#ክፍል_12
الحديث الثالث عشر
#13ኛው_ሐዲሥ፡ #ለራስ_የሚወዱትን_ለወንድም
#መውደድ
عَنْ أَبِي حَمْزَةَ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه خَادِمِ رَسُولِ اللَّهِ ﷺ عَنْ النَّبِيِّ ﷺ قَالَ: "لَا يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لِأَخِيهِ مَا يُحِبُّ لِنَفْسِهِ". رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ، وَمُسْلِمٌ.
የአላህ መልእክተኛ ﷺ አገልጋይ ከነበሩት አቡ ሐምዛ አነስ ኢብኑ ማሊክ رضي الله عنه ተይዞ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "#አንዳችሁ_ለወንድሙ #የሚወደውን_ለራሱ_እስካልወደደ_ድረስ_አላመነም (#እምነቱ_አልተሟላም)።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። [13] [45]
#ማሳሰቢያ፦
ሐዲሡ በሌላ ዘገባ ላይ "#አንዳችሁ #ከመልካም_ነገር_ለወንድሙ_የሚወደውን_ለራሱ #እስካልወደደ_ድረስ_አላመነም" በሚል መልኩ ነው የተላለፈው። [ነሳኢይ፡ 5017] ስለዚህ የተፈለገው መልካም የሆነን ነገር ስለመውደድ ነው። እንጂ ብልሹ የሆነ ሰው ለራሱ የሚወደውን ክፉ አመል፣ ሱስ፣ ጥፋት፣ ... ለወንድሙ ቢወድና ቢተባበር በራሱም በወንድሙም ጥፋት ተጠያቂ ይሆናል እንጂ የሚወደስበት ምግባር አይደለም። ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ይህቺ '#ከመልካም #ነገር' የምትለዋ ጭማሬ ወሳኝ ጭማሬ ናት። የሐዲሡን መልእክት ረቂቅ በሆነ መልኩ ትገድበዋለች። ምክንያቱም '#መልካም' የሚለው ቃል ዱንያዊም ይሁን ኣኺራዊ ትእዛዛትና ፍቁድ ነገሮችን የሚጠቀልል ሲሆን ክልክል ነገሮችን ደግሞ ያወጣል። 'መልካም' የሚለው ቃል አይመለከተውምና። ይሄ ግልፅ ነው። ስለዚህ ከአንድ ሙስሊም ስነ ምግባር ሙሉነት ውስጥ የሚካተተው ለራሱ እንደሚወደው ለሙስሊም ወንድሙ መልካምን መውደድ ነው። ልክ እንዲሁ ለራሱ የሚጠላውን መጥፎ ነገር ለሙስሊም ወንድሙ መጥላት ነው።..." [አስሶሒሐህ፡ ሐዲሥ ቁ. 73]
#ከሐዲሡ_የሚወሰዱ_ቁም_ነገሮች፦
✅ ሙእሚን ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ ሊወድ እንደሚገባ፣
✅ የኢስላም ወንድምን ወይም እህትን መውደድ ከኢማን እንደሆነ፣
✅ ኢማን መልካም በመስራት እንደሚጨምር፣ ወንጀል በመስራት ደግሞ እንደሚቀንስ ከሐዲሡ እንማራለን።
✅ በዚህ ሐዲሥ መልእክት መስራት እርስ በርሱ የሚዋደድና መተሳሰብ የነገሰበት ህብረተሰብ እንዲኖር ያደርጋል።
✍ #from_writer_በዱአ_አትርሱኝ
👉 የነወውይ አርባ ሐዲሥ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር (ገጽ 34-36)
👉 @Twehid12
👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah