❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ከሰባቱ_የዐዋጅ_ጾም አንዱ ለሆነው #ለታላቁ_ዐቢይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሰን። ጾሙን ጾመ በረከት ጾመ ድኅነትን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ያድለን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ጾም_እግዚእነ_በእንቲአነ። አርአያሁ ከመ የሀበነ። ትርጉም፦ አርአያ (ምሳሌ) ይሆነን ዘንድ #ጌታችን_ጾምን_ጾመ"።
✝ ✝ ✝
❤ #ስብሐተ_ነግ ፦ "#ይጹም_ዐይን_ይጹም_ልሣን እዝንኒ ይጹም እምሰሚዐ ኅሡም በተፋቅሮ። ትርጉም፦ #ዐይን _ይጹም_አንደበትም_ይጹም_ጆሮም በአንድነት ክፉ ነገር ከመስማት ይጹም። #ሊቁ ቅዱስ_ያሬድ_በጾም_ድጓው_ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ #ጾም፦ በፊደላዊ ትርጉሙ "ጾመ" ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ተወ፣ ታቀበ፣ ታረመ የሚል ነው። የቃሉ ፍቺ ምግብን መተው፣ ራስን ከምግብ መከልከል መጠበቅ ማለትነው።
❤ #ጾም፦ ማለት ጥሉላት ምግብን መተው፣ ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ ከሌላም ክፉ ነገር መጠበቅ፣ መግዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሓ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብና እርሱን ደጅ መጥናት፣ ማረኝ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበርከክ ምሕረተ አምላክን ለመቀበል መዘጋጀት ነው።
❤ የጾም ጥቅሙ፦ ጾም ተድላ ስጋን የምታጠፋ፣ የስጋን ጦር የምታደክም፣ ቁስለ ነፍስን የምታደርቅ፣ ሰው መላዕክትን መስሎ የሚኖርበትና ኃይል መንፈሳዊን የሚጐናፀፍባት ደገኛ መሳሪያ ናት።
❤ #የጾም_ዓይነቶች
❤ ጾም ሁለት ዓይነት ነው፡- የግል እና የዐዋጅ(የሕግ)።
❤ #የግል_ጾም፦ እግዚአብሔር ኃይሉን ብርታቱን የሰጣቸው ምዕመናን በግል (በስውር) የሚጾሙት የጾም አይነት ነው። ይህም በተለያየ መልኩ ሊሆን ይችላል። ከዐዋጅ ጾም ጋር ግን አንድ መሆን አይገባውም። ይህ ጾም የፈቃድና የንስሓ ጾም ተብሎም በሁለት ይከፈላል።
❤ #የዐዋጅ_ጾም፦ ይህ ጾም በስውር ሳይሆን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ አውቆት የሚጾመው ጾም ነው። ሁሉም በአንድነት ወጥ በሆነ መልኩ የሚጾመው በመሆኑ ከንቱ ውዳሴ የለበትም። በዐዋጅ
ጾም አንድ ሰው እጾማለሁ ቢል በውስጡ እስካልታበየና እስካልተመካ ድረስ ጾምን ሰበከ ይባላል እንጂ ውዳሴ ከንቱን አምጥቶበት ዋጋ አያሳጣውም። መጽሐፍ ቅዱስም የዐዋጅን ጾም እንድንጾም ሲያስተምረን እንዲህ ይላል። "በጽዮን መለከትን ንፉ ጾምንም ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ"። ት.ኢዩ 2፥15 በዚህ መሰረት ጾም በአዋጅ ተነግሮ ሁሉም ሰው ሊጾመው ይገባል። በቤተ ክርስቲያናችን ሰባት የዐዋጅ አጽዋማት አሉ። እነርሱም፦
1. የገሀድ ጾም
2 • የነነዌ ጾም
3 • ጾመ ስብከት (የነቢያት/የገና/ ጾም)
4 • የሁዳዴ ጾም (የዐቢይ ጾም)
5 • የሐዋርያት ጾም (የሰኔ ጾም)
6 • ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና አርብ)
7 • ጾመ ፍልሰታ (የእመቤታችን ጾም)
❤ #ጾመ_ሁዳዴ /የሁዳዴ ጾም/ #የዐቢይ_ጾም፦ ይህ ጾም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ከተጠመቀ በኋላ ወደ ገዳመ ቆሮጦቶስ በመሔድ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከቆመ ሳያርፍ ከዘረጋ ሳያጥፍ በትኅርምት የጾመውና ራሱ ባለቤቱ የመሰረተው በመሆኑ ዐቢይ ተብሏል ማቴ 4፥1። እኛም ጌታ የጾመውን ለማስታወስ፣ በረከቱን ለማግኘት፣ በግብር እርሱን ለመምሰል፣ የሥጋ ፈቃዳችንን ለነፍስ ፈቃዳችን ለማስገዛት እንጾመዋለን። ጌታችን የጾመው እቀደስ እከብር ወይም እነጻ ብሎ ሳይሆን ለእኛ አርዓያ ለመሆን ነው። ጾሙን 40 ቀንና 40 ሌሊት ያደረገበትንም ምክንያት የነገረ ሃይማኖት ሊቃውንት እንደሚከተለው ያስቀምጡታል።
❤ ቀድመው ነቢያት 40 ቀን ጾመዋል። ከዚያ ቢያተርፍ አተረፈ ቢያጎድል አጎደለ ብለው አይሁድ ድርጊቱን ሕገ ወንጌልን ከመቀበል እንዳይከለከሉ።
❤ ነቢዩ ሙሴ በ40 ዘመኑ ለዕብራዊ ረድቶ ግብጻዊውን ገድሎ በአሸዋ ቀብሮታል። ሙሴ
የጌታ፣ ዕብራዊ የአዳም፣ ግብጻዊ የዲያቢሎስ፣ አሸዋ የመስቀል የሶስቱ አርዕስተ ኃጣውእ ምሳሌ።
❤ ሙሴ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ጾሞ ሕገ ኦሪትን ሰርቷል።ጌታም 40 መዓልትና 40 ሌሊት ጾሞ ሕገ ወንጌልን የሚሰራ ነውና። እንዲሁም ሙሴ 40 ዘመን በምድያም ኖሮ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት መርቶ አውጥቷቸዋል። ጌታም 40 መዓልትና 40 ሌሊት ጾሞ ነፍሳትን ከሲዖል ባርነት ነጻ የሚያወጣ ነውና።
❤ ሕዝቅኤል በፀጋማይ (በግራ) ጎኑ 40 ቀን ተኝቶ ስድስት መቶ (600) ሙታን አስነስቷል። እናንተም 40 መዓልትና 40 ሌሊት ብትጾሙ ትንሳኤ ዘለክብር ትነሳላችሁ ሲለን ነው።
❤ ዐቢይ ጾም በተለያዩ ስሞች ይጠራል። ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ፦
❤ #ጾመ_ሁዳዴ፦ በጥንት ዘመን ገባሮች ለባለርስት የሚያወርሱት መሬት "ሁዳዴ" ይባል እንደነበረ ዐቢይ ጾምንም በመጾማችን ሠራኤ ሕግ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ርስት መንግስተ ሰማያትን ያወርሰናልና።
❤ #የካሳ_ጾም፦ የቀደመው አዳም አትብላ የተባለውን በልቶ ከገነት በመባረር ለውርደት ለሞትና ለሲዖል ባርነት ተዳርጓል። ዳግማዊ አዳም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በምግብ ምክንያት የመጣውን ስደት በጾም ድል ነስቶ ክሶናልና።
❤ #የቀድሶተ_ገዳም_ጾም፦ ከከተማ ርቆ ከሰው ተለይቶ ከአራዊት ጋር ኖሮ በዲያቢሎስ ተፈትኖ ድል አድርጎ እነ ኤልያስ እነ ዮሐንስ የኖሩትን የብሕትና ኑሮ ለባሕታውያን ለመነኰሳት ለገዳማውያን ባርኮ ቀድሶ የሰጠበት ነውና።
❤ #የሥራ_መጀመሪያ_ጾም፦ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማስተማር ስራውን ከመጀመሩ፣ አንቀጸ መንግስተ ሰማያትን ከማስተማሩ አስቀድሞ የጾመው ጾም በመሆኑ የስራ መጀመሪያ ጾም ተብሎም ይጠራል። እናንተም ሥራ፣ አገልግሎት ከመጀመራችሁ በፊት አስቀድማችሁ ጹሙ ጸልዩ ሲለን ነው።
❤ ዐቢይ ጾም ለሃምሳ አምስት(55) ቀናት የምንጾመው ጾም ሲሆን ካሉት ሌሎች
አጽዋማት ውስጥ ብዙ ቀናት ያሉበት ነው። ዐቢይ ማለት ዋና ማለት ሲሆን ጾሙ በቀን ብዛት፣ በምስጢርም፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የጾመው ጾም በመሆኑም የአጽዋማት ሁሉ የበላይ ነው። ጾሙ ሶስት ክፍሎችና ስምንት ሳምንታት አሉት።
❤ #የድል_ጾም፦ ሦስቱን አርስተ ኃጣውን ስስት፣ ፍቅረ ነዋይንና ትቢትን ድል ያደረገበት ስለሆነ። ማቴ 4፥1-1።
❤ ሶስቱ ክፍሎች
1 #ጾመ_ሕርቃል - ከዘወረደ እስከ ቅድስት ድረስ ያለው የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ነው።
2 #የጌታ_ጾም - ከቅድስት ጀምሮ እስከ ሆሳዕና ድረስ ያሉት 40 ቀናት ናቸው።
3 #ሰሙነ_ሕማማት - የጌታን መከራ መስቀል የምናስብበት ከሆሳዕና እስከ ትንሳኤ ያለው
የመጨረሻው ሳምንት ነው።
ስምንቱ ሳምንታት
1. ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)
2. ቅድስት
3. ምኵራብ
4. መጻጒዕ
5. ደብረ ዘይት
6. ገብር ኄር
7. ኒቆዲሞስ
8. ሆሳዕና
❤ ምንጭምንጭ፦ ጾምና ምጽዋት በዲ/ን ቃኘው ወልዴ የመናፍቃን ጥያቄና መልሶቻቸው በዲ/ን አሐዱ አስረስና መጽሐፍ ቅዱስ።
❤ ጾሙ ለአገራችን ኢትዮጵያና ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነቻችን ሰላም፣ ፍቅር አንድነትና መተሳሰብ የሚያመጣ ያድርግል። መልካም የጾም ወራት ለሁላችንም ይሁንልን።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886