቴ ግን አንድም ቀን እንኳን አማረን አናውቅም ልክ መስከረም 28 ቀን በተኛንበት እኔም ባሌም ተመሳሳይ ህልም አየን በጣም የምታምር እንደ ፀሃይ የምታበራዋ ባለዘንባባዋ እናቴ የሚያምር ወንድ ልጅ ይዛ ወደ ቤታችን ስትገባ ባሌ ያየውን ነገረኝ እኔም ስነግረው አላመነም ነበረ ወዲያው ተነሳንና ተጣጥበን የቅድስት አርሴማ እረፍቷን ልናከብር ወደ ለቡ አርሴማ አመራንና እኔም በሆዴ ለአርሴማ ልጅ ከወለድኩኝ ታቦትሽ የሚከብርበትን ጥላ አመጣለሁ ብዬ ባሌም ተስሎ ወደ ቤታችን ቄጤማና የአርሴማን ስዕለ አድህኖ ገዝተን ተመለስን ምግብ እየበላን አስር ጊዜ ሊያስታውከኝ ሲሞክር ምንም ስለማናውቅ ታምሜ መስሎን ወደ ሆስፒታል ጉዞ ጀመርን ወዲያው እንደደረስን ምርመራ ተደርጎልኝ የ2 ወር ነፍሰጡር ነሽ ተባልኩኝ ባሌ ተንሰቀሰቀ እና ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም በደስታ ዘለልን ወዲያውን ለቡ አርሴማ ሄድን የሚገርመው ባሌም ተስሎ የነበረው ጥላ ነበር ከዛ ገዝተን የማታ ጉባኤ ላይ ምስክርነት ሰጠን ዛሬ የ9 ወር ነፍሰጡር ነኝ በቅርቡ የልጅ እናት ልሆን ነው ከኔ በላይ የባሌ ደስታ አስደስቶኛል ከዛ ቀጠሮ ስላለን ወደ ሆስፒታል አመራን ምርመራ ተደረገልኝ ወጤቱ አስደንጋጭ ነበረ ልጁ በህይወት እንደሌለና ኦፕራስዮን ተደርጌ ልጁ መውጣት እንዳለበት ተነገረኝ ባሌ ደስ ብሎት ሳይጨርስ ብዬ አለቀስኩ እሱ ግን የእኔ ደህንነት ነበር ያሳሰበው ቅድስት አርሴማ አለች አይዞሽ ምንም አትሆኝም ደግሞ ሌላ ልጅ ትሰጠናለች አለኝ መንታ እንባዎች በአይኑ እየፈሰሰ ወዲያው ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ
ይቀጥላል
✍ ብርሃኑ ባውቄ