🎖#ነፍስህ_ልትወጣ_ስትል_ልትሰራዉ_ትችላለህን❓
✍ አሚር ሰይድ
በአንዳንድ ዘገባዎች ተጠቅሶ እንደሚገኘው አንድ ልብስ ሰፊ አንድን ሷሊህ ሰው እንዲህ በማለት ይጠይቃቸዋል፡-
የክብርና የልእልና ባለቤት የሆነው አላህ የባሪያውን ተውበት ነፍሱ ልትወጣ ከጉሮሮው እስካልደረሰች ድረስ ይቀበለዋል ፤ በሚለው ሐዲስ ላይ ያለዎት አስተያየት ምንድን ነው? ብሎ ጠየቃቸዉ
ሷሊሁ ሰው ልብስ ሰፊውን እንዲህ በማለት ጠየቁት፡-
“ይህ እውነት ነው፡፡ ሆኖም ግን አንተ ስራህ ምን እንደሆነ ንገረኝ?
እኔማ ልብስ ሰፊ ነኝ' አለ፡፡
......በልብስ መስፋት ሂደት ውስጥ ቀላሉ ስራ ምንድን ነው?”
.....መቀሴን ይዤ ልብስ መቅደድ” አላቸው፡፡
"ለመሆኑ ይህን ስራ ስትሰራ ምን ያህል ጊዜ ሆነህ?”
"ለ30 ዓመታት ሰፍቻለሁ"
ነፍስህ ልትወጣ አንገትህ ላይ ስትደርስ መቀስህን ይዘህ ልብስ መቁረጥ የምትችል ይመስልሀል?”
"አይ እንደዛ ማድረግ አልችልም፡፡"
በዚህ ጊዜ ሷሊሁ ሰው እንዲህ አሉት፡-
“አንተ ልብስ ሰፊ ሆይ ላለፉት 30 ዓመታት ስታከናውነው የኖርከውን ነገር ነፍስህ ልትወጣ ስትል በቀላሉ ልትሰራው ካልቻልክ ከዚህ በፊት አድርገኸው የማታውቀውን ተውባ ነፍስህ ልትወጣ ስትቃረብ ማድረግ ይሳካልኛል ብለህ እንዴት ታስባለህ? አሁን ጥንካሬና ጉብዝና እያለህ ተውበት አድርግ፡፡ ያ ካልሆነ በመጨረሻው ሰዓትህ ምህረትና መልካም ፍፃሜን አታገኝም: …ለመሆኑ ሞት ከመምጣቱ በፊት ተውባ እንድታደርግ ከዚህ በፊት የነገረህ ሰው የለምን?''
በዚህ ጊዜ ልብስ ሰፊው በፍጥነት ተውበት አድርጎ ከልቡ ወደ ፈጣሪው መመለስ በመቻሉ ራሱም ሷሊህ ለመሆን በቃ፡፡
የአላህ መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ
ሲናገሩ፡- “ሰዎች እንዳኗኗራቸው ይሞታሉ፡፡ እንዳሟሟታቸውም ይቀሰቀሳሉ'' ብለዋል፡፡
✨✨✨ተውባን በማዘግየትና የሰይጣንን ጉትጐታ በማስተናገድ በወንጀል ላይ መቆየት ሕይወት በመጥፎ ሁኔታ እንድታልፍ ማድረግ መሆኑን ልብ ማለት ያሻል፡፡ ብልህ የሆነ አማኝ ለኃጢአቶቹ ምህረትን በመጠየቅ እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ ድረስ ራሱን አዘጋጅቶ ይጠባበቃል።
🌹ረመዷን የተዉበት ወር ነዉና እንጠቀምበት
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group