በዚ ሳምንት አንድ ውሳኔ ወሰንኩ ከስልኬ ውስጥ የመፅሐፍ ቅዱስ app አጠፋው ለምን ትሉኝ ይሆናል ምክንያቴን ልትቃወሙኝ ትችላላቹ እኔ ግን አንዴ ወሰንኩ ምክንያቴን ከመናገሬ በፊት ጥያቄ ልጠይቃቹ ስንቶቻቹ ናቹ ከወረቀቱ መፅሐፍ ቅዱስ ይልክ በስልክ ያለውን ምታነቡ? እሁድ ጉባኤ ስትካፈሉ ስልክ ብቻ ይዛቹ በመሄድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም Note በስልካቹ ምትፅፉ? መጽሐፍ ቅዱስን ከመፈተሽ ይልቅ Search በማረግ ጥቅስ ምንጠቅስስ ስንቶች ነን? ከዩሐንስ ወንጌል ቀጥሎ ያለውን እንኳን በስልክ ካሎነ መክፈት ማይችልም አለ እኮ በርግጥ ከሞላ ጎደል ጥቂቱን መልሳቹ ይሆናል ግን ያደግን እየመሰለን ጠፍተናል የወረቀቱን መጽሐፍ ቅዱስ ሳነብ የነበረኝን እውቀትና በስልክ ሲሆን ያጣሁትን ሳመዛዝን የስልኩ ጉዳቱ መዘነ ስለዛ አጠፋሁት እናንተም መለስ ብላቹ አመዛዝኑና እንደፈቃዳቹ አድርጉት በሁሉ ግን ጌታ ይክበርበት ተባረኩልኝ
ኤደን ነኝ
ኤደን ነኝ