(342)
[ ገንዘብ ካለህ ሴት ልጅ ጥላህ አትሄድም ]
ሀብታም ከሆንክ፣ የተደላደለ ኑሮ የምትኖር ከሆነ፣ በወጣህ በገባህ ቁጥር በስጦታ ካንበሸበሽካት፣ የምትፈልገውን ሁሉ ከገዛኽላት ... ሴት ልጅ መቼም ጥላህ አትሄድም።
ውሸት .... ውሸት .... ውሸት
ሴትን ልጅ በገንዘብ አትይዛትም።
ኤለን መስክን ታውቀዋለህ ... ያ እንደውም የቴስላ መኪና አምራች ኩባንያ ባለቤት፣ የጠፈር ምርምር ጣቢያ ባለቤት እና ቲውተር ይባል የነበረውን ማህበራዊ ሚዲያ ገዝቶ X ብሎ ስሙን የቀየረው .... አዎ እሱ። ይኼውልህ የመጀመሪያ ሚስቱን አግብቶ ስድስት ልጆች ወልዷል። አንዴ መንታ፣ አንዴ ደሞ ሶስት ልጆችን በአንድ እርግዝና ... እንዴት ቢጫወተው ነው አልክ ... ተወው እሱ ይቅር። በዚህች አለም ላይ ሁሉም ነገር ላለው እንዳሽቃበጠ ነው። ብቻ ወደ ቁምነገራችን ስንመለስ ... ይህች ሴት አብራው የቆየችው ለስምንት አመት ብቻ ነው። ምነው ስትባል ግንኙነታችን "ጤናማ" አልነበረም አለች። እህህ ... ያ ሁሉ ሀብት እና ገንዘብ እያለው ሲሏት .... ገንዘብ የትኛውንም ነገር ጤናማ አያደርግም ብላ ውልቅ።
በዚህ የተናደደው ኤለን ቆይ ምን የመሰለችውን አግብቼ ባላደብንሽ ብሎ መነሳት .... ከሁለት አመት በኋላ እንደፎከረው ምራቅ የምታስውጥ አክተር አግብቶ ለሁለት አመት ሲያጫውት ከርሞ ተለያየ። ከአንድ አመት በኋላ ያልጨረስነው ፍቅር አለን ብለው እንደገና ተጋቡ። ያላለቀው ፍቅር የቆየው ለሶስት አመታት ብቻ ነው። እቺኛዋም በቃኝ ብላ ሄደች። አሁን እሱም ገንዘቡ የትኛዋንም ሴት እንደማያቆይለት አምኖ በየሄደበት እየወለደ ሴቶቹም በጋራ ልጅ እያሳደጉ መኖርን መርጠዋል።
ይሄ ሰው የአለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም ነው። የእሱ ገንዘብ ሴትን ካላቆየ የአንተ ሰባራ ሳንቲም በየትኛው አቅሙ ነው "በብሬ እይዛታለሁ" ብሎ ልብህን ያሳበጠው?
ቢል ጌትስ ጋር እንምጣ። ይሄ ሰው የማይክሮሶፍት ኩባንያ ባለቤት ነው። ለ27 አመት አብራው የቆየችው ሚስቱ ጥላው ስትሄድ ምክንያት ያደረገው "በግል ጉዳይ አልተግባባንም" የሚለውን ነው። አየህ ገንዘብ ከ27 አመታት በኋላ የሚመጣ የግል ጉዳይንም አይፈታም።
የአማዞኑ ባለቤት ጄፍ ቤዞስም ለ25 አመት የኖረው ትዳሩ ባለው የገንዘብ ብዛት አልዳነም። ብር አለኝ ብሎ ውሽማ ይዞ እሽኮለሌ ሲል አንተም ብርህም ገደል ግቡ ብላው እብስ። የምትካፈለውን ብር አስባ እንዳይመስልህ .... ትንሽ ነው የወሰደችው።
እንግዲህ አስበው እነዚህ ሁሉ ሰዎች ያላቸውን ብር አንተ እድሜ ልክህን አታገኘውም ... ግን ሴቷን በብሬ እይዛለሁ ብለህ ታስባለህ።
ደ|ደ|ብ ካልሆንክ በስተቀር የየትኛዋንም ሴት ታማኝነት በገንዘብ እንደማትገዛው መረዳት አለብህ።
በፍቅር ስም አብረህ ስትጃጃል ስለከረምክ ጥላህ አትሄድም ማለት አይደለም።
ጥሩ ሰው ነህ ማለት አስደግፋህ አትሸበለልም ማለት አይደለም። አንተ መልካም ስለሆንክላት ትሳሳልሃለች ማለት አይደለም።
ብልጥ ሁን ወዳጄ
ሴትን ልጅ አስሮ የሚያስቀምጣት ገንዘብህ፣ ፍቅርህ፣ ጥሩነትህ፣ መልክህ፣ የአልጋ ላይ ነብርነትህ አይደለም .... ፍላጎቷ ብቻ ነው።
እንደውም ገንዘብህ አስሮ እንደሚያስቀምጣት በተማመንክ ቁጥር የመሄዷ ነገር እርግጥ እየሆነ ይመጣል።
ጢባርህንም .... ትቢትህንም .... እብሪትህንም በልኩ አድርገው። አለበለዚያ ታበርድልሃለች !!
~
... ብቻ ነገሩ ውስብስብ ነው !!
~
✨ ባሻ ዘብሔረ ጠቅላይ ግምጃ ቤት ✨
★★★ ኦሮማይ ★★★
🧘♀️🧘🧘♂️
© Abby Junior
t.me/IslamisUniverstiy_public_group