Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በማህበራዊ ሚዲያ የለበሱትን ልብስ መኖሪያ ቤታቸውን በሚያሳዩ ሰዎችን በተመለከተ ጠንካራ ትችት ሰነዘረች ።
ከላይ በቪዲዮ እንደምታዩት ታዋቂዋ አርቲስት ቻቺ ታደሰ በመቅዲ ሾው ላይ በሰጠችው ቃለ መጠይቅ፣ አሁን ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየታየ ያለውን አጉል ንትርክ እና የቁሳቁስ እይታን (ማቴሪያሊዝም) አጥብቃ ተቸች።
አርቲስቷ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚስተዋለውን ጊዜ ማጥፋትና ፉክክር በመተቸት፣ "ምንድነው የምንጠማመዘው? ምንድነው የምንጣጣው? ምንድነው ይሄ ሁሉ የምናደርገው?" ስትል ወቅሳለች።
በተለይም ሰዎች የየዕለት ውሎአቸውን፣ የለበሱትን ልብስ፣ የመኖሪያ ቤታቸውን እና መኝታ ቤታቸውን ሳይቀር በየጊዜው በሚዲያ ላይ ማውጣታቸው አላስፈላጊ መሆኑን ገልጻ፣ "ማን ያስባል?" (Who cares?) በማለት ድርጊቱን ኮንናለች። እግዚአብሔር የባረከው ሰው ባገኘው ነገር በግሉ ሊደሰትበት እንደሚገባም መክራለች።
ከዚህም ባሻገር ቻቺ ታደሰ የሴቶችን እሴት ከቁሳቁስ ጋር አያይዞ መመልከትን አጥብቃ ተቃውማለች። "ሴት በዛ ልትገመት አትችልም፤ ሴት በቁሳቁስ ከተገመተች በጣም ወድቀናል ማለት ነው" በማለት ሴቶች ከቁሳቁስ የላቀ ክብር እንዳላቸው አስገንዝባለች።
ሴቶች ሰውን ሠርተውና አሳድገው ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስረክቡ በመሆናቸው፣ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ይህንን ትልቅ ዓላማና ኃይል በመገንዘብ በዚህ ብቻ ሊኮሩ እንደሚገባ አሳስባለች።
ግዮን ማለዳ
@GhionMaleda