ከ6 ዓመት በኋላ በቁጥጥር ስር ዋለ!
“ካንተ ጋር በፍቅር ግንኙነት መቀጠል አልፈልግም” ብላኛለች የግድያ ወንጀል የፈፀመና በሌለበት የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጣት የተላለፈበት ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
***
ተከሳሹ ጌታቸው አለምፀሃይ ይባላል፡፡ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ጥር 2 ቀን 2011 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰአት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሳባ ህንፃ ላይ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ተከሳሹ በህንፃው 6ኛ ፎቅ ወደሚገኘው የክፍለ ከተማው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ቢሮ ውስጥ በመግባት የፍቅር ጓደኛዬ ናት በሚላት መአዛ ካሳ በተባለች ግለሰብ ላይ የግድያ ወንጀሉን ፈፅሟል፡፡
“አልፈልግህም ብላኛለች” በሚል ምክንያት በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ግለሰቧን በቢሮዋ ውስጥ እያሯሯጠ የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በስለት በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሹ፤ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ የምርመራ መዝገብ ተደራጅቶበታል፡፡
ጌታቸው አለምፀሃይ በፖሊስ የተጠርጣሪዎች ማረፊያ ቤት በነበረበት ወቅት በህመም ምክንያት ወደ ህክምና ተቋም ለመሄድ የካቲት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ጥያቄ አቅርቦ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ከህክምና ቦታ እንደተሰወረ እና በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በሌለበት በፍርድ ቤት ሲታይ እንደቆየ የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተደራጅቶ የቀረበለትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በነሀሴ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ውሎው ጌታቸው አለምፀሀይ በሌለበት በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እና ከህዝባዊ መብቶቹ ለዘወትር እንዲሻር ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
የፍርድ ቤቱን የቅጣት ውሳኔ ተፈፃሚ ለማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል ፍርደኛውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቀንና ለሊት ያልተቋረጠ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ/ም ሆለታ ከተማ ውስጥ ከተደበቀበት ስፍራ ወንጀሉ ከተፈፀመ ከ6 ዓመት በኋላ በድጋሚ ሊያዝ ችሏል፡፡
ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ለጊዜው ቢሰወርም ከህግ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችል ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎችም የወንጀል ጉዳዮች መኖራቸውን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ከህግ ለማምለጥ የሚደረጉ ሙከራዎች ከፖሊስ ክትትል ውጪ እንደማይሆኑ በመገንዘብ ህብረተሰቡ ለፖሊስ እያደረገ የሚገኘውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችም ከመሰል ድርጊት እንዲታቀቡ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
@Ewun_Mereja1