Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በጋቶች ፓኖምና ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረው ክስተት ፤ የዘረኝነት ጥቃት ነበር ወይስ የደጋፊዎች ተቃውሞ?
በብሔራዊ ቡድኑ ካፒቴን ጋቶች ፓኖምና በባህር ዳር ስታዲየም ውስጥ በነበሩ ደጋፊዎች መካከል ከማክሰኞው ጨዋታ በኋላ የተፈጠረው ክስተት አሁንም የተለያዩ አስተያየቶችን እያስነሳ ይገኛል።
የብሔራዊ ቡድኑ ካፒቴን ጋቶች ፓኖም ለEthio Fm ለሰይፉ ፋንታሁን በስልክ በሰጠው አስተያየት በደጋፊዎች ዘንድ የዘረኝነት ጥቃት እንደደረሰበት መናገሩ ይታወሳል። በአንጻሩ በስታዲየሙ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች የሰጡት መረጃ ግን ጉዳዩን በተለየ መልኩ ያቀርባል።
ከላይ በቪዲዮ እንደምታዩት ጋዜጠኞች ነተለያዩ አስተያየቶችን በጉዳዩ ዙሪያ እየሰጡ ነው ጋዜጠኛ ዋለልኝ ነጋሽ በጉዳዩ ዙሪያ በስታዲየሙ የነበሩ ሁለት ሰዎችን በስልክ አነጋግሮ እንዳጋራው ከሆነ፣ በወቅቱ በደጋፊዎች በኩል «አትችሉም፣ አርጅታችኋል፣ ሽማግሌ ናችሁ፣ ለወጣቶች ቦታ ልቀቁ» የሚሉ ቃላት ተነግረዋል።
እነዚሁ ምስክሮች ከዚህ የተለየ የዘረኝነት ስድብ እንዳልሰሙ በመግለጽ፣ በተለይም ጋቶችና ከነአን ከደጋፊዎች ጋር በነበራቸው ግንኙነት የተጠቀሙት አንዳንድ ጸያፍ አነጋገር ደጋፊዎችን ይበልጥ እንዳስቆጣ ነግረውኛል ሲል ጋዜጠኛው አትቷል።
በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ዋለልኝ ነጋሽ በጉዳዩ ላይ በሰጠው አስተያየት ዘረኝነት በማንም ላይ ቢፈጸም በጥብቅ ሊወገዝ እንደሚገባው አስገንዝቧል። ከዚህ ቀደም በጋቶች ፓኖም ላይ ብቻ ሳይሆን በኡሞድ ኦኩሪም ላይ ተመሳሳይ አጸያፊ ድርጊት ሲፈጸም በራሱ እንደታዘበ ጠቅሷል።
ሆኖም ጋዜጠኛው ከምስክሮች ያገኘውን መረጃ በመነሳት ጋቶች ከደጋፊዎች ጋር የገባውን ክርክር በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ መፍታት እንደሚገባው የግል አስተያየቱን አቅርቧል።
ግዮን ማለዳ
@GhionMaleda