☔️ወደ ቀሶሳችን☔️
✍️አንዳንዴ ድክም ምርር ሲልህ ይህ ለምን ሆነ የሚል ወስዋስ ዐቅልህ ላይ ሽው ይልብሓል ነገር ግን ወደ ቁርኣንና ሐዲስ ፊትህን ባዞርክ ጊዜ መሰረታዊና ጦመእኒና የሚፈጥር መልስ ታገኛለህ።
፨ለምን ታሰርኩ ስትል ዱኒያ ለሙእሚን እስርቤት እንጅ ሌላ መች ሆና ታውቃለች የሚል መልስ ታገኛለህ።
✍️እስርቤት መጥፎ ነው።በእረኞች የምትጠበቅ ሰው ትሆናለህ። የእስር ቤቱ ግቢ የኳስ መጨዋቻ ሜዳዋ ላይ ሰውነትህን በወክ እያፍታታህ ባለህበት ቅፅበት ነው እኮ ልክ ሊመሽ አካባቢ ፀሓይ ልትገባ በተቃረበች ጊዜ ግው ግው የሚል የበር ድምፅ ትሰማለህ።ቆጠራ ቆጠራ የሚል ድምፅ በሚኒሚዲያው ይነገራል።ሁሉም በየማጎሪያው በር ጥንድ እየሆነ ይሰለፋል።የማረሚያ ቤቱ እረኞች እየቆጠሩ ያስገቡንና በሩን ክርችም አድርገው ቆልፈውት ይወጣሉ።
✍️ተመልከት በሩን መክፈት አትችልም።በሩን መክፈት እንደማትችል ስታውቅ የስነልቦና ሕመም ያምሓል።
✍️በሩ ተቆልፏል ለይል ብትታመም በር እየወገርክ ድረሱልን ብሎ እረኞቹን ከመጣራት በስተቀር ሌላ አማራጭ የለህም።
✍️እኔ የነበርኩበት ዞን 3 ማለት እኔ በብልፅግና ጊዜ ስታሰር ከእኔ ቀድመው በወያኔ ጊዜ የታሰሩ የድምፃችን ይሰማ ታሳሪ ሙስሊሞች በብዛት የነበሩበት ዞን እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚታሰሩ ዱርየዎች ነግርውኛል።
✍️ቂሊንጦ ዞን 3ከታሰሩ የድምፃችን ይሰማ ታሳሪዎች መካከል የደሴው ጀግና ሙባረክ ይመር رحمه الله ይገኝበታል።
✍️ሙባረክ رحمه الله ለይል ነበር የታመመው አሉ።መክፈት የማትችለው በር ተከርችሞ ወንድምህ ደግሞ በሕመም እያጣጣረ መመልከት ግን እስኪ ከሕሊናችሁ ጋ አስተውሉት✍️ሙባረክ ሆዱን ነበር በጣም የታመመው።እስረኛው የጉረናውን በር በሓይል እየወገሩ ድረሱልን ቢሉም ጥጋበኛው የወያኔ የቂሊንጦ እረኛ ግን ሰምቶ እንዳልሰማ ሆነ።በዚህ መካከል ሙባረክ ሕመሙ በጣም እየጠናበትና እያዳከመው ነበር ወንድሞቹም በሩን በሓይል እየመቱ ቢጮሁም ፖሊሶቹ የደረሱት በጣም ዘግይተው መጡና ምንድን ነው ሲሉ ወንድሞቹ ሰው ታሞብን ነው በማለት ነግረዋቸው በሩ ተከፍቶ ፖሊሶቹ ገብተው ሙባረክን ወደ ሕክምና ለማድረስ ማነው የሚደግፈው አሉ።
✍️ታውቃለህ እስርቤት ቤተሰቦችህ የሉም ፣የቅርብ ጓደኞችህ የሉም።ስትታመም የሚያስታምምህ ስታለቅስ እንባህን የሚጠርግልህ የለም።እዛው እስርቤት ያሉ ሰዎች ናቸው ይህንን ሁሉ የሚያደርጉልህ።
✍️ሙባረክ ግን አብረውት ጎደኞቹ አሉና ተሸክመው ሕክምና ቢያደርሱትም አላህ የፈለገውና የመረጠው ሆኖ ወደ አኼራ ሄደ።رحمه الله وغفر له
✍️አስተውል እስኪ አብሮህ የታሰረ ሙስሊም ወንድምህ እዛው እስርቤት ውስጥ ስታጣው😥
✍️ሙባረክ ጀናዛው ደሴ በገባ ጊዜ እጅግ መሪሪ ሐዘንና ቁጭት ነበር የፈጠረብን። የሙባረክን ጀናዛ አጂበን ወደ ቀብር ቦታ ሄደን አሳረፍነው። አላህ በጀነት ያሳርፈውና።
✍️ሙባረክን ቀብረን ስንመለስ ከቦንቧ ውሓ ደሴ አራዳ የደረሰ የወንድሞቹ የቁጣ ማዕበል ተጥለቅልቆ ነበር።በመጨረሻም በርካታ መከላከያ ጦር ጢጣ መሽጓል ተበተኑ ሁሉም ወደመጣበት ይመለስ የሚል ትዕዛዝ ጥቅምናጉዳቱን ከሚለዩ ሽማግሌዎች በተሰጠን ጊዜ በቁጭት ሁሉም ወደቤቱ በሰላም ተመለሰ።
✍️ያኔ የወያኔ ተቀናቃኝ ኢሳት በየት ቪድዮውን እንደቀረፀው ባላውቅም እረ አንተ ኢሳት ላይ አየንህ ተደበቅ የሚል ስልክ ከየቦታው እየተደወለ አዛ አድርጎኝ ቤተዘመድንም አስጨንቆ ነበር። አላህ የእኔን መታሰር በወያኔ ሳይሆን በብልፅግና ዘመን ነበር የወሰነውና በጊዜው ምንም አልሆንኩም።
✍️ሙባረክ ባለቤቱንና 2 ልጆቹን ለዚህ ኡማ አማና ሰጥቶ ነው ወደ አኼራ የሄደው። 😥እኛ ግን