🎖🎖#ሶላት_አሰጋገድ_እኛና_ሱሀቦቹ🎖🎖
✍አሚር ሰይድ
የሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ💚 ባልደረባዎች በሶላት ላይ ለአላህ የነበራቸውን ፍራቻና መተናነስ የሚደንቅና የሚገርም ነዉ እስኪ የአሊ ረዐ የገጠመዉን ታሪክ እነሆ
⚡️⚡️⚡️ በአንድ ጦርነት ላይ በዓሊ (ረ.ዐ) እግር የቀስት አረር ተሰካባቸው፡፡ ከዚያም ሰዎች ሊያወጡት ሲሞክሩ ከባድ ህመም ስላስከተለባቸው ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡-
“ሶላት ስሰግድ ያን ጊዜ ታወጡልኛላችሁ፡፡" ሰዎቹም እንደተባሉት ዓሊ (ረ.ዐ) ሶላት ላይ በቆሙ ጊዜ ያለምንም ችግር መዝዘው አወጡላቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ምንም ህመም ያልተሰማቸውና ሶላታቸውን ተረጋግተው
የጨረሱት ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡-
.....“ምንድን ነው ያደረጋችሁት?'
.........“የቀስቱን አረር መዘን አወጣንልዎ፡፡" አሏቸዉ፡፡ ይሄን ያህል ሶላት ላይ ሲሆኑ ቀጥታ ጌታቸዉ ጋር በኹሹዕ ይሰግዱ ነበር...የእኛስ ሶላት አሰጋገድ አስተዉለንዋልን???
⚡️⚡️⚡️ ዓሊ(ረ.ዐ)እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር ፡-የምእመናን አዛዥ ሆይ! የሶላት ሰአት ሲቃረብ የፊትዎ ቀለም የሚቀያየረዉና የሚንቀጠቀጡት ለምንድን ነዉ ??
ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት መልስ ሰጡ """ይህ ሰአት ሰማያትና ምድር እንዲሁም ተራሮች ሊሸከሙት እንዳልቻሉ በመግለፅ ያልተቀበሉትን አደራ ወደ ባለቤቱ የመመለሻ ሰአት በመሆኑ ነዉ ፡፡እኔ በትክክል መቻሌን አለመቻሌን አላዉቅም ለዛ ነዉ አሏቸዉ
✏️✏️ የሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ💚 የልጅ ልጅ የሆነዉ ሀሰን(ረ.ዐ) ምን ጊዜም ዉዱዕ ባደረገ ቁጥር ፊቱ ይገረጣ ነበር
አንድ ዕለት አንድ ሰዉ ሀሰን ሆይ!!! ዉዱዕ ባደረግክ ቁጥር ፊትህ የሚገረጣዉና ወደ ቢጫነት የሚቀየረዉ ለምንድን ነዉ ?? በማለት ጠየቀዉ
ሀሰን (ረ.ዐ) የሚከተለዉን መልስ ሰጠ፡- ብቸኛዉ የሀይል ባለቤት ታላቅና ባለግርማ ከሆነዉ አላህ ፊት የመቅረቢያ ሰአት በመሆኑ ነዉ ""
ሀሰን(ረ.ዐ) ወደ መስጊድ ሲገባ የሚከተለዉን ዱአ ያደርግ ነበር፡-
#ጠባቂየ_ሆይ!!!! ባሪያህ በቤትህ ደጃፍ ላይ ደርሷል፡፡ምህረት ሁሉ በእጅህ የሆነዉ ሆይ!!! ሀጢያተኛዉ ባሪያህ ወደ አንተ መጥቷል ፡፡ ቅን ባሪያዎችህ ሌሎች ሰዎች የሰሩባቸዉን መጥፎ ነገር ይቅር እንዲሉ አዘሀል፡፡ ምክንያቱም አንተ ይቅር ባይና ቸር ነህ፡፡ አላህ ሆይ በተለመደዉ ይቅር ባይነትህና ምህረትህ በደሌን ይቅር በል እዘንልኝም፡፡ ይል ነበር
ለሶላት ክብር ፍራቻ ነበራቸዉ እኛስ ??ብዙዎቻችን የመስጊድ ሙአዚን አዛን ሲል ሳንጠላዉ እንቀራለን ብላችሁ ነዉ?? ከኔ ጀምር ማን ነዉ አላህን ፈርቶ ሶላትን የሚሰግደዉ??? መልሱን ሁሉም በየቤቱ
✏️✏️ #ዘይኑል_አቢዲን ሁልጊዜም ዉዱዕ ሊያደርጉ ሲዘጋጁ ፊታቸው ይገረጣል፤ እንዲሁም ሶላት ሲጀምሩ እግሮቻቸው ይንቀጠቀጣሉ፡ ይህ ሁኔታ የሚታይባቸው ለምን እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ አሉ፡-ከማን ፊት ለመቆም እየተዘጋጀሁ እንዳለሁ አትገነዘቡምን?”ብለዉ መለሱላቸዉ
በአንድ ወቅት ዘይኑል አቢዲን ከቤታቸው ውስጥ ሆነው እያሉ ቤታቸው ተቃጠለ🔥🔥🔥፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ሁኔታ እርሳቸው አላወቁም ነበር፣ ሶላታቸውን እንደጨረሱ ስለተፈጠረው ሁኔታ ከነገሯቸው በኋላ ሰዎች የሚከተለውን ጥያቄ አቀረቡላቸው።
ቤትዎ በእሳት መያያዙን እንዳይገነዘቡ ያደረገዎት ነገር ምንድን ነው?”
ዘይኑል አቢዲን እንዲህ አሉ፡- "በመጪው ዓለም የሰውን ልጅ የሚጠብቀውና የተደገሰለትን የጀሀነም እሳት🔥🔥🔥 ሳስብ የዚህችን ዓለም እሳት እንድዘነጋው አደረገኝ፡፡"
ብለዉ መለሱላቸዉ
🌟🌟 የሙስሊም ቢን ያሲር ሶላትም ተመሳሳይ ሁኔታ ይንፀባረቅበት ነበር። አንድ ጊዜ በበስራ መስጊድ ውስጥ ይሰግድ ነበር፡ በቅፅበት መስጊዱ ተደርምሶ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ ይሁን እንጂ ሙስሊም ቢን ያሲር ይህን ክስተት ሳይገነዘብ በሶላቱ ላይ እንደተመሰጠ ቀጥሏል፡፡ ሶላቱን እንደጨረሰም ሰዎች ጠየቁት፡-
መስጊድ በላይህ ላይ እየተደረመሰ አንተ ግን አንድ ኢንች እንኳን አልተንቀሳቀስክም ይህ ሁኔታ ምንድን ነዉ?
ብለዉ ጠየቁት
....ሙስሊም ቢን ያሲር በመደነቅ የሚከተለዉን ጥያቄ
ለጠያቂዎች መልሶ አቀረበላቸዉ
...እንዴ! መስጊድ ተደርምሷል ነው የምትሉኝ?''
ጠያቂዎቹ በሙስሊም ቢን ያሲር መልስ ተአጀቡ::
✏️✏️ አንድ የአላህ ወዳጅ እንዲህ ይላል፡- “እኔ የዙህርን ሶላት ከዘኑን መስሪ ኋላ ቆሜ በመስገድ ላይ ነበርኩ፡፡ ያ ብሩክ ሰው 'አላሁ አክበር' ሲል #አላህ የሚለው ቃል በእርሱ ላይ የሚፈጥረውን ተፅእኖ ሳስተውል በአካሉ ውስጥ ነፍስ ያለው እስከማይመስል ድረስ ድርቅ ብሎ ነበር የሚቆመው፡፡ #አክበር የሚለውንም ከአፉ ሲያወጣው ከቃሉ ከባድነት ባለግርማ መሆን የተነሳ ልቤ ፍርስ ልትል ምንም አይቀራትም ነበር::
✏️✏️ አምር ኢብን አብዱሏህ ሶላት ላይ በሚቆምበት ጊዜ ከውጨኛው ዓለም ጋር የሚያስተሳስረው ነገር ሁሉ ይቆረጥና ከአላህ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያውክ አንዳችም ነገር አይፈጠርበትም ነበር፡፡''
ይህንን ሁኔታ ራሱ በአንደበቱ ሲገልፅ እንዲህ ይል ነበር፡-
“እኔ ሶላት ላይ እያለሁ የሰዎችን ድርጊትና ድምፅ ከምከታተል በቀስት ፍላፃ ሰውነቴን ብወጋ ይሻለኛል፡፡"ይል ነበር...
⚠️⚠️⚠️የእኛስ ሶላት ፈትሸነዉ እናዉቃለን??አሁን ላይ ሰዉ በስራ ቦታ እቤት ሲሰግድ ገና አሰጋጁን ኢና አእጦይናን ለሁለት አድርግ...እየተባለ ከአንገት በላይ እየሰገድን ነዉ ያለነዉ...አንተ አንቺስ ሁላችንም ሶላታችንን ፈትሸንዋልንን???
█
┻┻
╚▩PubLished by ▩╗
ISLAMIC UNIVERSITY
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━
4 another channal👇
t.me/Islam_and_Science
💐_⭐️💐⭐️___
t.me/IslamisUniverstiy_public_group