🙏🙏🙏❤️❤️❤️
#መልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ !!!
#የአራተኛው መልክ ደግሞ የአማልክትን መልክ ይመስላል
ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር በባቢሎን ምርኮ የወሰዳቸው የእግዚአብሔር ሰዎች አናንያ፤ አዛርያ፤ ሚሣኤል እጅግ ይወዳቸው ነበር፡፡
ከባቢሎናውያን ይልቅ ጠቢባን የነበሩት ሶስቱ ሕጻናት በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ሦስት ሰፍሮ በምናገኘው ታሪካቸው እንደሚግረን ንጉሱ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሳት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር።
ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻላል?" ቢላቸውም የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል፣ ባያድነንም ግን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም" አሉት፡፡
በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሳት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሳቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠለስቱ ደቂቅን ግን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው።
በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል፤ የአራተኛው መልክ ደግሞ የአማልክትን መልክ ይመስላል" አለ።
የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ይስገድ ተብሎ የነበረው አዋጅ ተሽሮ "ጉልበት ሁሉ ለሰለስቱ ደቂቅ አምላክ ይስገድ ይንበርከክ" የሚል አዋጅ ታወጀ፡፡
ይህ ድንቅ ተአምር የተገለጠበት ቀን ታህሳስ 19 የታላቁ አለቃ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው፡፡
የስሙ ትርጓሜ ታማኝ አገልጋይ ማለት የሆነው ቅዱስ ገብርኤል በዘመናችንም ለበርካቶች ታላቅ ተአምራት ሰርቷል፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ፤የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው ረድኤት በረከቱ አይለየንና ገዳማውያን አባቶችና እናቶች እንደ ባቢሎን እሳት በነደደው ስጋዊ ፍላጎት ውስጥ አሸናፊ እንዲሆኑ የሚረዳቸውም ነው፡፡ ገዳማውያኑ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሲሉትም በረከታቸው አብሮን እንዲሆን ገዳማቸውንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴
https://www.facebook.com/share/p/15v1ikPqqj/?mibextid=wwXIfr