FMC Sport ፋና ስፖርት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel.
@Fanatelevision
@afanoromofana
@tigrignafana
For more updates please visit
https://fanamc.com/amharic/

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ለካፍ ጥያቄ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበትን ሰነድ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስገብታለች፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢፌዴሪ መንግሥት ጋር በጋራ አስፈላጊ ሰነዶችን ያካተተ ዶክመንት ለካፍ ማስገባቱን አስታውቋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ትልቁን አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለ4ኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድና በአፍሪካ እግር ኳስ ያላትን ጉልህ ታሪክ ዳግም ለማደስ ዝግጁነቷን አረጋግጣለች።


አስፈሪው አርሰናል

ከደቂቃዎች በኋላ በኤክስትራ ታይም ስፖርት ቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን

#ስፖርት_ፖድካስት
#ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #fanapodcast #fanadigitalmedia #fanamediacorporation #PoodkaastiiFaanaa #fanadigitalmedia فانا_عربي_بودكاست


ቼልሲ የውድድር ዓመቱን በምዕራብ ለንደን ደርቢ ይጀምራል

‎አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ፉልሃምን ይገጥማል፡፡

በክረምቱ አዳዲስ አሰልጣኞችን የሾሙት ሁለቱ ክለቦች የውድድር ዓመቱን በድል ለመጀመር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ቼልሲ ከሪያል ማድሪድ የተሰናበተውን አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እንዲሁም ፉልሃም በተመሳሳይ ሪያል ማድሪድን በጊዜያዊነት ሲያሰለጥን የነበረውን አልቫሮ አርቤሎዋን በዚህ ክረምት መሾማቸው ይታወሳል፡፡

ምሽት 4 ሰዓት ላይ በክራቨን ኮቴጅ የሚደረገውን የምዕራብ ለንደን ደርቢ የ36 ዓመቱ ጆን ብሩክስ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡

ትናንት ምሽት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ 2 አቻ መለያየቱ ይታወቃል፡፡

የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ

ፌስቡክ https://web.facebook.com/fanasport
ቴሌግራም ?? https://t.me/FMCSport


ማንቼስተር ሲቲ በርንማውዝን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በርንማውዝን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በአዲስ አሰልጣኝ የተመራው ማንቼስተር ሲቲ በርንማውዝን በማሸነፍ በሊጉ መርሐ ግብር የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል፡፡

ማርከስ ታቨርኔር በርንማውዝን በ26ኛው ደቂቃ ቀዳሚ ያደረገ ቢሆንም ማርክ ጉሂ በ85 እና ገቫረዲዮል በ92 ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሲቲ ጨዋታውን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

በሌላ በኩል የአምናው የአውሮፓ ሊግ አሸናፊ አስቶን ቪላ በብራይተን የ4 ለ 0 ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡


ማንቼስተር ዩናይትድ በሀል ሲቲ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ የውድድር ዓመቱን የመክፈቻ ጨዋታ በሀል ሲቲ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

የሀል ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኖቤል ሜንዲ እና ሴሚ አጃዪ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥረዋል፡፡

ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ፣ ኢፕስዊች ታውን ከሰንደርላንድ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ ቀን 11 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።

በዕለቱ የመጨረሻ መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐር ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ይገናኛሉ።


ሀል ሲቲ ከማንቸስተር ዩናይትድ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ቀጥለው ይደረጋሉ።

ሊጉ ትናንት ምሽት አርሰናል ከኮቨንትሪ ሲቲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ሲጀመር፤ መድፈኞቹ 3 ለ ዐ አሸንፈዋል።

ዛሬ ቀን 8 ሰዓት ከ30 ማንቸስተር ከሜዳው ውጭ ተጉዞ አዲስ አዳጊውን ሀል ሲቲ በመግጠም የውድድር ዓመቱን ይጀምራል።

ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ፣ ኢፕስዊች ታውን ከሰንደርላንድ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ ቀን 11 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።

በዕለቱ የመጨረሻ መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐር ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ይገናኛሉ።

የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ

ፌስቡክ https://web.facebook.com/fanasport
ቴሌግራም ?? https://t.me/FMCSport


አርሰናል ኮቨንትሪ ሲቲን 3 ለ ዐ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል አዲስ አዳጊውን ኮቨንትሪ ሲቲ 3 ለ ዐ በማሸነፍ የ2026/27 የውድድር ዓመትን በድል ጀምሯል።

የመድፈኞቹን ግቦች ካይ ሀቨርት፣ ሳካ እና ኦዴጋርድ ከመረብ አሳርፈዋል።

የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ

ፌስቡክ https://web.facebook.com/fanasport
ቴሌግራም ?? https://t.me/FMCSport


አርሰናል ከኮቨንትሪ ሲቲ - ቋሚ አሰላለፍ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2026/27 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከደቂቃዎች በኋላ በይፋ ይጀመራል፡፡

የአምናው የሊጉ ባለክብር አርሰናል በፍራንክ ላምፓርድ የሚመራውን የሻምፒዮንሺፑ ሻምፒዮን ኮቨንትሪ ሲቲ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኤሚሬትስ ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ክለቦች ቋሚ አሰላለፋቸውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ የመድፈኞቹ የክረምቱ ፈራሚ ክሪስቶስ ሶሊስ በቋሚነት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ዴቪድ ራያ፣ ቤን ዋይት፣ ሞስኬራ፣ ጋብሬል ማጋሌሽ፣ ካላፊዮሪ፣ ዴክለን ራይስ፣ ሊውስ ስኬሊ፣ ኦዴጋርድ፣ ሳካ፣ ሶሊስ እና ካይ ሀቨርት በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ምርጥ 11 ውስጥ ተካትተዋል፡፡

ራሽወርዝ፣ ቫን ኤዊክ፣ ቶማስ፣ አሜንዳ፣ ዶሲልቫ፣ ግሪምስ፣ ኦኒዬካ፣ ቻውና፣ ቶማስ አሳንቴ፣ ሲምስ አርሰናልን በሚገጥመው የኮቨንትሪ ሲቲ ቋሚ አሰላለፍ የተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ

ፌስቡክ https://web.facebook.com/fanasport
ቴሌግራም ?? https://t.me/FMCSport


ከሊጎች ሁሉ የሚልቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለማችን ታላቁ፤ ተወዳጁ እና በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዘመን ዛሬ በይፋ ጅማሮውን ያደርጋል።

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በጉጉት የሚጠብቁት ይህ ሊግ ዛሬ የደረሰበት የኃያልነት እና የተወዳጅነት ማማ ላይ ከመድረሱ በፊት በርካታ ታሪካዊ ምዕራፎችን አሳልፏል።

በፈረንጆቹ እስከ 1992 ድረስ የእንግሊዝ እግር ኳስ በዋናነት በ"እንግሊዝ እግር ኳስ ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን" ስር ነበር የሚተዳደረው።

ሆኖም በወቅቱ የነበሩ ታላላቅ ክለቦች ከቴሌቪዥን ስርጭት እና ከስፖንሰርሺፕ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ራሱን የቻለ ሊግ ለመመስረት በመወሰናቸው 22 ክለቦችን በማሳተፍ በፈረንጆቹ 1992 በይፋ ተመሰረተ፡፡

ከፈረንጆቹ 1992 ጀምሮ ማንቼስተር ዩናይትድ 13 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት በሊጉ ታሪክ ቀዳሚው ክለብ ነው።

በዚህ የሊግ ውድድር አርሰናል ሙሉ የውድድር ዘመኑን ያለ ምንም ሽንፈት አጠናቅቆ የዋንጫ ባለቤት በመሆን ደማቅ ታሪክ ጽፎበታል።

https://web.facebook.com/share/p/1DV7tHdpp8/


አርሰናልን የተቀላቀልኩት ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ነው - ኤዝሪ ኮንሳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል እንግሊዛዊውን ተከላካይ ኤዝሪ ኮንሳ ከአስቶን ቪላ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

የ28 ዓመቱ ተጫዋች ለመድፈኞቹ ፊርማውን ካኖረ በኋላ በሰጠው አስተያየት፥ እዚህ የተገኘሁት ለአሸናፊነት ነው፤ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለሁ ሲል ተደምጧል፡፡

በዓለማችን ካሉ ምርጥ ክለቦች አንዱ የሆነውን አርሰናል መቀላቀል ለእኔ ትልቅ ክብር ነው ያለው ተጫዋቹ፤ የክለቡን ስኬት ለማስቀጠል ያለኝን ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ሲል ተደምጧል፡፡

ኮንሳ በሰሜን ለንደኑ ክለብ ለአራት ዓመታት የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን፤ 15 ቁጥር ማሊያ እንደሚለብስ ክለቡ ይፋ አድርጓል፡፡

የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ

ፌስቡክ 👉 https://web.facebook.com/fanasport
ቴሌግራም 👉 https://t.me/FMCSport


ስታዲየሞችን በስቱዲዮዋችን!

ዛሬ ከምሽቱ⏱️ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ዞላ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር 'በሞዛይክ ስፖርት' ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ ይደርሳል

የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ

🥅 ኤምሬትስ ስቴድየም

🔴 አርሰናል ከ ኮቨንትሪ ሲቲ 🔵

✍️ ሀሳብና ግምታችሁን አጋሩን!


ቶተንሀም ሆትሰፐር ሳቪንሆን ለማስፈረም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቶተንሃም ሆትስፐር ሳቪንሆን ከማንቼስተር ሲቲ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ለ22 ዓመቱ ብራዚላዊ የመስመር አጥቂ ዝውውር 75 ሚሊየን ፓውንድና ብቃቱ እየታየ የሚጨመር 10 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፍል ይሆናል።

ሳቪንሆ ከስፐርስ ጋር ለረጅም ጊዜ ውል ከመፈራረሙ በፊት የሕክምና ምርመራውን በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ተጫዋቹ ለማንቼስተር ሲቲ ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች 4 ግቦችን በማስቆጠር፤ 2 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ

ፌስቡክ https://web.facebook.com/fanasport
ቴሌግራም https://t.me/FMCSport


ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዘመን ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ሻምፒዮኑ አርሰናል ከኮቨንትሪ ሲቲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል።

ባለፈው የውድድር ዓመት የሊጉን ዘውድ የተቀዳጀው የሰሜን ለንደኑ ክለብ በተከታታይ ዓመት ሻምፒዮን ለመሆን በፍራንክ ላምፓርድ የሚመራውን ኮቨንትሪ ሲቲ በመግጠም ጉዞውን ይጀምራል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸውን ለማጠናከር በክረምቱ የዝውውር መስኮት እንደ ብሩኖ ጉማሬሽ፣ ክሪስቶስ ሶሊስ እና ኤዝሪ ኮንሳ ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

በሌላ በኩል ማንቸስተር ሲቲዎች ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ከተለያዩ በኋላ በቀድሞ ምክትላቸው ኤንዞ ማሬስካ እየተመሩ አዲስ ምዕራፍ ይጀምራሉ።

የግብ ማሽኑን ኧርሊንግ ሃላንድን የያዘው ሲቲ፡ ኤሊዮት አንደርሰንን ጨምሮ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ጠንካራ ተፎካካሪነቱን ለማስቀጠል ተዘጋጅቷል።

ሞሐመድ ሳላህን ጨምሮ ከወሳኝ ተጫዋቾቹ ጋር የተለያየው ሊቨርፑል በአንዶኒ ኢራኦላ እየተመራ የውድድር ዓመቱን ይጀምራል።

በማይክል ካሪክ የሚመራው ማንቸስተር ዩናይትድ በበኩሉ ባለፈው የውድድር ዘመን ያሳየውን መሻሻል ለማስቀጠል በሊጉ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች በመጨመር ወደ ፉክክሩ ይመለሳል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ደካማ ጊዜ ያሳለፈው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በአዲሱ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እየተመራ በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ ፊት በመምጣት ጠንካራ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሀል ሲቲ ከማንቸስተር ዩናይትድ፣ ኒውካስል ዩናይትድ ከሊቨርፑል እና ፉልሃም ከቼልሲ እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ ሌሎች የመጀመሪያ ሳምንት ተጠባቂ ፍልሚያዎች ናቸው።

በዮናስ ጌትነት


የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዳዲስ የጨዋታ እና የዳኝነት ህጎች

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዓመት ነገ ምሽት ሻምፒዮኑ አርሰናል አዲስ አዳጊውን ኮቨንተሪ ሲቲን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጀምራል፡፡ በሊጉ በአዲሱ የውድድር ዓመት የሚተገበሩ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ቦርድ አዳዲስ የጨዋታ እና የዳኝነት ህጎች ይፋ ተደርገዋል፡፡ በዚህም መሰረት በጨዋታ መሃል ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ የሚወጣ ተጫዋች ቢያንስ ለአንድ ደቂቃ ያህል ከሜዳ ውጪ ሆኖ ይቆያል፤ ከዚህ…

https://www.fanamc.com/archives/321002


ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል

የሊጉን ሁሉንም የጨዋታ መርሐ ግብር ውጤቶችና የቅድመ ጨዋታ ትንታኔዎችን በሁሉም የፋና ዲጂታል አማራጮች ይከታተሉ!

የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ

ፌስቡክ 👉 https://web.facebook.com/fanasport
ቴሌግራም 👉 https://t.me/FMCSport


አቶ ኢሳያስ ጅራ ብቸኛ እጩ ሆነው ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አቶ ኢሳያስ ጅራ ለኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ብቸኛ እጩ ሆነው ቀረቡ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴው እጩዎችን እስከ ነሀሴ 4 ቀን 2018ዓ.ም ድረስ መመዝገቡን ገልጿል።

ኮሚቴው ነሐሴ 5 ፣ 11 እና 13 ባደረጋቸው ስብሰባዎች የቀረቡ እጩዎችን ሰነድ የምርመራ እና የማጣራት ተግባር ማከናወኑን አመልክቷል።

በዚህም መሰረት ለእጩ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪነት የቀረቡት ብቸኛ ተወዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ጅራ ቦሾ መሆናቸውን ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።


አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን ከአስቶንቪላ ለማስፈረም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል እንግሊዛዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ኤዝሪ ኮንሳን ከአስቶንቪላ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡

መድፈኞቹ የዊሊያም ሳሊባ እና ጁሪያን ቲምበርን ጉዳት ተከትሎ ኤዝሪ ኮንሳን ወደ ስብባቸው ለመቀላቀል መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ተጫዋቹ በነገው ዕለት የህክምና ምርመራውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ኤዝሪ ኮንሳ በ2019/20 የውድድር ዓመት አስቶንቪላን የተቀላቀለ ሲሆን እስካሁን ድረስ ለቪላ 286 ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡

ኮንሳ አሰቶንቪላ ቪላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ እንዲያሳካ እና የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን እንዲያገኝ ትልቁን ሚና ተጫውቷል፡፡

አስቶንቪላ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ኮንሳን ጨምሮ ዩሪ ቴሌማንስ፣ ሞርጋን ሮጀርስ እና ሉካስ ዲኜን ለተለያዩ ክለቦች አሳልፎ ሰጥቷል፡፡

የአርጀንቲናዊው ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ የቪላ ቆይታ አጠራጣሪ መሆኑን ተከትሎ ጃፓናዊውን ግብ ጠባቂ ዛዮን ሱዙኪን በዛሬው ዕለት አስፈርሟል፡፡

በአብረሃም አበራ


አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን ለማስፈረም ተቃረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል እንግሊዛዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ኤዝሪ ኮንሳን ከአስቶንቪላ ለማስፈረም ተቃርቧል፡፡

አርሰናል የ28 ዓመቱን ተጫዋች የግሉ ለማድረግ መቃረቡን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

ተጫዋቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በአርሰናል ሲፈለግ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

ኤዝሪ ኮንሳ በ2019/20 የውድድር ዓመት አስቶንቪላን የተቀላቀለ ሲሆን አስካሁን ድረስ ለቪላ 286 ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡


ማንቼስተር ዩናይትድ ካርሎስ ባሌባን ለማስፈረም ተቃረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ካሜሩናዊውን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ካርሎስ ባሌባን ከብራይተን ለማስፈረም ተቃርቧል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ ለተጫዋቹ ዝውውር 60 ሚሊየን ፓውንድ ማቅረቡን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

የ22 ዓመቱ ተጫዋች በማንቼስተር ዩናይትድ ለበርካታ ጊዜ ሲፈለግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ባለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት በብራይተን ቆይታው 112 ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡

የመሐል ሜዳ ክፍሉን እያጠናከረ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ ዩሪ ቴሌማንስ እና አንድሬ ሳንቶስ አስቀድሞ ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡


ፖል ፖግባ ከሞናኮ ጋር ተለያየ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሞናኮ ከፈረንሳዊው ተጫዋች ፖል ፖግባ ጋር መለያየቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ፖግባ ከአበረታች ንጥረ ነገር ጋር በተያያዘ ለ19 ወራት ከእግር ኳስ ታግዶ ከቆየ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሞናኮ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለሞናኮ 6 ጨዋታዎችን ብቻ ነው ያደረገው፡፡

የ33 ዓመቱ ተጫዋች በጉዳት ምክንያት ለሞናኮ የሚጠበቀውን ያህል ግልጋሎት መስጠት አልቻለም፡፡

ፖግባ ከቀናት በፊት ልምምድ ላይ አዲስ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ክለቡ ውሉን ለማቋረጥ ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ሞናኮ ፖግባ በቀጣይ የእግር ኳስ ሕይወቱ መልካም ነገር እንዲገጥመው በመመኘት ከተጫዋቹ ጋር ተለያይቷል፡፡

የማንቼስተር ዩናይትድ እና የጁቬንቱስ የቀድሞ ኮከብ ከሀገሩ ፈረንሳይ ጋር በ2018 የዓለም ዋንጫን ማሳካቱ ይታወሳል፡፡

የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ቀጣይ ማረፊያ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡

20 last posts shown.