TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Ghion Maleda

18 Nov, 22:22

Open in Telegram Share Report

Prev Next
በንግድ ሥራ ላይ በነበረች እናት ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

በንግድ ስራ ላይ የተሰማራች የሦስት ልጆች እናት ​በእንዳሥላሴ-ሽረ ከተማ ፣ ኅዳር 8 ቀን 2019 ዓ/ም በሥራ ቦታዋ ላይ እያለች በጠራራ ፀሐይ በስለት ተወ *ግታ ሕይወቷ ማለፉን ከከተማው ፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የከተማዋ ፖሊስ ዛሬ ረቡዕ፣ በምስል አስደግፎ ባሰራጨው መረጃ ፤ በዚሁ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ተስፋይ ዮሐንስ የተባለ ግለሰብ ሳይውል ሳያድር በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስታውቋል።

​ፖሊስ አክሎም፤ ተጠርጣሪው ቀደም ሲል በሌላ ወንጀል የ22 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት የነበረና፣ በክልሉ ባገረሸው ጦርነት ምክንያት ከእስር ከተለቀቁት አንዱ መሆኑን ገልጿል።

ከቀናት በፊትም ሁለት ሴቶች በተመሳሳይ የጭካኔ ተግባር መገደላቸው ተሰምቷል። ይህም በከተማዋ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

​በከተማዋ እየተበራከተ የመጣው ይህ አሰቃቂ የወንጀል ተግባራት ያሳሰበው የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ኮማንድ ፖስት ግብረ-ኃይል፤ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ሲል ጥብቅ እገዳዎችን ጥሏል።

​ኮማንድ ፓስቱ ​በከተማዋ የሚካሄዱ የቢንጎ ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆሙ ፣​ የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እንዲገደቡ እንዲሁም የሰዎች እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ጥብቅ ክልከላ እንደተደረገበት ተነግሯል።

​ኮማንድ ፖስቱ፤ ሁሉም የጸጥታ አካላት በእጃቸው የሚገኝን ማንኛውንም የጦር መሣሪያ እስከ ኅዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጸጥታ ጽሕፈት ቤት እንዲያስመዘግቡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።

Via፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ
ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda

3.2k 0 0 1 33
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot