TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Ghion Maleda

19 Nov, 07:46

Open in Telegram Share Report

ጋዜጣ አዟሪው  መረጃ ሳይኖረህ አታውራ ።- የቲክቶከረ ጆን ዳንኤል ነቀፉ በጋዜጠኛ ሶዶ ለማ ላይ

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ ያለፈው አርቲስትና የስፖርት ባለሙያ አንተነህ ተኸርቁ ሀዘን ገና አልበረደም።

የቤተሰቡና የአድናቂዎቹ ልብ ባልተረጋጋበት በዚህ ሰዓት፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሌላ አነጋጋሪ ክስተት ተፈጥሯል።

ውዝግቡ የተነሳው አንድ የኤሌክትሮኒክስ እና የድርጅቱ አስተዋዋቂ ቲክቶከር ጆን ዳንኤል፣ ወደ ሀዘንተኞች ቤት በማቅናት ያደረጉትን የእቃ ድጋፍ ተከትሎ ነው።

ድርጊቱን የተመለከተው ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ(ሶዶ ለማ-Sodo Lema )፣ የንግድ ማስታወቂያና ቻሌንጅን ወደ ለቅሶ ቤት ይዞ መግባት ከባህላችንና ከስነ-ምግባር ያፈነገጠ ነው ሲል ጥልቅ ትዝብቱን አስፍሯል።

ሶዶ ለማ በትችቱ፣ “ካሜራ ደቅኖ የድርጅቱን ስም እየጠሩ ለሟች ቤተሰቦች የልብስ ማጠቢያ ማሽንና መተኮሻ ካውያ ማበርከት ተገቢ ነው ወይ?” ሲል ጠይቋል።

ጋዜጠኛው ያነሳውን ትችት ተከትሎ ቲክቶከር ጆን ዳንኤል በቪዲዮ ምላሽ ሰጥቷል። ጆን በምላሹ ጋዜጠኛውን “ጋዜጣ አዟሪ” ሲል የገለጸው ሲሆን፣ ድርጊቱ ማስታወቂያ ሳይሆን ቅን ትብብር መሆኑን አስረድቷል።
“እኔ የሄድኩት ማስታወቂያ ለመስራት አይደለም።

የምንወደው ኮሜዲያን ማርቆስ የአንተነህ እህት የልብስ ማጠቢያ  (ላውንደሪ) ከፍታ ራሷን እንድትችል በማሰብ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽንና ሁለት ካውያ እንድንተባበራት ጠየቀኝ። ኤሌክትሮኒክስ ድርጅቱ በደስታ እቃዎቹን ልኮልናል።

ቤት ውስጥ ምንም ቪዲዮ አልቀረጽንም፤ እቃውን አድርሰናል የሚል መረጃ ብቻ ነው የሰጠነው። እንኳን ሀዘን ቤት ሄደው ሊያጽናኑ ቀርቶ በገጻቸው ላይ 'እግዚአብሔር ያጽናችሁ' ያላሉ ሰዎች፣ አሁን አጀንዳ ፈጥረው እውቅና ለማግኘት ይሞክራሉ ብሏል።

ጆን ዳንኤል አያይዞም ፣ "መረጃ ሳይኖርህ ዝም ብለህ የምትጽፈው 'ጋዜጣ አዟሪ' ነኝ ያልከውም ሰውዬ ጉዳ በህግ ተይዟል " ሲል ጋዜጠኛውን በህግ አግባብ ሊጠይቀው መሆኑን ጠቁሟል።

የጆን ዳንኤልና ሶዶ ለማ ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሁለት የተለያዩ አመለካከቶችን ፈጥሯል።አንደኛው ወገን በሀዘን ቤት ካሜራ መደቀንና የድርጅት ስም መጥራት የቤተሰቡን ስሜት የሚጎዳና ስነ-ምግባር የጎደለው ድርጊት ነው ሲል ይኮንናል።

በሌላ በኩል ደግሞ ዓላማው ቤተሰቡን በዘላቂነት መደገፍ እስከሆነ ድረስ በአቀራረቡ ላይ መነታረኩ ተገቢ አይደለም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎችም አሉ።

የሆነው ሆኖ ክስተቱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደረጉ የበጎ አድራጎት ስራዎችና የማስታወቂያ አቀራረቦች የማህበረሰቡን ወግና ስነ-ልቦና ባከበረ መልኩ ሊከናወኑ እንደሚገባ ትልቅ ትምህርት የሰጠ ሆኗል። በ

ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የጋዜጠኞች እና የቲክቶከሩ የቃላት ጦርነት እየጨመረ መጧል ። በቅርቡ የእግርኳስ ጋዜጠኞች እና ስለ እግር ኳስ የሚዘገቡ ቲክቶከሮች ግጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር አይዘነጋም ።  እናንተ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አላችሁ ? ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ ?
           
          ግዮን ማለዳ

@GhionMaleda

2.7k 0 1 3 24
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot