Forward from: Bahiru Teka
🔷 ተውበት ከማድረግ ምን እስከሚሆን ነው የምጠብቀው ?
አላህ በተለያየ ዘመን የተለያዩ መልእክተኞችን ልኮ ህዝቦችን አስጠንቅቋል ። እንቢተኝነታቸው ሲበዛ በአመፃቸው ሲዋልሉ ማናለብኝነታቸው ሲያይል አቅማቸውን ሊያሳያቸው የውርደት ካባ ሊያከናንባቸው የሱን ሀያልነት ሳይወዱ በግዳቸው እንዲቀበሉ ሊያደርጋቸው አይናቸው እያየ ምድር እንዲውጣቸው አውሎ ንፋስ እንዲያነሳቸው ከሰማይ የእሳት ዝናብ እንዲዘንብባቸው ከምድር የፈላ ውሃ እንዲፈልቅባቸው በማድረግ በዱንያ ላይ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለሌላ መማሪያ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ። ነገር ግን የሰው ልጅ ቀልቡ ከድንጋይ የበለጠ የጠነከረ በመሆኑ ካለፈው ከመማር ይልቅ ይበልጥ በማመፅ የአላህን ህግ በመጣስ ለሌላ ጥፋት እራሱን በማዘጋጀት አሻፈኝ በማለት ከዘመን ዘመን ጥፋቱ እየባሰ ቅጣቱም ፉጡራንን እያመሰ ለእንሰሳትና አእዋፍት ተርፎ ምድር በሰው ልጅ አመፅ ሰላሟን አጥታ እያለቀሰች ነው ።
ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ መንስኤው የሰው ልጅ የመጥፎ ስራ ውጤት ነው ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ በተለያዩ አንቀፆች ነግሮናል ።
ቀጥሎ ጥቂቶቹን እንመልከት :–
وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ
الشورى ( 30 )
" ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው ፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል " ፡፡
አሁንም በሌላ አንቀፅ እንዲህ ይላል :-
« ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ»
الروم ( 41 )
" የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ) ፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና "፡፡
የሰው ልጅ የአላህ ፀጋ ከምድርም ከሰማይም እየመጣለት አሻፈረኝ ሲል ወደ ቅጣት የሚቀይረው መሆኑን ሲነግረን እንዲህ ይለናል :-
« وَضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا قَرْيَةً كَانَتْ آمِنَةً مُّطْمَئِنَّةً يَأْتِيهَا رِزْقُهَا رَغَدًا مِّن كُلِّ مَكَانٍ فَكَفَرَتْ بِأَنْعُمِ اللَّهِ فَأَذَاقَهَا اللَّهُ لِبَاسَ الْجُوعِ وَالْخَوْفِ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ »
النحل ( 112)
" አላህ ጸጥተኛ፣ የረካች፣ ሲሳይዋ ሰፊ ኾኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢኣት የረኃብንና የፍርሃትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ (መካን) ምሳሌ አደረገ " ፡፡
እነዚህ ሙሲባዎች አላህ ሰዎች ሲያምፁ ከሱ አምልኮት ሲርቁ ማናለብኝ ሲሉ የሚያመጣቸው የሱ ቅጣቶች ናቸው ። ወደርሱ ካልተመለሱ በቅጣት አለንጋ መገረፍ አይቀርም ።
ሙሲባ ሲመጣ አመፀኛውን ብቻ ለይቶ አይመታም ሁሉንም ይነካል ። ለዚህ ነው አላህ ለይቶ የማይነካውን ፈተና ተጠንቀቁ የሚለን ። ይህንንም በሚቀጥለው አንቀፅ እንመልከት: –
« وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ »
الأنفال ( 25 )
" ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ "፡፡
ተመልከቱ አላህ በዐለም ላይ ያመጣው ሁሉንም ያዳረሰው በሽታ ፣ በየሀገሩ በጎርፍ የሚያልቀው ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ የሚወድምው ከተማና መኖሪያው የነበረው ቤት ቀብሩ የሚሆነው ኸልቅ ፣ ለዘመናት በጆሯችን ስንሰማው የነበረውና አሁን በሀገራችን ላይ እየተከሰተ ያለው ርእደ መሬት ( የመሬት መንቀጥቀጥ ) መንስኤው የኛ ወንጀል ነው ሩቅ ማሰብ አያስፈልግም ። በጣም የሚያሳዝነው ሶሞኑን በጋሞ ከ300 በላህ ሰዎች በዚሁ መቅሰፍት አልቀዋል ። ሌሎች የመሬት መንሸራተት በሚል ሬሳቸው ጠፍቶ ቀርቷል ። አልቆመም አሁንም የማንቂያ ደወሉ እየተዛመተ ወደ ደሴ ከተማ ደርሶ ንብረት አውድሟል ። ታዲያ አሁን ከሰማይ የቅጣት እሳት እንዳይዘንብ ያልተፈራ መቼ ሊፈራ ነው ? ሁላችንም ተውበት አድርገን ወደ አላህ ተመልሰን ልንለምነው ይገባል ። በተቻለን አቅም ከጥፋቱ ሜዳ ርቀን ሰዎች እሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩ ወደ ነብዩ ሱና እንዲመለሱ ዳዕዋ ልናደርግ ይገባል ። ከተለያዩ ወንጀሎች ርቀው ተውበት አድርገው ወደ አላህ እንዲመለሱ ማስታወስ የግድ ነው ። ይህ ሀላፊነት በነዋይ የሰከሩት ፣ እውቅና ፍለጋ ከአቋማቸው የተንሸራተቱት ይወጡታል ማለት ቂልነት ነው ። በመሆኑም ሀላፊነቱ በተውሒድ ተጣሪዎች ጫንቃ ላይ የወደቀ እውነታ ነውና የነብያት ወራሾች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሀላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ።
ካልሆነ መጠበቅ ያለብን የባሰ ነገር ነው ።‼
http://t.me/bahruteka