“በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ
~ ~ ~~ ~ ~~~~ ~~~~~~~~~~
እጅግ ከሚገርሙ ነገሮች ውስጥ አንዱ መጤ ለሆነው መውሊድ ቁርኣንና ሐዲሥ የሚያጣቅሱ ሰዎችን ማየት ነው። ይሄ የሚያሳየው ሰዎቹ ምን ያክል ለቁርኣንና ሐዲሥ ተገቢ ክብር የማይሰጡ፣ ሐያእ የቀለላቸው እንደሆኑ ነው። መውሊድ በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስኮ፦
* ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት በሶሐቦቹ፣ በታቢዒዮቹ፣ በአትባዑ ታቢዒን፣ በታላላቅ ቀደምት ኢማሞች፣ ይከበር ነበር።
* እናንተ እንደምትሉት በሙዞፈር እስከሚጀመር ስድስት ክ/ዘመን መቆየት ሳያስፈልገው በኸሊፋዎቹ ይፈፀም ነበር።
* በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ በዚህ ቢድዐ ላይ ውዝግብ ባልተነሳ ነበር።
* በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ ነቃፊ ዑለማዎች ቀርቶ እንደ ኢብኑ ሐጀር፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣ ዒራቂ፣ ተዝመንቲ፣… ያሉ የመውሊድ ደጋፊዎች ጭምር ቢድዐ ነው ብለው ባልደመደሙ ነበር። ቁርኣንና ሐዲሥ ውስጥ የሚገኝ ጉዳይ “ቢድዐ ይባላልንዴ?!”
* በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ ሶላሑዲን አል አዩቢ የባጢኒያ ሺዐዎችን ስርኣት ሲገረስስ በነሱ የተጀመረውን መውሊድም አብሮ ባላቋረጠው ነበር።
እነዚህን እውነታዎች ይዘን ከዚያም እነዚህ አካላት ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናሉ ብለው የሚጠቅሷቸውን የቁርኣን አንቀፆችንና ሐዲሦችን ብንመለከት ስራቸው አይን ያወጣ ማምታት እንደሆነ እንደመድማለን። ምክንያቱም የሚጠቅሷቸው አንቀፆችና ሐዲሦች መውሊድን የሚጠቁሙ ቢሆኑ ኖሮ በዚያ እንቁ ዘመን ይከበር ነበርና። በዚያ ዘመን መውሊድ አለመከበሩ እነዚህ አታላዮች ለአንቀፆቹ የሚሰጧቸው ትርጓሜዎች የተሳሳቱ ለመሆናቸው በቂ ማሳያ ነው።
ባጭሩ ለነዚህ አካላት የምንሰጣቸው ጥቅል ምላሽ የትኛውም የቁርኣን አንቀፅ ወይም የሐዲሥ ትርጓሜ ዋጋ የሚኖረው የቀደምቶችን ግንዛቤ የተከተለ ሲሆን ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ የነሱን ቃላት እየተጠቀመ አፈፃፀሙ ግን የነሱን አፈፃፀም ያልተከተለ ከሆነ የሰለፎችን ግንዛቤ አልተከተለም ማለት ነው። ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ ረሒመሁላህ ሱብኪ የተባሉት ሸይኽ የሆነችን የቁርኣን አንቀፅ ከሰለፎች አንድም ባልቀደማቸው መልኩ በመፈሰራቸው የተነሳ ምላሽ ሲሰጧቸው እንዲህ ነበር ያሉት፡-
“ይሄ ተቃዋሚ ይህቺን አንቀፅ የፈሰረበት መንገድ በርግጠኝነት ውድቅ ነው። ሐቅ ቢሆን ኖሮ (ቀደምቶቻችን) በእውቀትም፣ በተግባርም፣ በማመላከትም፣ በመምከርም ይቀድሙን ነበር። በየትኛውም አንቀፅ ወይም ሱና ላይ በሰለፎች ዘመን ያልነበረ፣ እነሱ ያላወቁትና ለህዝቡ ግልፅ ያላደረጉት የሆነን ትንታኔ መፍጠር አይቻልም። እንዲህ ማድረግ እነሱ በዚህ ላይ ሐቁን ዘንግተውና ከሱም አፈንግጠው ኖሮ ይሄ ዘግይቶ የመጣው ተቃዋሚ አግኝቶታል ማለት ነው።” [አሷሪሙል ሙንኪ፡ 247]
በነገራችን ላይ እንደ ኢብኑ ሐጀር፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣… ያሉ ዓሊሞች መውሊድ በሰለፎቹ ዘመን ያልነበረ ቢድዐ ነው ብለው በግልፅ ሲናገሩ ብዙ ጣጣ ጨርሰውልናል። ምክንያቱም ሰለፎች ለማያውቁት ዒባዳ ቁርኣንና ሐዲሥን ማጣቀስ ስህተት መሆኑ በቁርጥ የሚታወቅ ነውና።
ይህንን ከያዝን በኋላ ሱፍዮች ለመውሊድ ቢድዐ ጠንካራ ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱትን የቁርኣን መልእክት እንመልከት፡-
{قُلۡ بِفَضۡلِ ٱللَّهِ وَبِرَحۡمَتِهِۦ فَبِذَٰلِكَ فَلۡيَفۡرَحُواْ هُوَ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ} [يونس: 58]
{“በአላህ ችሮታና በእዝነቱ ይደሰቱ። እርሱ ከሚሰበስቡት ሃብት በላጭ ነው” በላቸው።} [ዩኑስ፡ 58]
እና በዚህ ውስጥ መውሊድን የሚደግፍ ምን መልእክት አለ? ብትሉ “በአላህ እዝነትና ችሮታ እንድንደሰት ታዘናል፤ ከእዝነቶችና ችሮታዎቹ ሁሉ በላጩ ደግሞ የነብዩ ﷺ መወለድ ነው። ስለዚህ መውሊዳቸውን ማክበር በዚች አንቀፅ ውስጥ ተካቷል” ይላሉ።
መልስ፡-
=====
አዎ አላህ በችሮታውና በእዝነቱ እንድንደሰት አዞናል። ችሮታውና እዝነቱ ሲባል ምንድነው የተፈለገው በሚለው ላይ “ቁርኣን”፣ “ዲን”፣ “ኢስላም”፣ “ኢማን”፣ “ከቁርኣን ሰዎች ማድረጉ”፣ “ሱናዎች”፣ “ጀነት” ወዘተ የሚሉ ተፍሲሮችን በቀዳሚነት ብናገኝም ነብያችንንም ﷺ የሚያካትት ይሆናል። ይህንን የሚጠቁም ተፍሲር ኢብኑል ጀውዚ፣ ሲዩጢና ኣሉሲ አስፍረዋል። በርግጥ ሶስቱም በቀዳሚነት ያሰፈሩት ይህንን አይደለም። ሱፍዮች ግን ቀዳሚዎቹን ጥለው እዚህ ላይ ነው የሚያነጣጥሩት። ቢሆንም ብዙም የሚያሳስብ አይደለም። መልእክቱ ጠቅላይ ነውና እዚህ ላይ ከተጠቀሱት ውጭ ባሉ የጌታችን ችሮታዎች ጭምር እንደሰታለን፣ እናመሰግነዋለንም። ነገር ግን፦
1. የአንቀጿ መልእክት በነብያችን ﷺ ላይ የተገደበ ባልሆነበት እንዲያውም ሌሎቹ ተፍሲሮች ቀዳሚ በሆኑበት ነጥሎ እሳቸውን ብቻ የታሰቡ አድርጎ ማቅረብ ማድበስበስ ነው።
2. በቁርኣን፣ በሐዲሥ፣ በኢስላም፣ በኢማን፣ ... ለመደሰት አመት መጠበቅ እንደማያስፈልገን ሁሉ በነብዩ ﷺ ለመደሰትም አመት መጠበቅ አያስፈልገንም። ይሄ ሱፍያዊ ተርቲብ ነው። አመት ጠብቆ ያልዘለለ ሰው በነብዩ ﷺ መልላክ አልተደሰተም ብሎ ማሰብም የለየለት ብልግና ነው።
3. የአንቀጿ መልእክት ሙሉ በሙሉ ነብዩን ﷺ የሚገልፅ ነው ቢባል እንኳን አመት ጠብቃችሁ መውሊድ አክብሩ የሚል ጭብጥ በቅርብም በሩቅም የለም። እነዚህ አካላት ግን ካልተጨፈረ ካልተዘለለ ደስታ ያለ አይመስላቸውም። በዚያ ላይ የልደት ቀናቸው በቁርጥ አለመታወቁን ጨምሩበት።
4. የአንቀጿ መልእክት ለመውሊድ ማስረጃ ቢሆን ኖሮ ቀደምቶች እየተሰባሰቡ መውሊዳቸውን ያከብሩ ነበር። ይሄ ተግባር በዚያ ዘመን አለመፈፀሙ የቁርኣኑ መልእክት መውሊድን ፈፅሞ እንደማያካትት በቁርጥ ያስረዳል።
5. ሰለፎች መውሊድን ያላከበሩት ስላልተመቻቸው ነው የሚለውን ሱፍያዊ ማምታቻ ለጊዜው ብንቀበል እንኳ ሰለፎቻችን ከተፍሲሮቻቸው ያሰፍሩት ነበር። ልብ በሉ የመውሊድ አክባሪዎች ከዘመናት በኋላ መጥተው መልእክቱን ጠምዝዘው ለዚህ ቢድዐ እስከሚጠቀሙበት ድረስ ይህቺን አንቀፅ ለመውሊድ መረጃ ያደረገ አንድ እንኳን የለም። ሙልሀም እንደሆኑ ከተመሰከረላቸው ዑመር፣ ቁርኣንን እንደወረደ መቅራት የፈለገ ከሳቸው እንዲማር የተነገረላቸው ኢብኑ መስዑድ፣ ቱርጁማኑል ቁርኣን ከተባሉት ኢብኑ ዐባስ፣ ከቁርኣን ሰብሳቢው ዑስማንና ዘይድ ኢብኑ ሣቢት፣ ከነ ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ … የሙፈሲሮች ሸይኽ ከሚባሉት ከሙጃሂድ፣ ከነቀታዳ፣ ከነዶሓክ፣ ከነሻፊዒይ፣ ከነማሊክ፣.. እንዴት ተሰወረ? እነዚህ ሁሉ ያላወቁትን ነው ከዚያ በኋላ የመጣ ትውልድ የሚያውቀው?!
6. በነዚህ ሰዎች ስሌት ከተሄደ የሶሐቦችንም መውሊድ ማክበር ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ሶሐቦች አላህ ለኡማው ከዋላቸው ፀጋዎች ውስጥ ናቸው። የነብዩ ﷺ ሚኒስትሮችና ጉዳይ አስፈፃሚዎች ነበሩ። ሶሐቦች ለዚህ ኡማ ባለውለታ ናቸው። ቁርኣኑም ሐዲሡም ያለነሱ ወደኛ መድረስ አይችልም ነበር። ስለዚህ አላህ ለኛ ከዋለልን ውለታዎች፣ ከትሩፋቱ፣ ከእዝነቱ ናቸው። አላህ ደግሞ በትሩፋቱና በእዝነቱ እንድንደሰት አዞናል። ስለዚህ የእያንዳንዱ ሶሐባ መውሊድ መከበር አለበት። በተለይ ደግሞ ኹለፋኡ አርራሺዲን። ውለታቸውም ደረጃዎቻቸውም ከፍ ያለ ነውና። ኧረ እንዲያውም በአንቀጿ ውስጥ “ትሩፋቱ” ሲባል የተፈለገው ነብዩን ﷺ ለማለት ሲሆን “እዝነቱ” የሚለው ደግሞ “ዐሊይን ነው” የሚል ዘገባ ከኢብኑ ዐባስ እንደተላለፈ አልኸጢብ እና ኢብኑ ዐሳኪር ገልፀዋል። [ሩሑል መዓኒ፡ 6/133] ከነሱ ቀጥሎ የመጡት ታቢዒዮችም እንዲሁ እነሱስ ባይኖሩ