ከአጠቃላይ ተፈታኞች 36 ሺህ 409 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አልፈዋል- ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 36 ሺህ 409 መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን እና ተማሪዎችም ከሌሊቱ 6 ሠዓት ጀምረው ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች የነበረው የደንብ መተላለፍ ከአለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ እንደነበርም አንስተዋል፡፡
አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን በመግለጽ÷ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል፡፡
ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ሀገራዊ አማካኝ ውጤት 29 ነጥብ 76 መሆኑን ጠቅሰው÷ የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ከ700ው 675 መሆኑን እና ይህም በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ከፍተኛ ውጤት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
እንዲሁም ከ600 ከተፈተኑት ውስጥ 575 ከፍተኛው ውጤት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow