ይህ የሆነው መካ እንደተከፈተች ነው።አብደላህ ኢብን ሰዕድ ኢብን አቢ-ሰርህ ከሰለመ ቡኃላ ቁርዓንን የመመዝገብ ክብር የተሰጠው ሶሃባ የነበረ ሲሆን ለዲኑ ሲል ወደ መዲና ተሰድዶ እያለ በሆነ አጋጣሚ ወደ መካ ይመለስና እዚያው ሲቆይ ከኢስላም ተቀልብሶ ወጥቶ ወደ ቀደመ ጣዖታዊ ኣምልኮቱ ተመልሶ መካ እስክትከፈት ድረስ ኖረ።ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ድል አድርገው መካን ከፍተው አጠቃላይ ምህረት ሲያደርጉ ጥቂት ሰዎች ይህን እድል ኣገኙም ነበር።ከእነዚያ ሰዎች መካከል አብደላህ ኢብን ሰዕድ ኢብን አቢ-ሰርህ አንዱ ሲሆን መስሊሞች በካዕባ መጋረጃ ላይ ተንጠልጥሎ ቢያገኙትኳ እንዲሰይፉት/እንዲገድሉት ነብዩ (ሰ.ዓ.ወ) ትዕዛዝ አስተላልፈውበት ነበር።
፡
አብደላህ'ም ይህ እንደሚገጥመው ተገንዝቦ ስለነበር በቀጥታ ወደ ኡስማን ኢብን አፋን (ረ.ዓ) በማምራት ከዚህ ጉድ እንዲያወጡት ተማጸናቸው።።አብደላህ እና ኡስማን ኢብን አፋን (ረ.ዓ) የጥቢ ወንድማማቾች ነበሩ።
፡
ኡስማን (ረ.ዓ) አብደላህን ወደ አላህ ነብይ (ሰ.ዓ.ወ) ይዘውት በመምጣት ለደህንነቱ ዋስትና ጠየቁለት።የአላህ ነብይ (ሰ.ዓ.ወ) ግን ለረዢም ሰዓት ዝም ብለው ከቆዩ ቡኃላ በመጨረሻ "ይሁን" አሉ።ይቅርታውን ተቀብለው ዐብደላህ እና ኡስማን (ረ.ዓ) ወጥተው ከሄዱ ቡኃላ የአላህ ነብይ (ሰ.ዓ.ወ) በዙሪያቸው ያሉትን ባልደረቦቻቸውን "ከመካከላችሁ ለረዢም ጊዜ ዝምም ማለቴን ያየ ጮሌ ሰው ተነስቶ አይሰይፈውም/አይገድለውም ነበርን?" አሉ።ባልደረቦቻቸውም በዚህ ጊዜ "የአላህ ነብይ ሆይ! በአይኖችዎ የሆነ ምልክት አያሳዩንም ነበርን?" ሲሏቸው።ነብዩ'ም (ሰ.ዓ.ወ) እንዲህ አሉ ፦ "ነብይ በአይን ጥቅሻ ሰውን አይገድልም።" በሌላ ዘገባ ደግሞ "ለአንድ ነብይ ከዳተኛ አይኖች ሊኖሩት አይገባውም" ማለታቸው ተጠቅሷል።
፡
እዚህ ላይ "ከዳተኛ አይኖች" የተባለው አገላለጽ አንድ ሰው በአንደበቱ የሚናገረው እና በአይኖቹ የሚያሳየው ምልክት ለየቅል ሲሆኑ ነው።ለምሳሌ አንድ ሰው ከአንደበቱ አዎንታዊ ቃላትን እያወጣ በአይኖቹ ግን ከአንደበቱ የማይገጥም ምልክት ሊያሳይ ይችላል።እናም ነብያት እንዲህ እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም ማለት ነው።
፡
ኢብን ሒሻም (አላህ ይዘንላቸውና) እንደፃፉት "አብደላህ ኢብን-ሰርህ (ረ.ዓ) ከዚያ ቡሃላ ጥሩ ሙስሊም መሆን ችሏል።ዑመር (ረ.ዓ) በኸሊፋነት ዘመናቸው በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ያስቀመጡት ሲሆን ኡስማን'ም (ረ.ዓ) በተመሳሳይ መንግስታቸውን እንዲያገለግል ዕድል ሰጥተውታል።" ብለዋል።ኢብን ከሲር (አላህ ይዘንላቸውና) ደግሞ " አብደላህ ኢብር ሰርህ በቤቱ የፈጅር ሰላትን እየሰገደ (ሱጁድ ላይ ሆኖ) ወይም ሶላቱን አጠናቆ ነው የሞተው" ብለዋል።
፡
ለአለማት ዕዝነት - 794-795