የእባብ አመት ፥ ቻይናውያን እያከበሩት የሚገኘው አዲስ አመት
---------
የቻይና የሉናር አዲስ ዓመት እየተከበረ ነው። በዓሉ በብዙ የእስያ አገሮች እና በዓለም ዙሪያ ባሉ ዜጎቻቸው የሚከበር ጥልቅ በዓል ነው ፡፡
የቻይና ዘመን መለወጫ በዓል የፀደይ ፌስቲቫል ተብሎም የሚጠራ ሲሆን በዚህ ዓመት በቻይናውያን የቀን መቁጠሪያ መሰረት በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዓሉም ለቀጣይ ሁለት ሳምንታት የሚቆይ ነው፡፡
የቻይናውያን አዲስ አመት በ12 አመት ውስጥ የሚሽከረከርና በቻይና ኮከብ ቆጠራ ስርዓት ውስጥ ካለው እንስሳ ጋር የሚዛመድ ሲሆን ከአምስት ንጥረ ነገሮች ማለትም ከብረት፣ እንጨት፣ውሃ፣እሳት እና ከመሬት ጋር የተጣመረ ነው፡፡ የዘንድሮ አዲስ ዓመትም የእንጨት እባብ ዓመት ተብሎ እየተከበረ ይገኛል፡፡
የዘመን መለወጫ በዓሉ አመጣጥ በቻይና ቢሆንም እንደ ማሌዥያ፣ ፊሊፒንስ እና ሲንጋፖር ባሉ ሀገራት ያሉ የቻይና ማህበረሰቦች በተመሳሳይ ስም እና ተመሳሳይ ሁነቶች ያከብሩታል ፡፡ እንደ ቬትናም እና ኮሪያ ያሉ ሀገራትም የሉናር አዲስ ዓመትን ስሙን በመቀየር ያከብራሉ፡፡
ቻይናውያን አዲስ ዓመት ከመግባቱ ቀደም ብለው ባሉ ቀናት ያለፈው ዓመት መጥፎ ዕድል ለማባረር በሚል ቤቶቻቸውን በማጽዳት ያሳልፋሉ።
ይህ ጽዳት ለቀጣዩ አመት መልካም እድል እንደሚያመጣ የሚታመን ሲሆን በጌጣጌጦች ፣ መብራቶች፣ በተቆራረጡ ወረቀቶች እና በደማቅ ቀይ ቀለም ቤቶቻቸውን በማስዋብ መልካም እድልን ለማምጣት ይሞክራሩሉ፡፡
በአዲሱ ዓመት ዋዜማም ከቤተሰብ አባላት ጋር እራት በመብላት ያሳልፋሉ፡፡
የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ሲገባ አንግ ፓኦ ወይም ሆንግ ባኦ የሚባል ስርዓት የሚከናወን ሲሆን ይህም የቤተሰብ አባላት እና ጓደቾች በአንድ ተሰብስበው የተለያዩ ስጦታዎችን የሚሰጣጡበት ነው ፡፡
የቻይና ተወላጅ የሆነው ኢቮን ጎህ እንደሚለው ፤ አንዳንዶች በመጀመሪያዎቹ ቀናት ቤታቸውን ከመጥረግ ፣ ፀጉራቸውን እና ጥፍሮቻቸውን ከመቁረጥ ይቆጠባሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉትም በአዲስ ዓመት የተገኘውን መልካም እድል እንዳያጡ በመፍራት ነው ሲል ይገጻል፡፡
መልካም እድልን የሚጋብዙ እና እርኩሳን መናፍስትን ከቤት እና ከስራ ቦታ የሚያርቁ ባህላዊ የአንበሳ ጭፈራዎችን ማከናወንም የበዓሉ አንዱ አካል ናቸው።
በተለምዶ ያገቡ ሴቶች የቻይና አዲስ አመት የመጀመሪያ ቀንን ከአማቶቻቸው ጋር እንዲያሳልፉ የሚደረግ ሲሆን በሁለተኛው ቀን ደግሞ ሴት ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲጎበኙ ይደረጋል።
ሶስተኛው ቀን ፀጥ ያለ እንዲሆን እና በእረፍት እንዲያልፍ ከተደረገ በኋላ አራተኛው እና አምስተኛው ቀን ግን ለሀብት አምላክ የተሰጡ መሆናቸው ይነገራል ፡፡ ስድስተኛው ቀን ላይም ሰዎች ያረጁ ወይም ያልተፈለጉ ዕቃዎችን ጥለው ወደ ሥራ እንዲገቡ ሲደረግ በሰባተኛው ቀን የቻይና እናት አምላክ የሆነችው ኑዋ ሰዎችን እንደፈጠረች ይታመናል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።