የመንሃጅ ስህተት የታየበት/ ቢድዐ ላይ የወደቀ ሁሉ ከሱና ይወጣል ወይ?
~
ባለፈው ጥፋቶች ከክብደታቸው አንፃር እኩል እንዳልሆኑ ስለሆነም በኢጅቲሃዳዊ ጉዳዮ ሰዎችን ከሱና ማስወጣት እንደማይፈቀድ በመግለፅ የተወሰኑ ዑለማዎችን ንግግሮች አጣቅሼ ነበር። ዛሬ ማንሳት የፈለግኩት ደግሞ ስህተቶቹ መንሃጅ ነክ ቢሆኑ እንኳ ከሱና ለማስወጣት መቻኮል እንደማይገባ ማስታወስ ነው። በሱና የሚታወቅ ሰው እንዲህ አይነት ስህተቶች ስለታዩበት ግራ ቀኝ ሳይታይ በቢድዐ አይፈረጅም። የዑለማዎችን ንግግር እጠቅሳለሁ፦
1. ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ፦
وَقَدْ اجْتَهَدَ فِي طَلَبِهِ فَعَجَزَ عَنْهُ فَلَا يُعَاقَبُ وَقَدْ يَفْعَلُ بَعْضَ مَا أُمِرَ بِهِ فَيَكُونُ لَهُ أَجْرٌ عَلَى اجْتِهَادِهِ وَخَطَؤُهُ الَّذِي ضَلَّ فِيهِ عَنْ حَقِيقَةِ الْأَمْرِ مَغْفُورٌ لَهُ. وَكَثِيرٌ مِنْ مُجْتَهِدِي السَّلَفِ وَالْخَلَفِ قَدْ قَالُوا وَفَعَلُوا مَا هُوَ بِدْعَةٌ وَلَمْ يَعْلَمُوا أَنَّهُ بِدْعَةٌ إمَّا لِأَحَادِيثَ ضَعِيفَةٍ ظَنُّوهَا صَحِيحَةً وَإِمَّا لِآيَاتِ فَهِمُوا مِنْهَا مَا لَمْ يُرَدْ مِنْهَا وَإِمَّا لِرَأْيٍ رَأَوْهُ وَفِي الْمَسْأَلَةِ نُصُوصٌ لَمْ تَبْلُغْهُمْ.
“በርግጥም ሐቅን ፈልጎ ጥሮ ስላልደረሰበት አይቀጣም። ምናልባት ከታዘዘበት ከፊሉን ይሰራና በጥረቱ ምንዳ ይኖረዋል። ከትክክለኛው ጉዳይ ፈር የለቀቀበት ስህተቱ ይማርለታል። ከቀደምቶቹም ይሁን ከኋለኞቹ ብዙ ሙጅተሂዶች ቢድዐ መሆኑን ሳያውቁ በእርግጥም ቢድዐ የሆነን ነገር ተናግረዋል፣ ፈፅመዋልም። ይህም የሆነው ወይ ትክክለኛ መስለዋቸው ደካማ ሐዲሦችን ይዘው ነው። ወይ ደግሞ ትክክለኛ ያልሆነን መልእክት (በተሳሳተ መልኩ) ከ(ቁርኣን) አንቀፆች ተረድተው ነው። ወይ ደግሞ መረጃዎች ሳይደርሷቸው በጉዳዩ ላይ የራሳቸውን እይታ ተንተርሰው ነው።” [አልመጅሙዕ፡ 19/191]
አሁንም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ፡-
وَمِثْلُ هَؤُلَاءِ إذَا لَمْ يَجْعَلُوا مَا ابْتَدَعُوهُ قَوْلًا يُفَارِقُونَ بِهِ جَمَاعَةَ الْمُسْلِمِينَ؛ يُوَالُونَ عَلَيْهِ وَيُعَادُونَ؛ كَانَ مِنْ نَوْعِ الْخَطَأِ. وَاَللَّهُ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى يَغْفِرُ لِلْمُؤْمِنِينَ خَطَأَهُمْ فِي مِثْلِ ذَلِكَ. وَلِهَذَا وَقَعَ فِي مِثْلِ هَذَا كَثِيرٌ مِنْ سَلَفِ الْأُمَّةِ وَأَئِمَّتِهَا: لَهُمْ مَقَالَاتٌ قَالُوهَا بِاجْتِهَادِ وَهِيَ تُخَالِفُ مَا ثَبَتَ فِي الْكِتَابِ وَالسُّنَّةِ
“የነዚህ አምሳያ የሆነው የፈጠሩትን ነገር በሱ ሳቢያ የሚወዳጁበትና የሚጠሉበት፣ ከሙስሊሞች ህብረት የሚገነጠሉበት ንግግር ካላደረጉት እንደ ስህተት ነው የሚቆጠረው። የጠራውና የላቀው አላህ በዚህ አምሳያ ላይ ያሉ ስህተቶችን ለአማኞች ይምራልና። ለዚህም ነው ከመልካም ቀደምቶችና ምሁራን ውስጥ ብዙዎች ይህን በሚመስሉ ጥፋቶች ላይ የወደቁት። በኢጅቲሃድ የተናገሯቸው ከቁርኣንና ከሱና ጋር የሚፃረሩ ንግግሮች አሏቸው።” [አልመጅሙዕ፡ 3/349]
ልብ በል! ከሰለፍም ከኸለፍም ሳያስቡት ቢድዐ የፈፀሙ/ የተናገሩ አሉ እያሉ ነው። ሰለፎች ቢድዐ ላይ ብርቱ አስጠንቃቂዎች ነበሩ ማለት በተናጠል ከቢድዐ ፍፁሞች ነበሩ ማለት አይደለም። ከነቢያት ውጭ የሰው ልጅ በሙሉ ሰለፎቹን ጨምሮ ተሳሳች ነው። የአህለ ሱናን አቋም የሚከተል፣ ለሱና የሚለፋና ተቆርቋሪ የሆነ ሰው በሚታዩበት አንዳንድ ስህተቶች ገደል አይከተትም። ባይሆን ስህተት ከማንም ቢመጣ ይጣላል። እንጂ የተከበረ፣ የታወቀ፣ ዑዝር የሚሰጠው ስለሆነ ብቻ የተናገረው ሁሉ ሐቅ ይሆናል ማለት አይደለም።
2. አዘሀቢይ ረሒመሁላህ፦
አልኢማም ሙሐመድ ብኑ ነስር አልመርወዚ ረሒመሁላህ ከታላላቅ የኢስላም ሊቃውንት ናቸው። ከኢማን ጋር በተያያዘ ብዙዎች ያልወደዱት አሻሚ ቃል ይናገራሉ። በዚህ የተነሳ የዘመናቸው ዑለማዎች አኮረፏቸው። የኹራሳንና የዒራቅ ሊቃውንትም ተቃረኗቸው። ኢማሙ ዘሀቢ ረሒመሁላህ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጠልቆ መግባት እንደማያስፈልግ ገልፀው ከዚያም ትክክለኛውን እይታ አፍታተው ካስቀመጡ በኋላ እንዲህ ሲሉ ቁልፍ መልእክት አስተላለፉ፡-
وَلَوْ أَنَّا كلَّمَا أَخْطَأَ إِمَامٌ فِي اجْتِهَادِهِ فِي آحَادِ المَسَائِلِ خَطَأً مَغْفُوراً لَهُ، قُمْنَا عَلَيْهِ، وَبدَّعْنَاهُ، وَهَجَرْنَاهُ، لَمَا سَلِمَ مَعَنَا لَا ابْنَ نَصْرٍ، وَلَا ابْنَ مَنْدَةَ، وَلَا مَنْ هُوَ أَكْبَرُ مِنْهُمَا، وَاللهُ هُوَ هَادِي الخَلْقِ إِلَى الحَقِّ، وَهُوَ أَرحمُ الرَّاحمِينَ، فَنَعُوذُ بِاللهِ مِنَ الهوَى وَالفظَاظَةِ
“አንድ ኢማም በነጠላ ጉዳዮች ይቅር የሚባልበት የሆነን ስህተት በኢጅቲሃዱ በተሳሳተ ቁጥር ተነስተን በቢድዐ የምንፈርጀውና የምናኮርፈው ቢሆን ኖሮ ከኛ ጋር ኢብኑ ነስርም፣ ኢብኑ መንዳህም አይተርፉም ነበር። ኧረ ከነሱ የበለጠም አይተርፍም። ፍጡርን ወደ ሐቅ የሚመራው አላህ ነው። እሱ ከአዛኞች ሁሉ አዛኝ ነው። ከስሜትና ከክፉ አመል በአላህ እንጠበቃለን።” [አሲየር፡ 14/39-40]
ምን እያሉ እንደሆነ ገብቶሃል? ከነዚያ ታላላቆች በኩል መርወዚ ላይ የተወሰደውን እርምጃ በአደብ እያረሙ፣ ለሌሎች ወሳኝ ትምህርት እያስተላለፉ ነው። ነገሮችን በዚህ መልኩ ብንይዝ ኖሮ እንኳን መርወዚ ከሳቸው የሚበልጡ ታላላቆችም አይተርፉም ነበር እያሉ ነው። እየውልህ ወንድሜ! ይሄ ጥንቃቄ ከዘሀቢ ጋር የተቀበረ አይደለም። ዛሬም ይሰራል። ማንም ላንቃው እስከሚበጠስ ቢጮህ ከኋላው እንዲያሰልፍህ አትፈቀድለት። የምትገባው ከራስህ ቀብር ነው።
ልጨምር፡ ኢብኑ ኹዘይማህ ረሒመሁላህ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ያላፀደቁ ሰዎችን አክ^ፍ^ረው ተናግረዋል። ዘሀቢ የኢብኑ ኹዘይማን ክብርና ደረጃ ከገለፁ በኋላ እንዲህ ይላሉ፦
وَكِتَابُه فِي (التَّوحيدِ) مُجَلَّدٌ كَبِيْرٌ، وَقَدْ تَأَوَّلَ فِي ذَلِكَ حَدِيْثَ الصُّورَةِ. فَلْيَعْذُر مَنْ تَأَوَّلَ بَعْضَ الصِّفَاتِ، وَأَمَّا السَّلَفُ، فَمَا خَاضُوا فِي التَّأْوِيْلِ، بَلْ آمَنُوا وَكَفُّوا، وَفَوَّضُوا عِلمَ ذَلِكَ إِلَى اللهِ وَرَسُوْلِه، وَلَوْ أَنَّ كُلَّ مَنْ أَخْطَأَ فِي اجْتِهَادِهِ - مَعَ صِحَّةِ إِيْمَانِهِ، وَتَوَخِّيْهِ لاتِّبَاعِ الحَقِّ - أَهْدَرْنَاهُ، وَبَدَّعنَاهُ، لَقَلَّ مَنْ يَسلَمُ مِنَ الأَئِمَّةِ مَعَنَا، رَحِمَ اللهُ الجَمِيْعَ بِمَنِّهِ وَكَرَمِهِ