ጃፓኖች ሁሉም ነገር ላይ እጅግ ስነ ስርዓት አላቸው ይባላል። በቀደመ ህይወቴ ጃፓናዊ ነበርኩኝ መሰለኝ እኔም ስርዓት አበዛለሁ።😄 በእርግጥ የኔ የጤና አይደለም። በፀበልም በፀሎትም የማይድን OCD (Obsessive Compulsive Disorder) አለብኝ። የችግሩ አንደኛው ምልክት ነገሮች ሁሉ በስርዓት እንዲደራጁ አለቅጥ መሻት ነው። እኔም የሚታይብኝ ይሄኛው ምልክት ነው።
የተዛነፈ ነገር ማዬት አልችልም። የማላውቀው ሰው ኮሌታ ራሱ ካልተስተካከለ እጄን ይበላኛል። የምግብም ይሁን የቡና ሱፍራ ዘርፍ አሁንም አሁንም ሳስተካከል፣ ሲኒ ሆነ ብርጭቆ በልክ ስደረድር፣ ምንጣፍ ለማንጠፍ መስመር ሳሰምር ላዬኝ ድሮዊንግ ተጨንቆ እዬሰራ ያለ ሲቪል ኢንጂኒዬር ነው የምመስለው።
የተዝረከረከ ነገር አልወድም። አልጋ ሳነጥፍ ውጥር አድርጌ ነው። መጅሊስም ይሁን ፍራሽ ሰው ተቀምጦ በተነሳ ቁጥር ነው የማስተካክለው። ጫማ ሲቀመጥ ከተንሻፈፈም ከተደራረበም ተነስቼ አስተካክላለሁ። ደርቆ የገባ ልብስ ቶሎ ካልተጣጠፈ የሆነ የተሸከምኩት ነገር ያለ እስኪመስለኝ ነው የሚከብደኝ። ያልተተኮሰ ልብስ በተዓምር አልለብስም።
ልብሴ ላይ ትንሽ ጠብታ ነገር አርፎ ማስወገድ ካልቻልኩ ትኩረቴ እዛ ላይ ሆኖ ይውላል። አብሮ የማይሄድ ወይም ከላይም ከታችም የተዥጎረጎረ አለባበስ ያቅለሸልሸኛል። ዲዛይነር ብሆን የሚዋጣልኝ ይመስለኛል። የብር ኖት የባንክ ሠራተኛ እንኳን እንደኔ አያስተካክልም። ፅሁፍ ላይ ግድፈት እንዳይኖር በጣም እጠነቀቃለሁ። አለቆች ትንሽ ካወቁኝ በኋላ "መቼም አንቺ አትሳሳቺም" እያሉ ሳያነቡ መፈረም ይጀምራሉ። እምነታቸው በበሽታዬ ላይ ኃላፊነት ያሸክመኛል።
🤦♀️ እንኳን ቢሮ ፌስቡክ ላይም ስፅፍ የአንዲትም ፊደል ስህተት አልፈልግም። ለአፃፃፉ ግድ የሌለው ሰው ራሱ ይገርመኛል። የቢሮ ጠረጴዛዬ ላይ አንዲት ወረቀት ያለ አግባብ አትገኝም።
ፎቶ ሳነሳ ባለሙያ ይመስል አንግል፣ ሴንተር፣ ፎከስ እላለሁ። የተጣመመ ፎቶ የማይረብሻቸው ሰዎች ታድለው። የምቀርፃቸውን የኸሚስ ቪድዮዎች ያዬ አንድ ጓደኛዬ እንደውም እንቅስቃሴ ካለመኖሩ የተነሳ በስታንድ ካሜራ ነው ወይ የምትቀርጪው ብሎኛል። ለነገሮች ውበትና Details ስጨነቅ አርክቴክት ይቀናብኛል።
ሲበዛ ቀጠሮ አከብራለሁ። ሌላው ቀርቶ ፖስት ራሱ በተሸራረፈ ሰዓት መፖሰት አልወድም። 1 ሰዓት 5 ሰዓት እንደዛ። የአንድ የሁለት ደቂቃም ልዩነት አልፈልግም። በምንም ነገር ፐርፌክሽን ያስደስተኛል። ግድየለሽነት፣ ቸልተኝነት ያናድደኛል። የቱንም ያክል ቢበዛ ከቢሮ ሥራ ጨርሼ ነው የምወጣው። ካልሆነ ልቤ እዛው ተንጠልጥሎ ነው የሚያድረው። ልሠራው ያሰብኩት 5 ነገር ኖሮ አንዱ እንኳን ከጎደለ ይደብረኛል። ጓደኞቼ "ሞራልሽ የወታደር ነው!" ይሉኛል። አቡዳቢ እያለሁ ጂም ከሌሊቱ 7 ሰዓት ሊዘጋ እኔ 6 ሰዓት ሄጄ አውቃለሁ። ምክንያቱም ቀድሜ አስቤዋለኋ።🤣 ያሰብኩትን ነገር ካልፈፀምኩ የአዕምሮዬ መንገድ ይጨናነቃል። የሰውም ጉዳይ ቢሆን ሳላሳካ መተው አልችልም። በነገራችሁ ላይ ይሄ ችግር ቀላል እንዳይመስላችሁ። በዚህ ሰበብ የፈረሱ ትዳሮች ሁሉ አሉ። ደግነቱ እኔ እየመረረኝም ቢሆን ራሴ አስተካክላለሁ እንጂ ሰው አልጫንም። ቢያመኝም ቢደክመኝም ለዚህ ሲሆን አልሰንፍም። ምናልባት ልጆች ሲኖሩኝና ቤቱን እያመሳቀሉ ጢምቢራዬን ሲያዞሩት እንደ ኩፍኝ ካልወጣልኝ በቀር ነገርዬው በዋዛ የሚተውም አይደለም። ለማንኛውም መስመር የያዘች ቅድዬ ተመኘሁላችሁ!
ፏ_ያለች_ቅድዬ!♥♥♥
By: Atiqa Ahmed Ali
@HakimEthio