TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Ghion Maleda

17 Nov, 19:25

Open in Telegram Share Report

01:29
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
" ከዚህ ከመኪናየ መሪው ላይ ግደሉኝ እንጅ አልወርድም" - አሽከርካሪው በለቅሶና በጭንቀት ውስጥ ሆኖ

በትላንትናው እለት በዱከም ከተማ የተፈጸመ አሰቃቂ ድርጊት፤ ዜጎች ለህግ ከፍ ያለ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ።በተዘዋወረው አሰቃቂ ቪዲዮ ላይ፣ የታጠቁ 2 ግለሰቦች አሽከርካሪውን ከተሽከርካሪው እንዲወርድ በግፊት ሲያስፈራሩት የሚታይ ሲሆን...

ቪዲዮው ከላይ እንደምታዩት አሽከርካሪውም በከፍተኛ ጭንቀትና ለቅሶ “እዚሁ መሬት ላይ ግደሉኝ እንጂ አልወርድም” በማለት ሲማጸን ይደመጣል።

ይህ ክስተት የዜጎችን ደህንነት አሳሳቢነት በግልጽ የሚያሳይና በርካቶችን ያስደነገጠ ሆኗል።ይህንን ዘግናኝ ድርጊት ተከትሎ፣ ማህበረሰቡ እና የተለያዩ ዜጎች “የአሽከርካሪዎች እና የሰላማዊ ዜጎች መሠረታዊ የደህንነት ዋስትና መቼ ነው የሚረጋገጠው?” በማለት ጥያቄዎቻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

ህብረተሰቡ አሁን ላይ አጥብቆ ከሚያነሳቸው ጉዳዮች መካከል የክልሉ መንግስት የጸጥታ አካላት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ሕገ-ወጥ ድርጊቱን የፈጸሙትን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ይገባቸዋል የሚለው ጥያቄ ዋናው ነው።

ዜጎች በነጻነት በሰሯቸው ስራዎችና መንገዶች ላይ እንዲህ አይነት ጥቃት ሲደርስ ዝም ማለት ተገቢ ባለመሆኑ፣ ባለስልጣናት እና የጸጥታ አካላት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማህበረሰቡ ጥሪውን እያቀረበ ይገኛል።

ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda

8.4k 0 28 26 92
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot