=============== #ሶላት==============
✍አሚር ሰይድ
ሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ💚 ስለሶላት አንገብጋቢነት እንዲህ ብለዋል፡-
አንድ ሰው ሩኩኡንና ሱጁዱን አሳምሮ ሶላቱን የሚሰግድ ከሆነ ሶላቱ ሰውየውን እንዲህ ይለዋል፡-
አሳምረህ እንደሰገድከኝ አላህ አንተንም ያሳምርህ!' ይህን ካለ በኋላ ወደ ሰማይ ይወጣል፡፡
ሰውየው ሶላቱን ሳያስተካክልና ሩኩእና ሱጁዱንም በግብር ይውጣ ከሰገደ ሶላቱ እንዲህ ይለዋል፡-
"እንዳበላሸኸኝ አንተንም አላህ ያበላሽህ፡፡'' ከዚያም እንደ አሮጌ ቁራጭጨርቅ ወርዶ ከፊቱ ላይ ይለጠፋል:: ብለዋል፡፡
>>>በቅዱስ ቁርአን እንዲህ የሚል አንቀፅ ተፅፎ እንገኛለን፡-ወዮላቸዉ ሰጋጆች፡ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸዉ ዘንጊዎች ለኾኑት(አል-ማዑን 4-5)
🌙🌙 ሚስወር ቢን መሕረማ (ረ.ዐ) እንዲህ ብሏል፡-
ኡመር ቢን አል ኸጧብ (ረ.ዐ) በጩቤ በተወጉ ጊዜ ህሊናቸውን ስተው መሬት ላይ ተዘረሩ፡፡ ልጠይቃቸው ከተኙበት ክፍል ገባሁ ሰውነታቸውን ሸፍነዋቸው እንደተንጋለሉ ነበር፡፡ ዙሪያቸውን ያሉትን ሰዎች ጠየቅኩ-
"አሁን እንዴት ናቸው?''
.....እንደምታየው ህሊናቸውን ስተዋል" በማለት መለሱልኝ።
“ለሶላት ጥሪ አደረጋችሁላቸውን? በህይወት ካሉ ከሶላት በስተቀር ሊያነቃቸው የሚችል አንድም ነገር የለም፡፡" በዚህ ጊዜ ሰዎቹ እንዲህ
የምእመናን አዛዥ ሆይ! ሶላት፣ ሶላት እየተሰገደ ነው፡፡” ይህን የሰሙት ኡመር (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡-
እንደዚያ ነው? ወላሂ ሶላትን የተወ፣ ከኢስላም አንዳች ነገር የለውም" ይህን ካሉ በኋላ ከሰውነታቸው ደም እየፈሰሰ ተነስተው ሶላታቸውን ስገዱ።" (ሃይሰሚ፣ ኢብን ሰዓድ፣ መውጦእ) ዘግበዉታል፡፡
🌙🌙 እጅግ በጣም ጠንካራና በአምልኮ ላይ ፅኑ በመሆኑ ታላቅ ምሳሌ ሆኖ ሊጠቀስ የሚችለው የካውካሱ ሙጃሂድ ሸይኽ ሻሚል ሲሆን በብዙ ቦታዎች ላይ በሳንጃ፣ በሰይፍና በጥይት ተመትቶ ቆስሏል፡፡ እኤአ በ1829 በተደረገው የጊርሚ መከላከል ጦርነት በሰይፍ በመወጋቱ በደረቱ በኩል የገባው ሰይፍ ሳንባውን፣ የጎን አጥንቱንና ከአንገቱ አካባቢ ክፉኛ ጐድቶት ነበር፡፡ ለስድስት ወራት ያክል ከታከመ በኋላ ነበር ለማገገም የበቃው፡፡
ይህ ወጣት ሙጃሂድ ከቆስለ በኋላ ለ25 ቀናት ያክል ህሊናውን ስቶ ነበር የቆየው፡፡ በ25ኛው ቀን መጨረሻ ላይ አይኑን ሲገልጥ ከአጠገቡ እናቱን እንዳያት ከአንደበቱ መጀመሪያ ያወጣቸው ቃላት እንዲህ የሚሉ ነበሩ፡-
#የምወድሽ_እናቴ! የሶላት ወቅት አልፎኝ ይሆን?''ነበር ያለዉ .....
🟢 ከፈርድ ሶላት ዉጭ በሱና ሶላት ላይ መጠንከር እንዳለብን የአላህ መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል-
በፍርዱ ቀን አንድ ባሪያ መጀመሪያ የሚጠየቀው ሶላቱን የተመለከተ ጥያቄ ነው፡፡ ግዴታ የተደረጉበት ሶላቶች የተስተካከሉ ከሆነ የእርሱ ጉዳይ ቀላል ስለሚሆን ሌላ ችግር ሳይገጥመው ፈተናውን ያልፋል፡፡ ሶላቱ ያልተስተካከለ ከሆነ ፈተናውን ስለሚወድቅ ከባድ ችግር ይገጥመዋል፡፡ የሰውዬው ፈርድ ሶላቶች ችግር ካለባቸው ኃያሉና የላቀ የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፡-
“ባሪያዬ አንዳች ዓይነት የሱና ሶላት እንዳለው ፈልጉለት፡፡'' ሱና ሶላቶች በፈርድ ሶላት ላይ የተከሰተውን ጉድለት ያካክሳሉ፡፡ በዚህ ዓይነት በሌሎች ጉዳዮቹም ላይ ምርመራው ይቀጥላል፡፡” (ቲርሚዚ)
🔶 በፈርድ እና በሱና ሶላት ላይ ያለንን ቁርኝት እናስተካክል...እራሳችንን እንፈትሽ ሶላት ስንሰግድ የጠፋ እቃ መፈለጊያ አርገንዋል ወይስ በተመስጦት በሁሹዕ እየሰገድነዉ ነዉ ወይ??
🔶የእኛ ሶላት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዳሉት ሶላቱ አሳምረህ እንደሰገድከኝ አላህ ያሳምርህ ከሚለን ዉስጥ ነን ወይስ አበላሽተህ እንደሰገድከኝ አላህ አንተንም ያበላሽህ?? ከሚለዉ ወይስጥ ነን ወይ??
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group