የረመዳን ፆምና የስኳር ህመም ህክምና
• የጤና ባለሞያና የስኳር ህመም ታካሚ የስኳር ህመምን ባህሪን በአግባቡ በመረዳትና በመመካከር የረመዳ ፆምን በጡሩ ሁኔታ መፆምና እንድሁም የስኳር ህመም የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል።
መፆም የሚችሉ የስኳር ህመም ታካሚዎች
• ዓይነት 2 የስኳር ህመም ያላቸውና
1. በአመጋገብና በአኗኗር ዘይቤ ስኳር መጠናቸውን የተቆጣጠሩ
2. በሚዋጡ ፣ በአፍ በሚወሰዱ መድሃኒቶች የተቆጣጠሩ
3. በመሠረታዊነት ኢንሱሊን የሚጠቀሙና ቢያንስ ለ 2 ወር በጡሩ ሁኔታ የስኳር መጠናቸውን የተቆጣጠሩ
• ዓይነት 1 የስኳር ህመም ያላቸውና በጡሩ ሁኔታ የስኳር መጠናቸውን የተቆጣጠሩ፣ ከሀኪማቸው ጋር በመገናኘት አስፈላጊውን ማስተካከያ መውሰድ የሚችሉ።
የስኳር ህመም አመጋገብ በረመዳን ፆም
• ስሁር በአግባቡ መመገብ አለብዎት።
• በተቻለ መጠን ስሁርን አዘግይተው ይመገቡ።
• ከኢፍጣር አዛን በኋላ በፍጥነት ወዳውኑ ማፍጠር አለብዎት።
• ኢፍጣር ላይ የቴምር መጠን ይገድቡ ( 2 ወይም 3 ፍሬ ቴምር ብቻ ይጠቀሙ።
• ዝቅተኛ የስኳር መጠን ጠቋሚ ( low glyceamic index) ያላቸውን ምግቦች ይመገቡ :-
• ነጭ ጤፍ፣ ቀይ ጤፍ ፣ የገብስ ዳቦና እንጀራ
• ፍረሽ / ትኩስ ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶችና፣ ሰላጣዎች፣
• የአጃ ና የገብስ ሾርባ ፣
• ቅርፊት ያላቸው ጥራጥሬዎች:- ባቄላ፣ አተር፣ ምስር፣
• ከኢፍጣር እስከ ስሁር ድረስ ብዙ ውሃ ይጠጡ
• (ቢያንስ 8 ብርጭቆ ዉሃ) ይጠቀሙ።
አለመመግብ ወይም መቆጠብ ያለብዎት ምግቦች
1. ቅባት ወይም ጮማ የበዛብት ምግብ አይጠቀሙ።
2. ስኳር የተጨመረበ ምግብም ሆነ የታሸገ መጠጥ አይጠቀሙ
3. የተጠበሰ ምግብን ያስወግዱ ( ሳንቡሳ፣ ዶናት፣ ኩኪስ ) አይመገቡ።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተመለከተ
• ፈጣን እርምጃ ወይም የእግር ጉዞ ማድረግ ይችላሉ።
• የተራዊህ ( የለይል ሰላት ) እንደ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይጠቀሙ።
• ከሰዓት በሗላ ወደ ማፍጠሪያ ሲቃረቡ
• ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይመከርም።
• አድካሚና ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ ስራ አይስሩ።
• እንቅስቃሴዎችን በመደበኛነት የሚያደርጉ ከሆነ ከእንቅስቃሴ በፊትና በሗላ የደም ውስጥ የስኳር መጠንዎን ይለኩ።
• የስኳር መጠንዎ ከ 70 በታች ከሆነ ፆምዎትን ይፍቱ፣ ያፍጥሩ።
የስኳር ህመም መድኃኒት አጠቃቀም
• በጾም ሰዓታት በዓፍ የሚዋጡ የስኳር መድኃኒቶች ጾምን ያበላሻሉ።
• በቀን አንድ ጊዜ የሚዎሰዱ የስኳር ህመም መድኃኒቶች ኢፍጣር ላይ ይውሰዱ።
• በቀን ሁለት ጊዜ የሚዎሰዱ የስኳር ህመም መድኃኒቶች ኢፍጣርና ስሁር ላይ ይውሰዱ።
• የተለያየ መጠን ያላቸው መድሃኒቶች ካሉዎት ትልቁ መድሃኒት ኢፍጣር ላይ ቢወሰድ ይመከራል።
• በረመዳን ወቅት ለዝቅተኛ የስኳር መጠን የማጋለጥ እድል ያላቸው መድሃኒቶች አይመከሩም።
• ኢንሱሊን እሚወስዱ ከሆነ ከረመዳን በፊት ጧት እሚዎስዱት የነበረውን ኢፍጣር ላይ እንድሁም ማታ እሚውስዱት የነበረውን ስሁር ላይ ማድረግና መጠኑን መቀነስም ሊያስፈልግ ይችላል።
የረመዳን ፆምና የስኳር ህመም ህክምና ግብ
• የስኳር መጠን ከኢፍጣርና ከስሁር በፊት ከ 90 - 130 ማድረግ ነው።
• የስኳር መጠን ከ 70 በታች ወይም ከ 300 በላይ ከሆነ ፆምዎትን መፍታትና ለቀጣይ ቀናት ከሐኪምዎት ጋር በመመካከር ለስኳር መጠንዎ በጣም ከፍ ማለትና ዝቅ ማለት መንስኤውን መለየትና መፍትሄ ማስቀመጥ።
ማሳሰቢያ :- የስኳር ህመም ካለብዎት የረመዳን ፆም መፆም ሲያስቡ ቅድሚያ ከሐኪምዌት ጋር ይምከሩ። እንድሁ የአመጋገብ ሁኔታ፣ የመድሃኒትዎን አወሳሰድ ማስተካከልና የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችን ከሐኪምዎት በቂ ግንዛቤ ይውሰዱ።
References
- IDF-DAR Guideline 2021
- American Diabetes Association 2025
- Australian Diabetes Society 2020
ዶ/ር ሙሃመድ የሱፍ: የውስጥ ዴዌ ስፔሻሊስት
@HakimEthio