መልካም ልደት
ተወልዶ ወለደን ከአብ አስታረቀን
የልጅነት ማዕረግ ወጉንም አሳየን
በበረት ተኝቶ መልካም ልደት አለን
የተፈጥሮንም ህግ በብቃቱ ሽሮ
ተሰምቶ ማይታወቅ ድሮና ዘንድሮ
ከድንግል የአብ ልጅ መወለድ
ባይፈቀድልን በተፈጥሮ መንገድ
ፈጣሪ መሆኑን ገልጦ ሳያብራራ
አድርጎ አሳየት የሰው ህግ ተላላ
የተናቁትንም እረኞች አሰበ
በሜዳ ላይ ሳሉ መዳን አበሰረ
ከበርቴዎች ሄዱ ኮከቡ መርቷቸው
ለአለሙ ንጉስ ስገዱ ብሏቸው
በውልደቱ ወልዶ መዳኒት ከሆነልን
ዛሬ ሆነ የልደታችን ቀን
መልካም ልደት ይሁንልን
እንኳን ተወለዳቹ
በአብ አባት የተወደዳቹ
✍ኤደን አንድሬ
ተወልዶ ወለደን ከአብ አስታረቀን
የልጅነት ማዕረግ ወጉንም አሳየን
በበረት ተኝቶ መልካም ልደት አለን
የተፈጥሮንም ህግ በብቃቱ ሽሮ
ተሰምቶ ማይታወቅ ድሮና ዘንድሮ
ከድንግል የአብ ልጅ መወለድ
ባይፈቀድልን በተፈጥሮ መንገድ
ፈጣሪ መሆኑን ገልጦ ሳያብራራ
አድርጎ አሳየት የሰው ህግ ተላላ
የተናቁትንም እረኞች አሰበ
በሜዳ ላይ ሳሉ መዳን አበሰረ
ከበርቴዎች ሄዱ ኮከቡ መርቷቸው
ለአለሙ ንጉስ ስገዱ ብሏቸው
በውልደቱ ወልዶ መዳኒት ከሆነልን
ዛሬ ሆነ የልደታችን ቀን
መልካም ልደት ይሁንልን
እንኳን ተወለዳቹ
በአብ አባት የተወደዳቹ
✍ኤደን አንድሬ