ከአክሱም ከተማ ጠፍተው የነበሩትን የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ መቀጠሉ ተገለጸ
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት እና አለመረጋጋት በነበረበት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ማሳወቁ አይዘነጋም።
የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን የተዘረፉት እና የጠፉትን 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ብለዋል።
የጠፉትን ቅርሶች ማን እንደወሰዳቸው ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፁት ኃላፊው እነዚህን ቅርሶች የማስመለስ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።