የቀድሞ የአማራ ባንክ አመራሮች በ200 ሚሊዮን ብር ብድር የወንጀል ክስ ቀረበባቸው፡፡
የፌዴራል አቃቤ ህግ በቀድሞ የአማራ ባንክ አመራሮች ላይ ሌላ የወንጀል ክስ መሰረተ፡፡ ይህ ክስ በ200 ሚሊዮን ብር ብድር ላይ ያነጣጠረ ሲሆን አቃቤ ህግ እንደገለፀው ለብድሩ እንደዋስትና ቀረቡ የተባሉት 30 የጭነት መኪናዎች ‹‹የሌሉ›› ናቸው፡፡
በዚህ ክስ የባንኩ የቀድሞ የደንበኞች ግንኙነት ጉዳዮች ሀላፊው አቶ መስፍን ጌታቸውና የባንኩ ደንበኛ የሆኑት አቶ ቻላቸው ታዬ ስማቸው መጠቀሱን ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የፀረ ሙስና ችሎት የቀረበው ክሱ ተከሳሾቹ ለአቶ ቻላቸው ህገ ወጥ ጥቅም ለማስገኘት ሲሉ በባንኩ ላይ...
የ200 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ማድረሳቸውን የሚገልፅ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው ሁለቱም ተከሳሾች ከጥቅምት ወር አንስቶ በእስር ላይ እንደሚገኙ አስረድቷል፡፡
በክሱ ላይ አቶ ቻላቸው ‹‹ሀሰተኛ ማስያዣ›› በማቅረብ የብድር ጥያቄ ማቅረባቸው የተገለፀ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም ‹‹የሌሉና ፎርጅድ የባለቤትነት ሊብሬ የቀረበላቸው›› 30 የጭነት መኪናዎች እንደሚገኙበት ጠቅሷል፡፡
አቶ መስፍን ደግሞ ‹‹ሆነ ብለው ብድሩ እንዲፀድቅ ግፊት በማድረጋቸው›› የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ዘገባው ገልጿል፡፡ በአማራ ባንክ የቀድሞ አመራሮች ላይ እንዲህ አይነት የወንጀል ክስ ሲቀርብ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡
ባለፈው አመት በርካታ የቀድሞ አመራሮቹ በ137 ሚሊዮን ብር ሙስና ተከሰው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑ ይታወቃል፡፡
Via፦ Zehabesha
ግዮን ማለዳ
@GhionMaleda