ሒጃብ ነው ውበቴ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


السلام عليكم وراحمة الله وبركاته
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በአላህ ፍቃድ
* ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች
* አስተማሪ ታሪኮች
* ዲናዊ ትምርቶች
* ምክሮች
* ደዐዋወች
ይቀርብበታል ኢንሻአላህ
ማንኛውንም አስተያየት ለማድረስ
@Khewlibot
አላህ ዱኒያዬንም አሄራዬንም
እንዲያሳምርልኝ ዱዐ አርጉልኝ
👇👇👇Join
t.me/HijabNewWebta

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter




Video is unavailable for watching
Show in Telegram




☝️☝️ሳዑዲዎች !! እንግዳችሁን ተቀበሉት እንጂ !
   ከቻላችሁ በቀጥታ ደውላችሁ
እንደዛ ካልቻላችሁ በኔ በኩል አሳውቁኝ
@Fo1249  ስራ ካለ የሱ username  በውስጥ እሰጣችኋለሁ   ኑ ሀቂቃ ወንድማችን ገና የሳዑዲን ምድር የረገጠው በዚሁ አመት ነው  ተቸግራችሁም ቢሆን ፈልጉለት


Forward from: الشباب السلفيين
ስራ ፈልጉልኝ ቤተሰብ

በተለይ.. መካ ፣መዲና፣ጂዳ ያላችሁ

👉ከተገኘ ሪያድም ቢሆን እመጣለሁ።
http://t.me/nuredinal_arebi


🔠🔠🔠🔠

  

    

      
   ረ 

ገባ ገባ በሉ


🖋ርዕስ    ✅ኹሹዕ ፊ ሰላህ ⚫️

🎙አቅራቢ ፦✅ ከማል አህመድ ✅

የሚተላለፍበት ሊንክ

⬇️
t.me/tdarna_islam?livestream
t.me/tdarna_islam?livestream


🛜ዛሬ እና ነገ የሚደረጉ የዳዕዋ ፕሮግራሞች

ዛሬ ምሽት በትዳር እና ኢስላም ቻናል

t.me/tdarna_islam/4730
t.me/tdarna_islam/4730

ዛሬ ምሽት በኢብኑ ተይሚያህ ቻናል
⚫️
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13943
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13943
⭐️
ነገ እለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
በደሴ ከተማ
🌟
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/19805
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/19805

🛜ከላይ ባለው ልንክ እየገባችሁ ሙሉ ተጋባዥ እንግዶች እና ርዕስ አንብቡ✅


أَلَّا تَطْغَوْا فِي الْمِيزَانِ
(ሱረቱ አል ረሕማን - 8)
በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡


وَأَقِيمُوا الْوَزْنَ بِالْقِسْطِ وَلَا تُخْسِرُوا الْمِيزَانَ

(ሱረቱ አል ረሕማን - 9)
መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡
=


የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲሱ  ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው  ✅
በሀገር ውስጥም ይሁን ካሀገር ውጪ ያላችሁ
የሱና ወንድም እና እህቶቻችን 
ይህ ቻናል ይጠቅማችኋል ተቀላቀሉ
👇
join request የሚለውን በመጫን✅️
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0


Forward from: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
☀️አንዳንድ ሙስሊም ወገኖች አሉ!!

አንዳንድ ሙስሊም እህትና ወንድሞች ስለ #ኒቋብ ያላቸው አመለካከት የዘቀጠ ነው። ይህም ሳይበቃቸው ስለ ኒቃብና ስለ ሙተነቂቦች የሚያወሩበትን ቦታ አያውቁም። ከዙሪያቸው ካፊሮች ባሉበት ለኒቃቢስቶች ያላቸውን ጥላቻ ያወራሉ።

ሀቂቋ ይህን ያልኩት ስላጋጠመኝ ነው። ሙስሊሟ እንዲህ ካለች እነሱ ካፊሮቹ ምን ሊሉ ነው ????

ሙተነቂቦችም እኮ  ተሳሳቾች ናቸው ስህተት ካያችሁ በአደብ ማረም አለዚያ ደግሞ የማያውቁትን ከማውራት መቆጠብ ነው።


የታደሉ እግሮች ገና ከማለዳው  ከግቢያቸው ወጥተው ወደ የትም ከመራመዳቸው በፊት ወደ አላህ ቤት ይራመዳሉ/ ያቀናሉ የእለቱ የእንቅስቃሴ ጅማሬያቸው መስጅድ ነው
يـــــــــــــــــــا سلام
ምንኛ መታደል ነው!


የምር አንዳንዴ  ፈጅር አዛን ሲል ያለው ድባብ ሳይ  ምነው ወንድ በሆንኩኝ እላለው።

ያለ ምንም ኡዝር ፈጅርን ተኝታችሁ  አሳልፋችሁ  ከረፈደ በኋላ እቤታችሁ  እምትሰግዱ ወንዶች ካላችሁ በእርግጥም የፈጅር ሶላትን ጣዓም አታውቁትም።


እናማ ነቃ በሉ ማለቴ ጀግና  ወንድሁኑ ከአዛኑ
በፊት ቀድማችሁ አወል ሶልፍ ላይ ተገኙ አዛን
ለማውጣትና ኢማም ሁኖ ጀማዓውን መርቶ ለማስገድ ተሽቀዳደሙ ስላቹ ነው  ይህ ነው
ጀግንነት ጡንቻ ብቻ ማፊ ፋዒዳ ተማም👌

🌸────⊱◈◈◈⊰───🌸


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


የነቢዩ ባልደረቦች የሰውነታቸው ጠረን እስኪቀየር ድረስ ይሰሩ ነበር ! ለዱንያ መስራታቸውና ሰርተው ማግኘታቸው ግን ለአኺራ ከመልፋት አያግዳቸውም ነበር
ኡስታዝ ሙሓመድ ሲራጅ
@HijabNewWebta


እሱ በሱ ላይ መልካም ያሰቡትን ፣ በሱ የተመኩትን፣ በሱ ላይ ተሰፋ የጣሉትን ሁሉ አያሳፍራቸውም።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
t.me/HijabNewWebta


Forward from: ኢህሳን Advertising
📣የትኛውም የስራ ማስታወቂያ ሲኖር
በእነዚህ username ሹክ በሉን
👇
1️⃣ @twhidfirst1
🐽@Tolehaaaaaa
ማሳሰቢያ🔻 ምንም አይነት ክፍያ አንጠይቅም።
- ስለ ስራው ግን እናጣራለን አጣርተን ቀጥታ በቻናሉ እንለቃለን ✅

🔗ሼር በማድረግ አሰራጩት
የስራ ማስታወቂያ የሚለቀቅበት ቻናል
👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0


ስጋት!!ጭንቀት !!ሽብር    ዱ ኒ ያ እንዲህ ናት  ...

ተማሪው እወድቅ ይሆናል ብሎ ሊወድቅ ይደርሳል
ተመራቂው ሥራ አላገኝም ብሎ ይሸበራል
አባት ልጆቼ በርሃብ ሊያልቁብኝ ነው ብሎ ይብሰለሰላል

በዕድሜ የገፋው በሽታ ሊጥለኝ ነው ብሎ ይሰጋል
ኮረዳዋ  ሳላገባ ዕድሜዬ ገፋ ብላ  ትጨነቃለች
ወጣቱ ከምንም ሳልሆን ጊዜው ሄደ ብሎ ይደነግጣል

እናት ልጄን ክፉ ያገኘዋል ብላ ትቆዝማለች
ነጋዴው እከስር ይሆናል ብሎ ይንቀጠቀጣል
ኪሣራ  ዉድቀት በሽታ እንቅፋት ሐዘን ፍርሃት ስጋት

ሽብር  ትካዜ  ከጥንት ጀምሮ የዚህ ዓለም መገለጫዎች ናቸው ዱንያ አላህ ሲፈጥራት ቀድሞውኑ እንዲህ ናት!!!

አብሽሩ

ነገሮች
#አላህ ካለው ልክ ላያልፉ
ማሰብ መጨነቅ ምንድነው ትርፉ??✅


Forward from: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
ከአላህ ፍራቻ አንፃር ዐይናችን እንባ ከቋጠረች ሰላም ነን።

የደረቀች እንደሆነ ግን አደጋ ላይ ነን።✅


ቅድሚያ ለኣኺራ
~
ሐሰኑል በስሪይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"ሁሉም ፀጋ ጠፊ ነው፣ የጀነት ሰዎች ፀጋ ሲቀር።
ሁሉም ሃሳብ አላፊ ነው። የእሳት ሰዎች ሃሳብ ሲቀር።"
[አልሙጃለሰህ ወጀዋሂሩል ዒልም፡ 19]
@HijabNewWebta
@HijabNewWebta


Forward from: ኢህሳን Advertising
⚙ይህ ቻናል በሀገር ውስጥ ያሉ ስራ አጥ
            ወንድም እህቶች
በአላህ ፍቃድ  የስራ ማግኛ ሰበብይሆን ዘንድ
ታስቦ የተከፈተና የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲስ ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው  ✅

🔗ተቀላቀሉ ✅
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0

20 last posts shown.