#በስነምግባር_ባልሽን_አክሚ “
✍ አሚር ሰይድ
85 ዓመቱ ሸይኽ ዐብደላህ በሳተላይት ቻናል ላይ የፈትዋ ፕሮግራም እየሰጡ አንዲት ትውልደ አልጄሪያዊት ሴት ደወለችና እንዲህ አለች፦
"ሙስሊም ነኝ ለጌታዬ ታዛዥ። ትውልዴም በሀገረ አልጄሪያ ነው። የአላህን ትዕዛዝ የባሌን ሐቅ እየተወጣሁ ለብዙ በደሎቹ ትዕግስትን ተላብሼ እኖራለሁ። ባሌ ዘወትር መጠጥ ሲጠጣ አምሽቶ እየተንገዳገደ ወደቤት ይገባል። ትላንት በዛ ሁኔታ ላይ ሆኖ ሲመጣ ቁርአን እየቀራሁ ነበር። እየተሳደበ ከእጄ ላይ ነጠቀኝና ሽንት ቤት ወረወረው። በንዴት ተቃጠልኩ ድንበር ማለፉ ከኔ አልፎ በክቡር የአላህ ቃል ቁርአን ላይም ደረሰ። እኔም ከዚህ በላይ መታገስ ከበደኝ ፍች መጠየቅ እችላለሁን?"
በማለት ጥያቄዋን ሰነዘረች።
“ስንት ልጆች አሉሽ” ሲሉ ጠየቋት
“አምስት ወንዶች ልጆች አሉኝ ገና ልጆች ናቸው" አለች።
ለትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ። ጥንቃቄን የተሞሉ ቃላቶች ከአፋቸው እየሰነዘሩ ንግግራቸውን ቀጠሉ“ፍቺ አትጠይቂ ስሞታም ሳታቀርቢ ታግሰሽ ኑሪ የሚመጣብሽን ችግር ተቋቁመሽ በስነምግባርሽ ባልሽን አክሚ
በመሀል ጣልቃ ገብታ ንግግራቸውን አቋረጠች “ግን እንዴት ከዚህ በላይ መታገስ ይቻለኛል??" እያለች ተንሰቅስቃ አነባች።
"ልጆችሽ የእሱን ባህሪ ከሚላበሱ በጀሀነም እሳት ከሚማገዱ ታግሰሽ እሱን መመለስ አይሻልምን?!
ደሞስ በወንጀል ላይ ላለው ባለቤትሽ ችግሩን የሚረዳ ካንቺ በላይ ማን አለው?! ካንቺ በቀር ይህን ተግባሩን ታግሶና ወንጀሉን ደብቆ ከሰጠመበት ማዕበል ሊያወጣው የሚጥር ማንም የለም። ብትፈቸው እየሰከሩ ቁርአንን ሽንት ቤት የሚጥሉ ልጆችን ያፈራልና እባክሽ ታገሺ እዘኚለት ፍቺ ጠይቀሽ ማምለጥ መፍትሄ አይደለም። ነገ ለልጆችሽ ድልድይ መሆኑን አውቀሽ ለሊት ተነስተሽ አምርረሽ ዱዓ አድርጊለት አሏት
ቀናቶች ወራቶችን ወልደው ድፍን አንድ ዓመት ተቆጠሩ። ሸይኹ በሕንድ የሳተላይት ጣቢያ ላይ ተጥደው ፈትዋ እየሰጡ ስልኩ አቃጨለ።
"አሰላሙ ዓለይኩም ያ ሸይኽ አልኮል እየጠጣ ቁርአንን ስለሚቀዳድደው ባሌ ከአንድ ዓመት በፊት የደወልኩህ አልጀሪያዊቷ ሴት ነኝ"
“ወላሂ አስታወስኩሽ ልጄ እንዴት ነሽ?? የባልሽስ ሁኔታ ምን ላይ ነው? "ብለዉ ጠየቋት
"በአላህ ይሁንብኝ መስጂድ ቀድሞ ገብቶ አዛን የሚል፣ ሶለተ ተሀጁድ ቆሞ የሚያነጋ፣ ቁርአንንም በአግባቡ የሚቀራ ሰው ሆናል። ግዴታ የተደረጉበትን ሶላቶች ከነሱናቸው የሚሰግድ የአላህ ባርያ ሆናል። እኔ እንድፀና እርስዎን ሰበብ አርጎ አላህ እሱን ወደ ቀጥተኛ መንገድ መራው” አለችና የደስታ እንባ ከዓይኗ እየዘረገፈች ተንሰቀሰቀች። ለጌታዋ የቀረበች አማኝ ሴት በመሆኗ ንፅህናዋንና የልቧን ቅንነት አይቶ በዱዓዋ መልስ ሰጣት።
#አንድ ሰው ከወንጀል አዘቅጥ ይወጣ ዘንድ ትዕግስትን ከዕዝነት ጋር ተላብሳችሁ በጥበብ አስተምሩ!
ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group