የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ ሰፊውን ህብረተሰብ እንዲያካትት በማሰብ የአነስተኛው ድርሻ (33 አክሲዮኖች) ዋጋ 9 ሺህ 900 ብር እንዲሆን ተደርጓል - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
**********
መንግሥት ከአፍሪካ ቀደምትና ፈር ቀዳጅ የቴሌኮም ኩባንያ የሆነውንና ባለፉት 130 ዓመታት ታላቅ ሀገርና ህዝብን በማገልገል ላይ የሚገኘውን የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ የባለቤትነት ድርሻን ለኢትዮጵያውያን ለመሸጥ መወሰኑን ተከትሎ አስፈላጊው ሂደት ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአክሲዮን ሽያጩን በይፋ አስጀምረዋል።
በዚሁ መሰረት 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለኢትዮጵያውን ከዛሬ ጀምሮ በቴሌብር ሱፐርአፕ ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን፤ አክሲዮን ሽያጩ ሰፊውን ህብረተሰብ እንዲያካትት በማሰብ የአነስተኛው ድርሻ (33 አክሲዮኖች) ዋጋ 9 ሺህ 900 ብር፣ በማድረግ የከፍተኛው ድርሻ (3,333 አክስዮኖች) ዋጋ ደግሞ 999,900 ብር እንዲሆን መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው ጽሑፍ አብራርቷል።
በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በነገዋ ሀገራችን ልዩ የኢንቬስትመንት ዕድል ተጠቅመው በአገሪቱ ካሉት ግዙፍ ተቋማት መካከል የአንጋፋው ኩባንያ ባለአክሲዮን እንዲሆኑ እና የኢትዮ ቴሌኮምን ቀጣይ ዕድገት እንዲደግፉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውቋል።
#invest #habesha @habeshaDiasporaUSA