በሰው ተፈጥራዊ ቅርፅ ላይ አንድ ነገር ቢጨመርበት እንኳን አያምርም። እንዲሁ አንድ ነገር ቢቀነስ ያስጠላል።
የዓለም ሰዓሊዎችና ዲዛይነሮች ተሰባስበው በሰው ቅርፅ ላይ አንድ የሚያስውብ ነገር እንፍጠር ቢሉ አይችሉም። ወይም ይህ አያስፈልግም ብለው ቢቀንሱ ያስጠላልም፥ እንዲሁም ይበላሻልም።
ሌላው ቀርቶ ከሰው ተፈጥሮ ጋር የማይመሳሰል አዲስ ነገር እንኳን መሳል አይችሉም። ምሳሌ ስላልታወቁ ፍጥረታት (Aliens) የተሰሩ የአሜሪካ ፊልሞችን ካያችሁ ሁሉም ኤሊዬንሶች ከሰው ጋር የሚመሳሰሉና የሆነ ተፈጥሮ የጎደላቸው አስቀያሚ ፍጥረታት ናቸው። የዚህ ምክንያቱ በፊልሞቹ ላይ በርካታ “ጠበብት” ዲዛይነሮች ቢሰባሰቡም ከሰው የተለዬ አዲስ ፍጥረት መቅረፅ ስላልቻሉ ነው።
ይህ የሰው ልጅ በሌላ ሰው ወይም ፍጥረት ሊፈጠር ቀርቶ ሊሳል እንኳን እንደማይችል የሚያሳይም ነው።
አላህ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ቅርፅ እንከን የሌለው የተሟላና የተዋበ እንደሆነ ሲነግረን እንዲህ አለ፦
❝ቀረፃችሁም! ቅርፃችሁንም አሳመረ።❞
(አት-ተጋቡን 3)