በድንገተኛ ህመም የተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ህይወት አለፈ!
በኢትዮጵያ የሙዚቃ አድናቂዎች ዘንድ በተወዳጅነቱ የሚታወቀው ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ባጋጠመው ድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት ዛሬ በወልቂጤ ሆስፒታል ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
የድምፃዊው ድንገተኛ ህልፈት ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለሙዚቃ አጋሮቹና ለበርካታ አድናቂዎቹ ከባድ ሀዘንና ድንጋጤን ፈጥሯል።
ሚኪያስ ቸርነት በሙዚቃ ሥራዎቹ በብዙዎች ልብ ውስጥ ስፍራ የነበረው አርቲስት ሲሆን፣ ድንገተኛ ህልፈቱ በሙዚቃው ዓለም ላይ የሀዘን ድባብ ፈጥሯል።
እንዲህ ያለ ድንገተኛ የህይወት ሽኝት ለመቀበል ከባድ ነው። የሰው ልጅ በሥራውና በትዝታው ሲኖር ደግሞ ሞት ቢለየውም በሰዎች ልብ ውስጥ ይቀጥላል።
ለድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ቤተሰቦችና ለመላው አድናቂዎቹ ፈጣሪ መጽናናቱን ይስጥ። ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን! #RIP
ነፍስህን ይማርልን ሚኩ! 💔🙏
ግዮን ማለዳ
@GhionMaleda