ቼልሲ የውድድር ዓመቱን በምዕራብ ለንደን ደርቢ ይጀምራል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ፉልሃምን ይገጥማል፡፡
በክረምቱ አዳዲስ አሰልጣኞችን የሾሙት ሁለቱ ክለቦች የውድድር ዓመቱን በድል ለመጀመር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ቼልሲ ከሪያል ማድሪድ የተሰናበተውን አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እንዲሁም ፉልሃም በተመሳሳይ ሪያል ማድሪድን በጊዜያዊነት ሲያሰለጥን የነበረውን አልቫሮ አርቤሎዋን በዚህ ክረምት መሾማቸው ይታወሳል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በክራቨን ኮቴጅ የሚደረገውን የምዕራብ ለንደን ደርቢ የ36 ዓመቱ ጆን ብሩክስ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡
ትናንት ምሽት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ 2 አቻ መለያየቱ ይታወቃል፡፡
የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ
ፌስቡክ https://web.facebook.com/fanasport
ቴሌግራም ?? https://t.me/FMCSport