🙏🙏🙏
#ያዩ አይኖቻችሁ፣ የሰሙ ጆሮቻችሁ ብጹዓን ናቸው
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ምስጢር በሚከናወንበት ስርዓተ ቅዳሴ ወቅት ቅዱስ ወንጌል ከመነበቡ በፊት ዲያቆናቱ ለምስባክ ሲወጡ ሰራኢው ካህን ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋርያት የተናገረውን "ብዙ ነቢያት ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ፈለጉ አላዩም፣ ዛሬ እናንተ የምትሰሙትን ሊሰሙ ወደዱ አልሰሙም፤ የእናንተ ግን ይህን ያዩ አይኖቻችሁ፣ የሰሙ ጆሮቻችሁ ብፁዓን ናቸው። (ማቴ.13፥16) ይላሉ።
ብዙ ነቢያት ጻድቃን ለማየት ፈልገው ያላዩት፣ ሊሰሙ ፈልገው ያለሰሙት ምን ነበር? ከዐበይት እስከ ደቂቀ ነቢያት የጌታችንን ሰው መሆንና ማዳን በመንፈስ ቅዱስ ተቃኘተው፣ በትንቢት መነጽር ተመልክተው ቢናገሩም ማዳኑን በዘመናቸው አላዩም፣ ይህ ድንቅ ምስጢር ፈጥኖ እንዲገለጥ አቤቱ ጌታችን ሆይ ውረድ፤ ተወለድ፤ አድነን›› እያሉ ይጾሙ ይጸልዩ ነበር።
ቅዱሳን ሐዋርያት ግን ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዋለበት እየዋሉ ባደረበት እያደሩ በቃልና በተግባር ሲማሩ ኖረው፣ ማዳኑን አይተው ለአባቶቻችን፣ አባቶቻችንም ለእኛ ገለጡት።
እኛም የቅዱሳን ሐዋርያትን ዓይን፣ ዓይን አድርገን አየነው ዳሰስነው፣ ከእርሱም ጋራ በላን ጠጣን እንዲል አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም፣ የጌታችንን ማዳን አምነን ተቀብለን ስጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን ልጅነትን እናገኛለን፣ መንግሥቱንም እንወርሳለን።
ታዲያ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳን ነቢያትን ጾም ከሰባቱ አጽዋማት እንዱ እድርጋ ከህዳር 15 እስከ ታህሳስ 29 እንደንጾም ለምን ታደርጋለች? ነቢያት የተናገሩለት፣ የማዳን ሥራ ተፈጸመልን፣ ወርዶ ተወልዶ አዳነን ስንል እንጾማለን። ላመነውም ማዳኑን ያዩ አይኖቻችን፣ የሰሙ ጆሮቻችንም ብጹዓን ናቸው።
ጾም በስጋም ብነፍስም በርካታ በረከት እንድናገኝ የሚረዳ ትልቅ መሳሪያ ነው። በነፍሳችን መንግስተ ሰማያት የምንወርስበት፣ የጠላትን ኃይል የምንደመስስበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት፣ ንስሐችንን የምንፈጽምበት ኃጢአታችን የሚሰረይበት ነው። በስጋችንም የጾም በረከት እጅግ በርካታ ነው።
ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የደምና የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር ፣ የስብ ክምችትን ለመቀነስ፣ የአንጎላችንን እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ፣ የካንሰር ሕዋሳትን እድገት ለመከላከል፣ ወቅት የመከላከል አቅም እንዲዳብርና፣ ለቆዳ ጥራት ጭምር ትልቅ እገዛ አለው።
ጾም የቃሉ ትርጉም መከልከል ማለት ነውና በጾም ወቅት አእምሯችንንና ሰውነታችንን ከስጋ ስራ ማቀብ በነፍስ መንገድ መመላለስ ይገባል። የተራቡ የተጠሙ ወገኖችን መዘከር፣ በጸሎት መትጋት፣ ቅዱሳን መካናትንና ገዳማውያን አባቶችን ማሰብ ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ ትልቅ ተግባር ነው።
ወደ ቅዱሳን መካናት ስንሔድ፣ ገዳማውያኑን ስናግዝ ልዩ በሆነው ጸሎትና ቡራኬያቸው እንቀደሳለን።
ጾመ ነቢያት በረከት የምናገኝበትን የነፍስ ስራ እንስራበት።
ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴
https://www.facebook.com/share/p/14TRWhZvfi/?mibextid=WC7FNe