''ትዕቢተኛ ሴት ከሴት ጋር ልትኖር ትችላለች፤ ከባል ጋር ግን በተአምር አትኖርም!'' - የትዳር አማካሪ ፀጋዬ አሰፋ
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ክብርን ይፈልጋል። ይህ የወንድ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ሁሉ የጋራ ባህሪ ነው። የትዳር አማካሪው ፀጋዬ አሰፋ በአንድ ወቅት እንዳነሳው፣ ትዕቢተኛ ሴት ከሌላ ሴት ጋር ተቻችላ ልትኖር ትችል ይሆናል...
ከወንድ ጋር፣ ከባል ጋር ግን በታሪክ ተግባብታ መኖር አትችልም። ልቧ በንቀትና በትዕቢት የተሞላ ሴት ወይ ትዳር ሳትይዝ ቆማ ትቀራለች፣ አልያም ብታገባ እንኳ መልሳ የመፍታት ዕድሏ እጅግ ሰፊ ነው።
በአንድ በኩል ትዳርን ከልብ የሚፈልጉ፣ ትሁትና ቅን ሆነው ለመግባባት፣ ለማውራትና ለመቀራረብ የአቅማቸውን ጥረት የሚያደርጉ ሴቶች አሉ፤ የእነዚህ ቅንነት እጅግ ደስ የሚያሰኝና የሚያስመሰግን ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ማግባት እየፈለጉ ነገር ግን በአደገኛ ትዕቢት የተተበተቡ ሴቶች ይስተዋላሉ። ለእነዚህ ሴቶች የትዳር አማካሪው ፀጋዬ የሚለግሰው ምክር ግልጽ ነው፦
መጀመሪያ ትሁት መሆን፣ ቀለል ማለትና ልብን ሰበር ማድረግ። ሴት ልጅ ሴት የምትሆነው፣ ሚስትም ልትሆን የምትችለው በትህትና፣ በመልካምነትና በቅንነት ስትጌጥ ነው።
በተለይ በአረብ ሀገራትም ሆነ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ሴቶች በብዙ ነገሮች ጠንካራና ጎበዝ ሊሆኑ ይችላሉ። ሆኖም የማይፈልጉት ሰው እንኳ ቢደውልላቸው በትህትና፣ በየዋህነትና በቅንነት ማናገርን መልመድ ይኖርባቸዋል።
ራስን ከፍ አድርጎ በመስቀል፣ የዛሬ ሰላሳ ዓመት የነበረውን ዘመን በማሰብ «ወንዱ ጨቅጭቆኝ፣ ጀንጅኖኝና ታግሎኝ ያግኘኝ» የሚል አስተሳሰብ በዛሬው ዘመን አይሰራም። የዘመኑን አካሄድ መረዳት ያስፈልጋል።
ሴት ልጅ ብትግደረደር እንኳ መግደርደሯ በቅንነትና በጨዋነት የታጀበ መሆን አለበት ። ለዚህም አንድ ጥሩ ማሳያ አለ። አንድ ወጣት በሚዲያ ቀርቦ ለወደዳት ልጅ የፍቅር ጥያቄ ያቀርብላታል።
ልጅቷ ከእሱ ጋር እንደማይሆን ጠንቅቃ ታውቃለች፤ ነገር ግን ጨዋና ስነስርዓት ያላት ሴት ስለነበረች ሰብዕናውን ሳትነካ «እሺ፣ ላስብበት» ስትል በአክብሮት መለሰችለት። ጨዋነት ማለት ይህ ነው።
ብዙዎች የማይናግሩት ሚስጥር ቢኖር፣ ወንዶች ትሁት፣ መልካምነት የተላበሰች ለወንድ ልጅ ክብር ያላትን ሴት እንደሚወዱ ነው። ሚስት ልትሆን የምትችለውም እንዲህ ያለችዋ ሴት ናት።
ከዚያ ውጪ እዚህና እዚያ የምትንጠለጠልና በትዕቢት የምትወጠር ሴት ፣ ለጊዜያዊ ፍላጎት ካልሆነ በቀር ለትዳርና ለቁም ነገር ፈጽሞ የማትፈለግ ሆና ትቀራለች።
ብዙ ጊዜ ሴቶች ትዕቢተኛ የሚሆኑት በየዕለቱ ብዙ አላስፈላጊና ፌዘኛ ሰዎች ስለሚደውሉላቸው ሁሉንም በአንድ ዓይን በመመልከት ነው። ነገር ግን ከአስር ፌዘኞች መካከል አንድ እውነተኛ ቁም ነገረኛ ሰው ሊኖር ይችላል።
የማይፈልጉትን ሰው በጨዋነት መሸኘት ወይም መዝጋት ሲቻል፣ ሁሉንም በንቀት ማናገር ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል። እስቲ አስቡት፤ ሊያገባት የፈለገ አንድ ቁም ነገረኛ ወንድ ከጓደኛው ጋር ቁጭ ብሎ ስልኩን «ላውድ» ላይ አድርጎ ይደውልላታል።
እሷ ግን ምንም የሚጋብዝ ለዛ ሳይኖራት በበረዶ በቀዘቀዘ ንቀት «ሄሎ... እሺ... ምን ልታዘዝ... እሺ... አመሰግናለሁ...» እያለች ብትመልስለት፣ ያ ሊያገባት የፈለገ ሰው ምን ብሎ ሊያወራት ይችላል? አንደበቱ ይዘጋል፣ ፍላጎቱንም ይተወዋል።
ትዳር የሚገነባው በጉልበት ወይም በኩራት ሳይሆን በተሰበረ ልብና በቀና መንፈስ ነው። ትዕቢት የዘጋውን የትዳር በር የሚከፍተው ትህትና፣ መልካምነትና ለሰው ልጅ የሚሰጥ ንጹህ ክብር ብቻ ነው።
ግዮን ማለዳ
@GhionMaleda