ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መውሊድ በመጣ ቁጥር ሰለፍዮች በመውሊድ ቢድዐ እና በሚያጅቡት ጥፋቶች ዙሪያ በሰፊው ማስጠንቀቂያ እንደሚሰጡ ለማንም አይሰወርም፡፡ በርካታ የኢኽዋነል ሙስሊሚን አስተሳሰብ አራማጆች ታዲያ ይሄ ዘመቻ ክፉኛ ሲረብሻቸው ይታያሉ፡፡ እራሳቸውን መካከለኛ ለማድረግ የመውሊድ ፅንፈኛ ደጋፊዎችን በስሱ ከነኩ በኋላ ያለ የሌለ ሃይላቸውን መውሊድን በሚነቅፉት ላይ እንደሚያደርጉ በሰፊው እየታዘብን ነው፡፡ መውሊድ ላይ የሚሰነዘረው ተቃውሞ ክፉኛ እንዲረብሻቸው የሚያደርጓቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል፡-
1. ኢኽዋነል ሙስሊሚን እንደ ቡድን መሰረቱ ተሶውፍ ነው፡፡ የቡድኑ መስራች ሐሰን አልበና የሻዚሊያ ጦሪቃ ቅርንጫፍ የሆነው “ሐሷፊያ ጦሪቃ” ተከታይ የነበረ ሲሆን እራሱ እንደገለፀው “የሐሷፊያን አስተሳሰብ የጠገብኩ ሆኜ ወደ ደመንሁር ወረድኩ” ይላል፡፡ [ሙዘኪራቱ ደዕዋ፡ 31 - 34] ከቡድኑ አመራሮች አንዱ የሆነው ሰዒድ ሐዋ “የኢኽዋነል ሙስሊሚን ንቅናቄ እራሱ ሱፊ ነው የመሰረተው፡፡ አሉታዊ ጎኖቹን በመተው የተሶውፍን እውነታ ወስዷል” ይላል፡፡ [ጀውላቱን ፊል ፊቅሀይን፡ 154] እስከ ፍፃሜው ተሶውፍ ላይ እንደዘለቀ ታላላቅ የኢኽዋን ቁንጮዎች መስክረዋል፡፡ ስለዚህ ዛሬ የኢኽዋን ፀሐፊዎች በተለያየ ስልት ከሱፍዮች የሚከላከሉት ከራሳቸው፣ ከመሪዎቻቸው፣ ከቡድናቸው ለመከላከል ነው፡፡ ሱፍያ ተነካ ማለት ኢኽዋን ተነካ ማለት ነው፡፡ ሙስሊሞች ሱፍያን ተፀየፉ ማለት የኢኽዋን መሰረቱ ተናጋ ማለት ነው፡፡
2. የቡድኑ መስራች ሐሰን አልበና ረቢዑል አወል አንድ ካለ ጀምሮ እስከ 12 ድረስ መውሊድን ያከብር እንደነበር እራሱ ፅፏል፡፡ [ሙዘኪራ፡ 58] ዛሬም ድረስ ለመውሊድ ሽንጣቸውን ገትረው የሚሟገቱ ኢኽዋኖችን የምናየው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ በየመውሊዱ የሚፈፀመውን ሺርክና ቢድዐ ደግሞ የምናውቀው ነው፡፡ ምናልባት “እነሱ ነፍስን ማጥራት ላይ የሚያተኩረውን፣ ንፁሁን ተሶውፍ ነው የተከተሉት” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ ቀጣዮቹን ነጥብ ተመልከቱ፡፡
3. በርካታ ሱፍዮች ዘንድ ነብዩ ﷺ ከመውሊዱ ጭፈራ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ቀጣፊዎች ናቸው፡፡ ነብዩ ﷺ ፈፅሞ ከእንዲህ አይነቱ የባእድ አምልኮ ድግስ ላይ አይገኙም፡፡ ይሄ ቅጥፈታዊ እምነት በኢኽዋነል ሙስሊሚን መስራቹ ሐሰን አልበናም ጭምር ሲስተጋባ የነበረ ነው፡፡ ይሄው እነ ሐሰን አልበና መውሊድ ላይ ሲያንጎራጉሯቸው ከነበሩ ስንኞች ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡-
هذا الحبيب مع الأحباب قد حضرا …
… لا شك أن حبيب القوم قد حضرا
“ይህ ወዳጃችን (ነብዩን ነው) ከወዳጆች ጋር ተገኝቷል
…
… ያለጥርጥር የሰዎቹ ወዳጅ ተገኝቷል፡፡” [ሐሰን አልበንናህ በአቅላሚ ተላሚዘቲሂ ወሙዓሲሪሂ፡ 71-72]
ይህ እምነት ዛሬም ድረስ ከሱፍዮች ዘንድ በሰፊው ያለ ነው፡፡ በመውሊድ ጭፈራቸው መሃል መብራት አጥፍተው ነብዩ መጡ ይሉና “መርሐባ ነቢ መርሐባ! መርሐባ!” እያሉ አቀባበል ያደርጋሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ታዳሚው እንዳለ ይቆማል፡፡ ክቡሩ ነቢይ ﷺ የነሱን በሺርክ የተጨማለቀ፣ በውዝዋዜ የታጀበ ድግስ ሊታደሙ መሆኑ ነው፡፡ “አይ ይሄኮ ስማቸው ሲወሳ ለአክብሮት ያክል የሚፈፀም እንጂ ቦታው ላይ ይገኛሉ ተብሎ አይደለም” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ ቦታው ላይ ይገኛሉ የሚል እምነት እንዳለማ ይሄው የሐሰን አልበናን ንግግር አጣቀስኩልህ፡፡ በሃገራችንም በሰፊው የሚታወቅ እምነት ስለሆነ መወሻሸት አያስፈልግም፡፡ ደግሞስ በየደዕዋው ላይ፣ በየ መስጂዱ፣ በየ መድረኩ ስማቸው ሲወሳ ትቆማላችሁ እንዴ? ውሸት!!
በነገራችን ላይ ነብዩ ﷺ በህይወት ሳሉ ማንም እንዲቆምላቸው አይወዱም ነበር፡፡ አነስ ኢብኑ ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “እነሱ (ሶሐቦች) ዘንድ ዱንያ ውስጥ እንደ ነብዩ ﷺ ሊያዩት የሚወዱት ሰው አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን መጥላታቸውን ስለሚያውቁ ለሳቸው አይቆሙም ነበር፡፡” [አሶሒሐህ፡ 358]
ሌላ በነገራችን ላይ! ይህንን ነብዩ መጡ እያሉ መነሳትን የሚሰማ ጠፋ እንጂ ከሚውሊድ አክባሪዎች ውስጥ ሳይቀር የኮነኑት ነበሩ፡፡ ኢብኑ ሐጀር አልሀይተሚ እንዲህ ይላል፡-“የዚህ አምሳያው ብዙዎች የነብዩ ﷺ ልደትና እናታቸው እሳቸውን መውለዷ ሲወሳ የሚያደርጉት መቆም ሲሆን ይህም ምንም አይነት መረጃ ያልመጣበት ቢድዐ ነው፡፡ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት እሳቸውን ﷺ ለማላቅ ነው፡፡ መሃይማኑ ከአዋቂዎቹ በተለየ በዚህ ድርጊታቸው ይታለፋሉ (መዕዙሮች ናቸው፡፡)” [አልፈታዋ አልሐዲሢያህ፡ 58]
4. መውሊድን ያክል እጅግ በርካታ ቢድዐዎችን አቅፎ የያዘን ቢድዐ አቅልሎ ማቅረብ ቡድናዊ ስሜት እየጋረዳቸው እንጂ ላስተዋለ ሁሉ በቀላሉ የሚታይ ነው፡፡ በስፍራዎቹ የሚፈፀሙትን እንደ ዝሙት፣ አላስፈላጊ የወንድና የሴት ቅልቅል፣ በመስጂድ ውስጥ መጨፈር፣ መስጂዶችን በጫትና በተረፈ ምግብ ማቆሸሽ፣… ይቅርና ብዙ ከባባድ ሺርኮች ይፈፀማሉ፡፡ ግና በርካታ ኢኽዋኖችን የሺርክ ጉዳይ ሲያስጨንቃቸው አይታይም፡፡ እንጂማ በነቢዩ ﷺ እና በ“ወልዮች” ላይ ብዙ ድንበር ይታለፋል፡፡ በመውሊድ ቦታዎች ላይ ብዙ አይነት ሺርክ ይፈፀማል፡፡ ለቀብር ሱጁድ ይወረዳል፡፡ ጦዋፍ ይደረጋል፡፡ ለበረካ እየተባለ የቀብር አፈር እየተበጠበጠ ይጠጣል፡፡ ከዘመናት በፊት ያለፉ ሙታኖችን ሰዎች ይማፀናሉ፡፡ ስለት ይፈፅማሉ፡፡ ያርዳሉ፡፡ በሺርክ የተሞሉ መንዙማዎች ይቀነቀናሉ፡፡
ይህን ሁሉ ጥፋት አጭቆ የያዘን ቢድዐ ስላወገዙ ነው ሰለፍዮች እንደ ጠርዘኛ የሚሳሉት፡፡ መውሊድ በመጣ ቁጥር ሰዎችን ከዚህ ጥፋት ስላስጠነቀቁ ነው ጨቅጫቃ የሚደረጉት፡፡ “ረቢዕን የመጨቃጨቂያ ወር አደረጉት” ይላሉ፡፡ የጥቱን ጠንሳሾችና አራጋቢዎች ባላዩ እያለፉ ከሺርክና ቢድዐ የሚያስጠነቅቁ ሰዎችን ማብጠልጠል ምን ያክል ሃፍረተ ቢሶች እንደሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡ እውነት ለህዝብ ብትቆረቆሩ ኖሮ ወገናችንን በዚህ በሺርክ ከተወረረ በዓል ለማትረፍ ድርሻ በነበራችሁ ነበር፡፡ “ወላኪን ላ ሐያተ ሊመን ቱናዲ!”
“ይህን ሁሉ ጉድ እያወቁ እንዴት ለመውሊድ ይሟገታሉ?” የሚሉ የዋሆች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንጀቴ!! “ጅቡን ነወይ አውሬ እምትይው?” አሉ፡፡ ችግሩ የራሳቸውም ጭምር ነው፡፡ የሚሟገቱት ወደው እንዳይመስላችሁ፡፡ የኢኽዋን ቡድን መስራች ሐሰን አልበና ከጭፍሮቹ ጋር በመሆን በመውሊድ ሲያቀነቅኑት ከነበሩ ዜማዎች ውስጥ እነዚህ ነበሩ፡-
هذا الحبيب مح الأحباب قد حضرا …وسامح الكل فيما قد مضى وجرى
… لا شك أن حبيب القوم قد حضرا
“ይህ ወዳጃችን ከወዳጆች ጋር ተገኝቷል፡፡
ያለፈ የሆነውን ሁሉ ይቅር ብሏል፡፡

ይሄ ከኢስላም የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክ አይደለምን? ከአላህ ውጭ ወንጀልን የሚምር አለ?! አላህ ምን እንዳለ አስተውሉ፡-
وَمَنْ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إلاَّ اللهُ
“ከአላህ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምረው ማነው?” [ኣሊ ዒምራን፡ 135]
ኢኽዋን ለተውሒድ ደዕዋ እንቅፋት የሚሆነው ያለ ምክንያት አይምሰላችሁ፡፡ በብዙ መስጂዶች ተብሊግ እየፈነጨ “ያለ ኮሚቴው ፈቃድ ደዕዋ ማድረግ አይቻልም” የሚል ወረቀት ገና ከበር የሚለጥፉት ብዙዎቹ የተውሒድ ደዕዋን ለመዝጋት ነው፡፡ አንዳንዶቹ መሸፋፈኛ ስልቱን በመዘንጋ