ጀነራል አልቡርሃን ማዕቀብ ቢጣልባቸውም ዘመቻው እንደማይቆም አስታወቁ
የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን ዓለም አቀፍ ባላንጣዎች በእሳቸውና በሀገሪቱ ላይ በቅርቡ አዲስ ማዕቀብ ይጥላሉ ብለው እንደሚጠብቁ ትናንት ዓርብ የገለጹ ሲሆን፣ ይህ ዓለም አቀፋዊ ጫና የፓራሚሊታሪውን ፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) ለመደምሰስ የሚደረገውን ወታደራዊ ዘመቻ እንደማያቆመው አስታውቀዋል።
ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው፤ ጀነራሉ በአልጃዚራ ግዛት በአልማናጊል ከተማ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ባደረጉት ንግግር፤ የሚጣሉ ማናቸውም አዳዲስ የቅጣት እርምጃዎች የሀገሪቱን ቁርጠኝነት ሊሰብሩ ወይም ወታደራዊ ኃይሉ ወደኋላ እንዲል ሊያስገድዱት እንደማይችሉ በጽኑ ተናግረዋል።