ወጣቶች ወደ ከተማ መፍለሳቸውን ተከትሎ በ1 ስኒ ቡና ባነሰ ዋጋ የሚሸጡ ባዶ ቤቶች ቁጥር ጨመረ
በጣሊያን ገጠራማ መንደሮች የሚኖሩ ወጣቶች የተሻለ ሥራ እና ሕይወት ፍለጋ ወደ ትላልቅ ከተሞች እና ወደ ውጭ ሀገር በመፍለሳቸው ምክንያት፣ በርካታ ታሪካዊ መንደሮች ያለ ነዋሪ ጭር ብለው ቀርተዋል።
በተለይም በደቡብ ጣሊያን እና በሲሲሊ ደሴት የሚገኙ የአካባቢ መስተዳድሮች መንደሮቻቸው ሙሉ በሙሉ እንዳይጠፉ ሲሉ፣ ባዶ የቀሩ ቤቶችን በ1 ዩሮ (ከአንድ ስኒ ቡና ባነሰ ዋጋ) ለሽያጭ ማቅረብ ጀምረዋል።
የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ ከቤቱ ሽያጭ ገንዘብ ማግኘት ሳይሆን፣ የውጭ ሀገር ዜጎችን እና ባለሀብቶችን በመሳብ ጭር ያሉ መንደሮችን ዳግም በሰው እንዲሞሉ እና የአካባቢው ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።
ቤቱን በ1 ዩሮ የሚገዛ ማንኛውም ሰው ግን አንድ ዋና ቅድመ ሁኔታ አለበት፤ ይኸውም ቤቱን በገዛ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ በራሱ ወጪ አድሶ ለመኖሪያነት ማብቃት የሚጠበቅበት ሲሆን፣ ለእድሳቱ ከ20,000 እስከ 50,000 ዩሮ ሊወጣ ይችላል።
በተጨማሪም ገዢው ቃል የገባውን እድሳት በሰዓቱ እንደሚያጠናቅቅ ለማረጋገጥ ወደ 5,000 ዩሮ የሚጠጋ የዋስትና ማስያዣ (Deposit) የሚያስይዝ ሲሆን፣ እድሳቱ ሲጠናቀቅ ገንዘቡ ተመላሽ ይደረግለታል።
ይሁን እንጂ፣ እንደ ሮም፣ ሚላን እና ፍሎረንስ ባሉ ትላልቅ የጣሊያን ከተሞች አሁንም የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ የቤት ኪራይ እና የግዢ ዋጋ ውድ ሆኖ ቀጥሏል።
Via፦ መናኸሪያ ሬዲዮ
ግዮን ማለዳ
@GhionMaleda