እስልምና ከ9 አመት በኋላ በ2035 ክርስትናን በመብለጥ በዓለም ትልቁ ሃይማኖት እንደሚሆን ተተነበየ !
እስልምና ከዘጠኝ ዓመት በኋላ በአውሮፓውያኑ 2035 ክርስትናን በመብለጥ በዓለም ትልቁ ሃይማኖት ይሆናል ተብሎ እብደሚጠበቅ የፒው የምርምር ማዕከል ትንበያ አመለከተ።
ላለፉት 25 ዓመታት በሃይማኖታዊ የሕዝብ አሰፋፈር ላይ ተዓማኒነት ያላቸው ሪፖርቶችን ሲያወጣ የቆየው ፒው፣ እስልምናም ሆነ ክርስትና እያደጉ ቢሆንም፣ እስልምና ግን እጅግ በፈጠነ ሁኔታ እያደገ መሆኑን ገልጿል።
ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ሙስሊሞች ከሌሎች ዋና ዋና ሃይማኖቶች ይልቅ ብዙ ልጆችን የመውለድ ዝንባሌ ስላላቸው እንደሆነ ማዕከሉ ትናንት ኀዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ዝርዝር ትንበያ አስረድቷል።
የፒው ከፍተኛ የሥነ-ህዝብ ተመራማሪ ኮራንድ ኮንራድ ሃኬት፣ ሃይማኖትን መቀየር እና ሌሎች የሃይማኖት ለውጦች ከወሊድ መጠን አንጻር ያላቸው ድርሻ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ስለማብራራታቸው ኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።
እንደፒው መረጃ ከሆነ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2020 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ የሙስሊሞች የወሊድ መጠን በአንዲት ሴት 3.1 ልጆች ነበር። ክርስቲያኖች ሴቶች ደግሞ በ2.5 ልጆች ይከተላሉ።
የሌሎች ሃይማኖቶች አማካይ የወሊድ መጠን 1.6 ሲሆን፣ ይህም እያንዳንዱ ትውልድ ራሱን ለመተካት አስፈላጊ ነው ተብሎ ከሚታሰበው 2.1 ምጣኔ ያነሰ ነው።
ከዚህ ቀደም በነበረው የፒው ግምት እንደሚያሳየው፣ በ2020 በዓለም ዙሪያ 2.27 ቢሊዮን ክርስቲያኖች እና 2.02 ቢሊዮን ሙስሊሞች ነበሩ።
በአዲሱ የፒው ትንበያ መሠረት ደግሞ፣ በ2035 በዓለም ላይ 2.57 ቢሊዮን ሙስሊሞች እና 2.52 ቢሊዮን ክርስቲያኖች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አሁን ያለው አዝማሚያ ከቀጠለ፣ በ2070 ደግሞ በዓለም ዙሪያ ከ3.6 ቢሊዮን በላይ ሙስሊሞች እና ከ3 ቢሊዮን በታች ክርስቲያኖች ይኖራሉ።
በ2020 እና በ2070 መካከል የዓለም ሕዝብ ቁጥር በ29 በመቶ እንደሚጨምር ፒው አስታውቋል።ማዕከሉ ከተነተናቸው የሃይማኖት ቡድኖች መካከል ከዚህ ዕድገት ጋር እኩል ይጓዛሉ ተብሎ የሚጠበቁት ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው። ክርስቲያኖች በ30 በመቶ፣ ሙስሊሞች ደግሞ በ80 በመቶ ያድጋሉ።
ሂንዱዎች እና አይሁዶች በጠቅላላ ቁጥራቸው እያደጉ ቢሆንም፣ ከዓለም ሕዝብ ቁጥር አንጻር ያላቸው ድርሻ ግን እንደሚቀንስ ፒው ገልጿል።
የቡድሂስቶች ቁጥርም ሆነ ከዓለም ሕዝብ ያላቸው ድርሻ እንደሚቀንስ ተገምቷል። ይህ ከሆነባቸው ምክንያቶች አንዱ በቻይና፣ በደቡብ ኮሪያ እና በጃፓን አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር እንደሚቀንስ የሚጠበቅ መሆኑ ነው።
በመጪዎቹ አሥርት ዓመታት ውስጥ፣ አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ቁጥር ዕድገት የሚከሰተው በአፍሪካ፣ በተለይም አብዛኛው ሕዝብ ክርስቲያን ወይም ሙስሊም በሆነበት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት እንደሆነ ፒው ገልጿል።
ከፍተኛ “ሃይማኖት የሌላቸው” ሰዎች ድርሻ ያላትን ነገር ግን አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥሯ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ያለችውን ቻይናን ሳይጨምር፣ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ቁጥር በ2070 ከ180 ሚሊዮን በላይ እንደሚያድግም ፒው አስታውቋል።
እናንተ በዚህ የፒው የምርምር ማዕከል ትንበያ ትስማማላችሁ ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?
ግዮን ማለዳ መረጃውን ያገው ከቢቢሲ ነው።
ግዮን ማለዳ
@GhionMaleda