በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም እንዲለዩ የተላለፈ ጥሪ - call for community diagnosis and early referral of Familial Hypercholesterolemia
በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም (የፋሚሊያል ሃይፐርኮሌስትሮሌሚያ, Familial Hypercholesterolemia, FH) በጣም ከፍተኛ የኮሌስትሮል መብዛት የሚያመጣና ለልብ ህመም የሚያጋልጥ የተለመደ በዘር የሚወረስ በሽታ ነው። ሮጠው ያልጠገቡ ልጆችን እና ወጣቶችን በልብ ህመም የሚያሰቃይ ህመም ሲሆን በጊዜ ካልታከመ ገዳይ በሽታ ነው።
በአለም አቀፍ ደረጃ ከ300 ሰዎች አንዱን እንደሚያጠቃ የተረጋገጠ ሲሆን በዘር ከሚወረሱ የሜታቦሊክ ህመሞች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። በሃገራችን ኢትዮጵያም ይህ በሽታ እንዳለ ማረጋገጫዎች ቢኖሩም የህመሙን ስፋት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን ሊይዝ እንደሚችል ከመገመት ውጭ በውል አይታዎቅም።
ይህንን አስከፊ ህመም ለማከም እያንዳንዱ ሰው ማገዝ ይችላል! እንዴት ቢባል የህመሙን ምልክቶች በራስ፣ በቤተሰብ አባላት፣ በጓደኞች ወይም በስራ ቦታ ላይ በመመልከት እና በመለየት ለትክክለኛ ምርመራ እና ህክምና ወደጤና ተቋም እንዲሄዱ በማበረታታት ህይወት አድን ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።
ማንም ሰው ሊያያቸው የሚችላቸው የህመሙ ምልክቶች እነዚህ ናቸው፡
1️⃣ በቆዳና ጅማት ላይ የሚወጡ ቢጫማ እብጠቶች (xanthoma) ዋነኛ የህመሙ ምልክቶች ናቸው። እነዚህ እባጮች በቁርጭምጭሚት አካባቢ የተረከዝ ጅማት (ቋንጃ) ላይ፣ በጉልበት፣ በእጆች ወይም ክርን ላይ ሊወጡ ይችላሉ። በአይን ዙሪያም (xanthelasma) ሊወጡ ይችላሉ። እነዚህ እብጠቶች በቀላሉ የሚታዩ ቀለማቸው ቢጫማ ሲሆን ኮሌስትሮል በቆዳና ጅማት ውስጥ ሲከማች የሚመጡ ናቸው።
2️⃣ የአይን መስታውት ዙሪያ ላይ የሚወጣ ቀለበቶች (arcus cornealis) ሌላኛው የኮሌስትሮል ህመም መገለጫ ሊሆን ይችላል። ይህ ነጭ ወይም ግራጫ ቀለም ያለው ክብ መሰል ሲሆን ኮሌስትሮል በአይን መስታወት ዳርቻ ላይ ሲከማች የሚፈጠር ነው። በአብዛኛው በአረጋውያን ላይ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚታይ ሲሆን ከ45 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ ሲታይ የኮለኢስትሮል ህመም ምልክት ነው።
3️⃣ ከቤተሰብ አባላት ውስጥ በወጣትነታቸው ከ50 አመት እድሜ በፊት ድንገተኛ የልብ ድካም (heart attack) ወይም ስትሮክ (stroke) ያጋጠመው ካለም እንዲሁ የዚህ የኮሌስትሮል ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።
4️⃣ ለሌላ አጠቃላይ የጤና ምርመራ ሲሰራ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መብዛት ከተገኘም እንዲሁ የፋሚሊያል ሃይፐርኮሌስትሮሌሚያ ሊሆን ይችላል።
ይህን ህመም ማወቅና ተጠቂዎችን በቶሎ መለየት ለምን አስፈለገ?
በቅድመ ምርመራ፣ ትክክለኛ ህክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ይህ በዘር የሚወረስ የኮሌስትሮል ህመም ያለባቸው ሰዎች ረጅም እና ጤናማ ህይወት ሊመሩ ይችላሉ። እነዚህን ቀላል ምልክቶች በማወቅ በማህበረሰባችን ውስጥ የዚህ ህመም ተጠቂዎችን የልብ ድካም ሳይዛቸው አስቀድሞ መታከምና መከላከል ይቻላል።
በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም በመለየት በወጣትነት የሚመጣን የልብ ድካም ለመከላከል የሚደረገውን ሃገራዊ ጥረት እናግዝ። ይህን ማድረግ እንዲያስችለን በሚኖሩበት፣ በሚሰሩበት ከባቢ ውስጥ የፋሚሊያል ሃይፐርኮሌስትሮልሚያ (FH) ምልክቶችን ይወቁ! ለሌሎችም ያሳውቁ።
ይህንን መረጃ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ እና ከጎረቤት ጋር ያካፍሉ።
ተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም ግብረ መልስ ካሉዎት የዚህን መረጃ ያሰናዳዉን ዶ/ር መላኩ ታዬ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳር ህክምና ክፍል ማግኘት ይችላሉ።
ተግባራዊ የጤና ምክሮችን በዶ/ር መላኩ ድህረ ገጽ www.melakutaye.com እና ማህበራዊ ሚዲያዎች @hakimmelaku ይከታተሉ!
telegram https://t.me/hakimmelaku
write me feedback at https://maps.app.goo.gl/twmS9fq7LiG1eRnq9
WhatsApp/Telegram consults at +251921720381
Dr. Melaku Taye (Endocrinologist, Lipidologist)
Get social with Hakim on Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207
@HakimEthio