"የኢትዮጵያ እግር ኳስ ‘አንችልም’ ከሚል ትህትና ሊነሳ ይገባል።" – ጋዜጠኛ አልዓዛር አስገዶም
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ለዘመናት ከተተበተበበት «እንችላለን» እና «በቴክኒክ ጥሩ ነን» ከሚል ራስን የማታለል አዙሪት በመውጣት፣ «አንችልም» ከሚል እውነተኛ ትህትና ሊጀምር እንደሚገባ ጋዜጠኛ አልዓዛር አስገዶም አሳሰበ።
ጋዜጠኛው «ፉትቦል ካፌ» በተሰኘው መሰናዶው ላይ ባቀረበው ሰፊ ትንታኔ፣ ሀገሪቱ በእግር ኳሱ ዘርፍ ውጤታማ መሆን ያልቻለችው የችግሩን ትክክለኛ መንስኤ በአግባቡ መርምራ ማከም ባለመቻሏ መሆኑን አስረድቷል።
በእግር ኳሱ ዙሪያ «በቴክኒክ የተካንን ነን» የሚለው የተለመደ አባባል መሰረተ ቢስ መሆኑን የጠቀሰው አልዓዛር፣ እውነተኛ የእግር ኳስ ቴክኒክ ማለት ትክክለኛ ቅብብል (ፓሲንግ)፣ ኳስ ማሻማት (ክሮሲንግ) እና ኳስ መንጠቅ (ታክሊንግ) እንጂ ሰፈር ውስጥ የሚታይ የፍሪስታይል ትርኢት አለመሆኑን አብራርቷል።
ሀገሪቱ «ኳስ እንችላለን» ከሚል የተሳሳተ መነሻ ስለምትጓዝ፣ ሽንፈት ባጋጠመ ቁጥር አንድ ቀን ዕድልን፣ በሌላ ቀን ደግሞ አሰልጣኙን፣ በረኛውን ወይም አጥቂውን ተጠያቂ ከማድረግ ባለፈ የእግር ኳሱን ዋነኛ ህመም ለመለየትና ለማከም እንዳልቻለች ገልጿል።
ለዚህም የእንግሊዝ እግር ኳስን እንደ ትልቅ ማሳያ ያነሳው ጋዜጠኛው፣ እንግሊዝ የእግር ኳስ መገኛና የዓለም ተወዳጅ ሊግ ባለቤት ብትሆንም፣ በአንድ ወቅት ከፈረንሳይ፣ ከስፔንና ከጀርመን ወደ ኋላ መቅረቷን በትህትና መቀበሏን አስታውሷል።
በወቅቱ የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የልማት ኃላፊ የነበሩት ሰር ትሬቨር ብሩኪንግ «አልቻልንም» በሚል መንፈስ የፈረንሳይን ታዋቂ የክሌርፎንቴን አካዳሚ አሰራር በማጥናትና በሴንት ጆርጅስ ፓርክ ተግባራዊ በማድረግ...
እንግሊዝ ከ17 እና ከ19 ዓመት በታች የዓለምና የአውሮፓ ዋንጫዎች ላይ ዋና ቡድን ለመሆን የበቃ ሲሆን እንዲሁም ከ2018 ወዲህ በትላልቅ ውድድሮች መደበኛ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ እንድትሆን ማስቻላቸውን ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ከሚገኝ ውጤት ባለፈ እንደ ሴኔጋል፣ ግብጽ፣ ናይጄሪያ እና ኮትዲቩዋር ያሉ የአፍሪካ ኃያላንን በወጥነት መገዳደር ይቅርና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና እንኳን ምርጡ ቡድን መሆን አለመቻሉን አልዓዛር በግልጽ አስቀምጧል።
በመሆኑም የብሔራዊ ቡድኑን የአሰልጣኝነት ወንበር ሁሉም ሰው በየተራ እየመጣ የሚሄድበት መተላለፊያ (ሪቮልቪንግ ዶር) ማድረግ መፍትሄ እንደማያመጣ ጠቅሶ፣ ላለፉት 30 ዓመታት የዘለቀውን መሰረታዊ የእግር ኳስ ችግር ለመቅረፍ ከትህትና የመነጨ መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥቷል።
Via፦ ጌጡ ተመስገን
ግዮን ማለዳ
@GhionMaleda