ባልና ሚስት ይጣሉና ሽማግሌ ይሰበሰባል። ከዚያም ሁለቱም ችግራችሁን ተናገሩ ሲባሉ ...
ባል፦ "እኔ ከስራ ደክሞኝ ስመለስ ማረፍ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ልጆችን እያንጫጫች አያሳርፉኝም" አለ
ሽማግሌዎቹም "ሌላስ?" ይሉታል
"እኔ ከስራ ስመለስ ልጅ ያዝ ትለኝና ወጥ ትሰራለች። የልጅ ወተት ታፈላለች። ምናለ ሳልመጣ ጨርሳ ብጠብቀኝ ተቀምጣ እየዋለች" ይላል በንዴት።
ሚስትም በሰዎቹ ፊት "ከዚህ በኃላ በፍፁም አንረብሸውም" ብላ ይቅርታ ስለጠየቀች ሽማግሌዎቹ ትተዋቸው ይሄዳሉ።
በነጋታውም ሚስት ልጆቿን ይዛ እናቷ ቤት ሄደች። ከስራ ሲመጣ ቤቱ ተቆልፏል። ልክ ከፍቶ ሲገባ ቤቱ እጅግ ይቀዘቅዛል። ከሰል ለማቀጣጠል ቢሞክር እምቢ አለው። ልብሱን ደራርቦ ሚስት ሰርታ የነበረውን
ጠራርጎ በላ። ዝምታው ሲጨንቀው ቴሌቪዥን ከፍቶ ለማየት ሞከረ ግን የለመደው የልጆቹ ድምፅ ናፈቀው እና እየከፋው ተኛ።
ጠዋት ሲነሳ ያ የሚጣፍጠው ቁርስና የሚወደው የሚስቱ ፈገግታ የለም። ከፋው። ፊቱን ታጥቦ ወደ ስራው ሄደ። ቁርሱንም ውጪ በላ ግን አላረካውም። ቀኑ እንደከበደው ዋለ። ስልኩን ቢያይም አትደውልለትም። ውሎ ሲመለስ ራቱን ውጭ በልቶ ከጓደኞቹ ጋር ቢያመሽም በመጨረሻ ያ ባዶ ቤት ጠበቀው። ለቅሶ ቤት ይመስል መግባት አስጠላው። ዞር ብሎ ሲያስብ ለካ ያለ ሚስቱ ጎዶሎ ነው።
ለካ ልጆቹ ረባሾቹ ሳይሆኑ አጫዋቾቹና የመንፈስ እርካታው ናቸው።
ከዚያ በኃላ "በእጅ የያዙት ወርቅ ሆናችሁብኝ ጥቅማችሁን ስላልተረዳሁ በጣም በድያችኃለሁ። እባክሽ ይቅር በይኝ ውዷ ሚስቴ!" ብሎ በሽማግሌ ታረቃትና በሰላም ኖሩ።
***
መልዕክቱ፦ ሚስቶች ሸክሞች ሳይሆኑ የቤቱ ተሸካሚዎች፣ ሰራተኞች እና አስተዳዳሪዎች ናቸው። ልጆች የቤቱ ሁከት ፈጣሪዎች ሳይሆኑ ደስታና ሙቀት ፈጣሪዎች ናቸው።
ስለዚህ ደስታ የሚሰጠንን ነገር ከማጣታችን በፊት ቀድመን ለይተን አውቀነው ተገቢውን ቦታ እንስጠው ለማለት ነው።